Uncategorized

ወደ ቤተ መንግስት ያለፈቃድ ያቀኑት ወታደሮች ዝርዝር ቅጣት ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) ወደ ቤተ መንግስት ያለፈቃድ ካቀኑ ወታደሮች ውስጥ 66ቱ ላይ የተላለፈባቸው ዝርዝር ቅጣት ይፋ ሆነ። ከነትጥቃቸው ያለፈቃድ ወደ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ካመሩት 200 የሰራዊት አባላት መካከል 66ቱ ላይ ከ5 እስከ 14 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡ ፋይል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ከ500 ሰው በላይ በተገኘበት ግልጽ ችሎት  መታየቱ ታውቋል። በውሳኔው መሰረት አንድ ተከሳሽ በ14 ዓመት ጽኑ ...

Read More »

አቶ መላኩ ፈንታ የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር(አልማ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ በሕወሀት አገዛዝ ወቅት በሐሰት ተወንጅለው ላለፉት 5 አመታት በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል። ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ ያገኙት አቶ መላኩ ፈንታ ለእስር በባለስልጣናት የተዳረጉት የተሰወረ ቀረጥ እንዲከፈል በመታገላቸው እንደሆነ ሲነገር ...

Read More »

ፕሬዝዳንት ኢሳይስ ኬንያ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 5/2011) በኢትዮጵያ፣ኤርትራና ሶማሊያ መሪዎች መካከል የተጀመረው የሶስትዮሽ የምክክር መድረክ አካል የሆነ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ሞቃዲሾ የነበሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይስ አፈወርቄ ዛሬ ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል።           ወደስልጣን ከወጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶማሊያን የጎበኙት አቶ ኢሳያስ አፈወርቄ፣ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሚስተር መሃመድ አብዱላሂ ጋርበሁለቱ ሃገራትና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተመልክቷል።           ይህ በእንዲህ እንዳለም የአልሻባብ ኮማንደር የነበረውና ከአልሻባብ የከዳው ሙክታር ሮቦው በሶማሊያ ...

Read More »

ቱባቱባ የቀድሞ ባለስልጣናትን ወደ አንድ ቦታ መሰብሰብ ይገባል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 05/2011) በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት አልበኝነት መልክ ለማስያዝ ቱባቱባ የቀድሞ ባለስልጣናቱን ወደ አንድ ቦታ መሰብሰብ እንደሚገባ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አሳሰቡ። የትግራይ ህዝብም በውስጡ የበቀሉትንአረሞች እየሰማ የነርሱ መሸሸጊያ ሊሆን አይገባም ያሉት ፕሮፌሰርር መስፍን ወልደማርያም ሌላውም ህዝብ የትግራይን ህዝብ ከህዉሃትለይቶ እንዲመለከት ጥሪ አቅርበዋል። እነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚሰብኩት ፍቅር፣ ሰላምና ይቅር ባይነት በህጋዊ ሰይፍ ካልታገዙ እነሱንም ሆነ ህዝቡን ወደ ...

Read More »

ማንነትን ማክበርና ማስከበር የልዩነት ግንብን መገንባት አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ /2011) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ማንነትን ማክበርና ማስከበር አጥር ማጠርና የልዩነት ግንብ መገንባት አይደለም ሲሉ ገለጹ። በጎንደር በተካሄደውና በአማራና ቅማንት ማህበረሰብ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሚመክረው መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት መሪዎች ከማለፋቸው በፊትየማያልፍ  ጠባሳ ለትወልዱ ጥለው እንዳያልፉ ሊጠነቀቁ ይገባል። አቶ ደመቀ መኮንን እንዳሉት ማንነትን ማክበርና ማስከበር አጥር ማጠርና የልዩነት ግንብ መገንባት አይደለም ። ህዝብን ማድመጥና ታሪካዊ ...

Read More »

የሃይማኖት አባቶች ጎሰኝነትን ከማራገብ እንዲቆጠቡ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 5/2011) የሃይማኖት አባቶች ጎሰኝነትን ከማራገብ እንዲቆጠቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ አቶ ለማ መገርሳ ከሃይማኖትአባቶችና ምሁራን የተውጣጣውን ስብስብ ባነጋገሩ ጊዜ  በአንዳንድ አካባቢዎችመጽሀፍ ቅዱስ በአንድ እጃቸው በሌላኛው ደግሞ የጎሳ ፓለቲካን የሚያቀነቅኑ የሃይማኖት አባቶች ጉዳይ አስቸግሮናል ሲሉ ገልጸዋል። ሰላም እየታጣ ነው፣ ሀገራችን ውሎና አዳሯ እሳት ማጥፋት መሆኑ አሳሳቢ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንት ለማ። የሃይማኖት አባቶቹ ትዕግስት አስፈላጊ ቢሆንም ሀገር ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰላምና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጀመረች

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 5/2011)የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሃገሪቱ እየታየ ያለውን አለመረጋጋትና ግጭት ለማስቆም በሚል በመላ ኢትዮጵያ የሰላምና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጀመረች። በመላ ሀገሪቱ 52 አህጉረ ስብከት የሚዳረሱበት ይህው የሰላምና የወንጌል ዘመቻ ለአንድ ወር የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተሰማሩት የዘመቻው አባላት በ5 ቡድኖች የተከፈሉና እያንዳንዳቸው በሊቀጳጳስ የሚመሩ እንደሆነ ከቤተክህነት አካባቢ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ለዚህ ሃገር አቀፍ የሰላምና የወንጌል ዘመቻ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከ2ሺህ በላይ ነዋሪዎች ቤተክርስቲያን መጠለላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011) ከአዲስ አበባ በተለምዶ አጃምባ በሚባል አካባቢ ቤት ሰርተው ለዓመታት የቆዩ ከ2ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ቤተክርስቲያን መጠለላቸውን ገለጹ። ህገወጥ ናችሁ ተብለው በሌሊትበተኙበት በአፍራሽ ግብረሃይል ቤታቸው የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች በፋኑዔል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተጠልለው መኖር ከጀመሩ 15ቀናትያለፋቸው መሆኑን ለኢሳት ገልጸዋል። በወቅቱ በድንገት በተወሰደው የማፍረስ ተግባር በተፈጠረ ግርግር በጥይትና በግፊያ 3 ሰዎች መሞታቸው ተመልክቷል። የከተማው አስተዳደር ምላሽ አልሰጠንም የሚሉት ተፈናቃዮቹ ህጻናትን ...

Read More »

የማዕከላዊ አፍሪካ ሚኒስትር በጦር ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011)የማዕከላዊ አፍሪካ ሚኒስትር የነበሩ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን የኮሚቴ አባል በጦር ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ። ግለሰቡን የያዘችው ፈረንሳይ ስትሆንወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ዘሔግ እንደሚወሰዱም ተመልክቱል። ፓትሪስ ኤድዋርድ ናጊሶና የተባሉት የማዕከላዊ አፍሪካ የስፖርት ባለስልጣን በቁጥጥር ስር የዋሉት በሃገሪቱ ከ4 ዓመት በፊት በተካሄደ ሃይማኖት መሰረት ባደረገ ጥቃት ተዋናይ ሆነው በመገኘታቸው እንደሆነም ተዘግቧል። እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የወጣችው ...

Read More »

ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ክፍል መዘጋቱ ተረጋገጠ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011) ማዕከላዊ በመባል የሚጠራው የወንጀል ምርመራ ክፍል መዘጋቱን አረጋግጬአለሁ ሲል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። ኮሚቴው ማዕከላዊን ተዘዋውሮ ከጎበኘበኋላ በሰጠው መግለጫ ማዕከላዊ ተዘግቶ ክፍሎቹ ለቡራዩ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መኖሪያነት እያገለገሉ ነው ብሏል።  የኮሚቴው አባላት አረጋገጥን እንዳሉትም በማዕከላዊ አንድም እስረኛ የለም። የነበሩት 139 እስረኞችም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ማረሚያ ቤት በአደራ መሰጠታቸውን ተረድተናል ብለዋል ...

Read More »