Amsterdam

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በድህረ ምርቃ ተማሪዎች ከፍያ ላይ 125 በመቶ የክፍያ ጭማሪ አደረገ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በድህረ ምርቃ ተማሪዎች ከፍያ ላይ 125 በመቶ የክፍያ ጭማሪ አደረገ ( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) ተማሪዎቹ ለኢሳት በላኩት መረጃ እንዳመለከቱት ዩኒቨርስቲው በድህረ ምረቃ ተማሪዎች ክፍያ ላይ 125 በመቶ ጭማሪ በማድረጉ በኑሮአቸው ላይ ጫና ፈጥሯል። ለጥናት ወረቀት ወይም ፕሮጀክት በክሬዲት 600 የሚክፍሉ ሲሆን ለ30 ክሬዲት እስከ 18 ሺ ብር ይከፍላሉ። ተማሪዎቹ የክፍያ መጠናቸው አቅምን ...

Read More »

የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዎች ታወቁ

የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዎች ታወቁ ( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) ይህ ሽልማት የ25 ዓመቷን ወጣት ወ/ሮ ናዲያ ሙራድን የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማትን በወጣትነቷ ያገኘኝ ሁለተኛዋ እንስት መሆን አስችሏታል። ባለፈው ተመሳሳይ ዓመት የ17 ዓመቷ ፓኪስታኒያዊቷ ወጣት ማላላ ዩሳፊዛይ የ2017 እ.ኤ.አ. ሽልማትን ማግኘቷ ይታወሳል። የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ተወላጅ የሆኑት የ63 ዓመቱ ዶ/ር ዴኒስ ሙክዌጌ በበኩላቸው ለበርካታ ዓመታት በእርስበእርስ ...

Read More »

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ( ኢሳት ዜና መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ/ም ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ በካማሺና ሌሎችም ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር በእየለቱ እየጨመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የተፈናቃዮች ቁጥር ከ150 ሺ በላይ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል። መንግስት ያቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አዲሱ ገብረ እግዚአብሄር መንግስት በቂ የመከላከል እርምጃ እንዳልወሰደ እና ግጭቱ መጨመሩን ሲገልጹ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ባለስልጣን ...

Read More »

በሰሜን ሸዋ የመብራት መጥፋት በነዋሪዎቹ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው።

በሰሜን ሸዋ የመብራት መጥፋት በነዋሪዎቹ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። ( ኢሳት ዜና መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ/ም ) በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች በተከታታይ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት የኤሌትሪክ መቆራረጥ በመፈጠሩ በነዋሪዎቹ እና በባለሃብቶች ሥራ ላይ ከፍጠኛ ጫና መፍጠሩን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በተለይም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በመብራት መጥፋት ምክንያት የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለኅብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ተቸግረዋል። ግምቱ ከ7.2 ሚሊዮን በላይ ...

Read More »

ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ በሚቀጥሉበትጊዜያት ስለሚመራበት የፖለቲካ አቅጣጫ ተናገሩ

ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ በሚቀጥሉበትጊዜያት ስለሚመራበት የፖለቲካ አቅጣጫ ተናገሩ ( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለ3 ቀናት የሚቆየውን ኢህአዴግ ጉባኤ በአዋሳ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ፓርቲያቸው የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በምን መልኩ ተግባራዊ እንደሚያደርግንና ወዴት አቅጣጫ ሊወስደው እንዳሰ በተናግረዋል። “ አገራችን የቀደመውን ጠብቀውና አዲስም አክለውበት ለመጪው በሚያስተላልፉ ተተኪ ወጣቶች እየተመራች፣ እየተገነባች የ21ኛው ...

Read More »

በከፋዞን ከ800 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

በከፋዞን ከ800 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) በደቡብ ክልል በከፋ ዞን ይኖሩ የነበሩ ከ882 ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። በ1946 ዓም ከሰላሌና ሜታሮ ቤት የተወሰዱ 20 ሺ የሚጠጉ የኦሮሞ ተወላጆች በከፋ ዞን እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ከ1983 ዓም ጀምሮ ቋንቋቸውን እንዳይጠቀሙ በመታገዳቸው ጥያቄ ማቅርባቸውን ተናግረዋል:፡ የአካባቢው ባለስልጣናት ...

Read More »

በቦረና አካባቢ ኦነግ ህዝቡን የጦር መሳሪያ እያስታጠቀ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው

በቦረና አካባቢ ኦነግ ህዝቡን የጦር መሳሪያ እያስታጠቀ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው ( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በቡሌ ሆራና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ታጣቂዎች፣ “ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች ተመልሰው ስልጣን የሚይዙ በመሆናቸው ትጥቃችን አንፈታም” በማለት ህዝቡን ሰብስበው በማናገርና ወጣቶችን እየመለመሉ በማስታጠቅላይ ናቸው። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሰዎች እንደተናገሩት፣ የታጣቂዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ህዝቡ ...

Read More »

አዴፓና ደኢህዴን መሪዎቻቸውን መረጡ

አዴፓና ደኢህዴን መሪዎቻቸውን መረጡ ( ኢሳት ዜና መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ተብሎ የተሰየመው ብአዴን አቶ ደመቀ መኮንን በሊቀመንበርነት እንዲሁም የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በምክትል ሊቀመንበርነት በመምረጥ ጉባኤውን አጠቃሏል። ድርጅቱ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ አቶ ተፈራ ደርበው፣ ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ አቶ መላኩ አለበል፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ አቶ ምግባሩ ከበደ፣ አቶ ላቀ አያሌው፣ አቶ ...

Read More »

በከፋ ዞን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ከ15 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ

በከፋ ዞን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ከ15 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ ( ኢሳት ዜና መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም )የአካባቢው ባለስልጣናት ለኢሳት እንደተናገሩት ባለፉት 3 ቀናት ማንነታቸው የማይታወቁ ታጣቂዎች በከምባታ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ነው። የቡልካቡል ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ታደለ ለኢሳት በስልክ እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ቀናት ከ15 ያላነሱ ሰዎች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተገድለዋል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ዜጎች አካባቢያቸውን ...

Read More »

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት በርካቶች እንደተገደሉ እና ከስድሳ ሺህ የሚበልጡ ዜጎች እንደተፈናቀሉ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወታደሮች ትጥቃቸውን ፈተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ መመሪያ ተላለፈ።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት በርካቶች እንደተገደሉ እና ከስድሳ ሺህ የሚበልጡ ዜጎች እንደተፈናቀሉ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወታደሮች ትጥቃቸውን ፈተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ መመሪያ ተላለፈ። ( ኢሳት ዜና መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም ) በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በፈጸሙት ትንኮሳ የተቀሰቀሰ ነው የተባለውና ለሳምንት የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ግጭት እስካሁን ቁርጥ ያለ እልባት አላገኘም። በተለይ በካማሽ ዞን በተባባሰው በዚህ ...

Read More »