Amsterdam

በኢሊባቦር ዞን በደርግ ጊዜ ስፍረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው

በኢሊባቦር ዞን በደርግ ጊዜ ስፍረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በ1977 ዓም የነበረውን ድርቅ ተከትሎ ከትግራይ ወደ ኢሉባቦር ዞን ተሰደው የነበሩና በመቱ ወረዳ በሮይ እና በቾ በሚባል አካባቢ እንዲሁም በሁሩሙ ወረዳ ያሉ ሰፋሪዎች ያላቸውን ማንኛውንም ንብረት ሸጨው እንዲወጡ በትግራይ ልማት ማህበር እና በህወሃት ታዘናል በማለት ንብረታቸውን እየሸጡ ...

Read More »

በርካታ የታሰሩ ወጣቶችን የጫኑ 2 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ገቡ

በርካታ የታሰሩ ወጣቶችን የጫኑ 2 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ገቡ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የአይን እማኞች ለኢሳት እንደገለጹት ዛሬ ከጠዋቱ 8 ሰአት ከ18 ደቂቃ ላይ በርካታ ወጣቶቹን የጫኑ 2 ኦራል መኪኖች ወደ አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ያመሩ ሲሆን፣ ወጣቶቹ በራሳቸው ልብስ አፋቸው ተለጉሞ፣ እጃቸውም በገደም ታስሮ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ሁለቱም መኪኖች ስናይፐር በታጠቁ የአጋዚ ወታደሮች እየታጀቡ በመጓዛቸው ...

Read More »

89 በመቶው ትምህርት ቤቶች ከዓለም አቀፍ መመዘኛ በታች መሆናቸውን የትምህርት ሚንስቴር ጥናት አረጋገጠ

89 በመቶው ትምህርት ቤቶች ከዓለም አቀፍ መመዘኛ በታች መሆናቸውን የትምህርት ሚንስቴር ጥናት አረጋገጠ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) ተማሪዎችና መምህራን በቋንቋ መግባባት ተቸግረዋል በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የጥራት ደረጃቸው አጠያያቂ ደረጃ ላይ መድረሱን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥራት ጉባዔ ላይ ተገልጿል። በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና መምህራን መካከል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ማነስ ምክንያት ...

Read More »

በተጠናቀቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በአባይ ጸሃዬ የተማራው ህወሃት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ጸብ ቀረሽ ክርክር ማድረጉ ታወቀ

በተጠናቀቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በአባይ ጸሃዬ የተማራው ህወሃት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ጸብ ቀረሽ ክርክር ማድረጉ ታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ለሳምንት በተደገረው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ህወሃት በአቶ አባይ ጸሃዬ ዋና ተከራካሪነት ተወክሏል። ከአቶ አባይ ጀርባ አቶ ስብሃት ነጋና አቶ በረከት ስምዖን ተሰልፈው በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ አድርገዋል። ኦህዴድ በአቶ ለማ መገርሳ ዋና ተከራካሪነት ሲቀርብ፣ ...

Read More »

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህራን በወታደሩ ላይ የሰላ ትችት ሲያሰሙ አረፈዱ

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህራን በወታደሩ ላይ የሰላ ትችት ሲያሰሙ አረፈዱ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ በቅጽል ስማቸው ጄኔራል ሾማ እየተባሉ በሚጠሩ ወታደራዊ አዛዥ እና በፕ/ር ጨመዳ ፊኒኒሳ በተመራው የመመህራንና የሰራተኞች ስብሰባ ፣ ሰራተኞቹ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ትችት ሲሰነዝሩ ውለዋል። ከጠዋት 2 ሰአት እስከ 6 ሰዓት በቆዬው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹ በስሜት ይናገሩ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። አንድ መምህር፣ “ክቡር ጄኔራል፣ ...

Read More »

የድል ሚድድ ደጋፊ ናቸው የተባሉ የኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች ቤተሰቦች አሁንም እየታሰሩ ነው

የድል ሚድድ ደጋፊ ናቸው የተባሉ የኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች ቤተሰቦች አሁንም እየታሰሩ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የሶማሊውን ክልል መሪ የአቶ አብዲ ኢሌን አገዛዝ ለመቃወምና በክልሉ ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን ለመታገል በውጭ የሚገኙ የሶማሊ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙትን ድል ሚድድ የተባለው ንቅናቄን ተከትሎ የንቅናቄው አባላትና አመራር ናቸው የተባሉ ቤተሰቦች እየተያዙ መታሰራቸው ቀጥሎአል። በቅርቡ በክልሉ ዱል ሚድድ የሚል እና ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ የሚጠይቅ ...

Read More »

ከ150 ያላነሱ በአብዛኛው የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው የጉምሩክ ሰራተኞች ከስራ ተቀነሱ

ከ150 ያላነሱ በአብዛኛው የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው የጉምሩክ ሰራተኞች ከስራ ተቀነሱ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ከተቀነሱት ውስጥ 98 በመቶ የሚሆኑት የህወሃት ወታደሮች የነበሩ ናቸው። ብዙዎቹ የትምህርት ማስረጃቸው ብቁ አይደለም በሚል እንደተባረሩ ኢሳት ከደረሰው ደብዳቤ ለማወቅ ችለናል። ኢሳት ትናንት ባቀረበው ዘገባ በሶማሊ ክልል 38 የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው እና ከመከላከያ ወደ ጉምሩክ ተዛውረው ለ8 ዓመታት ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች መቀነሳቸውን ጠቅሶ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 16 የጉምሩክ ጣቢያዎች 38 ሃላፊዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ 34 ቱ የትግራይ ብሄር ተወላጅና የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው።

በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 16 የጉምሩክ ጣቢያዎች 38 ሃላፊዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ 34 ቱ የትግራይ ብሄር ተወላጅና የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ምንጮች እንደገለጹት እነዚህ የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው አዛዦች ከመከላከያ በጡረታ ከተገለሉ በሁዋላ ያለ ትምህርት ደረጃቸው በትዕዛዝ ብቻ በመላ አገሪቱ ባሉ የጉሙሩክ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ላለፉት 8 ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ሲመዘብሩ ቆይተዋል። ዛሬ የትምህርት ...

Read More »

በሰሜን ወሎ ሮቢት ከተማ ላይ አንድ አውቶቡስ በድንጋይ ተመታ

በሰሜን ወሎ ሮቢት ከተማ ላይ አንድ አውቶቡስ በድንጋይ ተመታ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ የተነሳ ስካይ ባስ በሚል የሚጠራ የመንገደኞች ማመላለሻ አውቶቢስ ሮቢት ከተማ ላይ በድንጋይ ተመትቶ የሚከናው መስታውት መሰባባሩን ገልጸዋል። ወጣቶቹ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ በተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት ይድረስ አይድረስ የታወቀ ነገር የለም። ጥቃቱ እንደተሰነዘረ ከቆቦ የተነሱ ወታደሮች ወዲያውኑ አካባቢውን ...

Read More »

ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ

ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የመኢአድ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣት አወቀ አባተ፣ በጎንደር ሲካሄድ የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ትመራለህ ተብሎ በ2008 ዓም ከተያዘ በሁዋላ፣ ያልሰጠውን ቃል እንደሰጠ ተደርጎ እንዲፈርም ለማስገደድ ለ4 ቀናት ያክል እጆቹና እግሮቹ ታስረው ሲደበደብ መቆየቱን ተናግሯል። በድብደባው ብዛት በጥፍሮቹ ደም ይፈሰው እንደነበር ...

Read More »