በኢሊባቦር ዞን በደርግ ጊዜ ስፍረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው

በኢሊባቦር ዞን በደርግ ጊዜ ስፍረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በ1977 ዓም የነበረውን ድርቅ ተከትሎ ከትግራይ ወደ ኢሉባቦር ዞን ተሰደው የነበሩና በመቱ ወረዳ በሮይ እና በቾ በሚባል አካባቢ እንዲሁም በሁሩሙ ወረዳ ያሉ ሰፋሪዎች ያላቸውን ማንኛውንም ንብረት ሸጨው እንዲወጡ በትግራይ ልማት ማህበር እና በህወሃት ታዘናል በማለት ንብረታቸውን እየሸጡ እየወጡ ነው።
የአካባቢው ተወላጆች ” አብረን ኖረን፣ ስንት ችግር ነገር አሳልፈን ለምን ትሄዳላችሁ?”ብለው ቢለምኑዋቸውም፣ ” በአስቸኳይ ውጡ ተብለናል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ተመሳሳይ ትዕዛዝ እየተላለፈላቸው መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።