ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ

ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የመኢአድ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣት አወቀ አባተ፣ በጎንደር ሲካሄድ የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ትመራለህ ተብሎ በ2008 ዓም ከተያዘ በሁዋላ፣ ያልሰጠውን ቃል እንደሰጠ ተደርጎ እንዲፈርም ለማስገደድ ለ4 ቀናት ያክል እጆቹና እግሮቹ ታስረው ሲደበደብ መቆየቱን ተናግሯል። በድብደባው ብዛት በጥፍሮቹ ደም ይፈሰው እንደነበር የገለጸው አወቀ፣ በመጨረሻም አንዲት ሴት ፖሊስ በብልቱ ላይ የሃይላንድ ውሃ ልታንጠለጥልበት ስትመጣ ስቃዩን መቋቋም ባለመቻሉ ያለ ጥፋቱ ጥፋተኛ ነኝ ብሎ መፈረሙን ተናግሯል።
አወቀ በእስር ቤት ውስጥ የኦሮሞ ወጣቶች ሲንከባከቡት እንደነበርና እስር ቤት ከገባ በሁዋላ ስለ ኦሮሞ ወጣቶች የነበረው አስተሳሰብ ፍጹም መቀየሩን ተናግሯል።