በሽንሌ ዞን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ አለመላኩን የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በኢትዮ-ሶማሊ ክልል በሽንሌ ዞን ፣ በሃርዋ ፣ ገሚ፣ አይሎሶና ሌሎችም ቦታዎች አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ የተጎዱ ዜጎች እስካሁን ድጋፍ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለችግር ተዳርገዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤቶች መፍረሳቸውን፣ አንድ ሺ የሚሆኑ የእርሻ ማሳዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የአካባቢው ተወላጆች ...
Read More »Amsterdam
በአርቢትር ኢያሱ ፈንቴ ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ቅጣጥ ከተጣለባቸው የወልዋሎ ተጫዋቾእች መካከል የአምስቱ ቅጣት እንዲነሳ ተደረገ።
በአርቢትር ኢያሱ ፈንቴ ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ቅጣጥ ከተጣለባቸው የወልዋሎ ተጫዋቾእች መካከል የአምስቱ ቅጣት እንዲነሳ ተደረገ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ-ከመከላከያ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ የመሀል ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም የወልዋሎ ተጫዋቾችና የቡድን መሪው ዳኛውን መሀል አስገብተው የፈጸሙት ድብደባ ብዙዎችን ማሳዘኑና ማነጋገሩ ይታወሳል። ድርጊቱን ተከትሎ “ዳኞች ዋስትና ካልተሰጠን ዳግም አናጫውትም”፡በማለታቸው ፕሪሚየር ሊጉ ለተወሰነ ጊዜ ...
Read More »የዋልያ ቢራ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
የዋልያ ቢራ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በሆላንዱ ታዋቂ የቢራ ፋብሪካ ሃይነከን የተገነባው ቂሊንጦ በሚገኘው የቢራ ፋብሪካ ውስጥ በመጫንና በማውረድ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ500 የማያንሱ ሰራተኞች መብታችን አልተከበረልንም በሚል የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። አድማው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ በፋብሪካው የተመረቱ የቢራ ምርቶች ሳይሰራጩ ቀርተዋል። ሰራተኞቹን በኮንትራት የሚያሰራቸው ኤዶምያስ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ ...
Read More »ኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅሟ በመዳከሙ የአጭር ጊዜ ብድር መውሰድ አቆመች
ኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅሟ በመዳከሙ የአጭር ጊዜ ብድር መውሰድ አቆመች (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢትዮጵያ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ የተበደረችውን ብድር በወቅቱ ለመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መምጣቱን ተከትሎ በአጭር የክፍያ ጊዜና በከፍተኛ የወለድ መጠን የሚሰጡ ብድሮችን መበደር ማቆሟን የገንዘብ ሚኒስትሩ ለሪፖርተር ተናግረዋል። አገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች በቂ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች ተብሎ ቢታቀድም እቅዱ ሊሳካ አለመቻሉን ...
Read More »የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውሃ ችግር ምክንያት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውሃ ችግር ምክንያት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የኮምቦልቻ ግቢ ተማሪዎች ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓም በሰልፍ በመውጣት የውሃ ችግራቸው እንዲቃለል ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ የሚጠጣ ውሃ እንኳን በበቂ ሁኔታ ማግኘት አልቻሉም። ተማሪዎቹ ችግራቸውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም መልስ የሚሰጣቸው አካል አላገኙም። የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተገኝተው ተማሪዎችን ለማረጋጋት ...
Read More »የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በማስፈጸም ረገድ በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት ተገለጸ፡፡
የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በማስፈጸም ረገድ በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት ተገለጸ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የማስፈጸም ችግሩ በአንድ ሴክተር መስሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሴክተሮቻችን የሚታይ ችግር ነው የሚሉት የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን አብዛኛውን ነገር እያሰረ ያለው የማስፈጸሙ ችግር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከኢንቨስትመንት አኳያ ባለሃብት መማምጣት ላይ ችግር እንደሌለ ሚገልጹት ከፍተኛ አመራር ዋናው ችግር የመጡትን ባለሃብቶች በመጡበት ፍጥነት ወደ ስራ ...
Read More »በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚያዚያ አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ቀናት ከ5 በላይ የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚያዚያ አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ቀናት ከ5 በላይ የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ለአመታት በክልሉ በኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹት የአማራ ተወላጆች፣ ባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ ከ5 ያላነሱ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ብለዋል። ደባጢ ወረዳ ውስጥ የ14 አመት ታዳጊ የሆነው አበጠር ወርቁ እጅግ አሰቃቂ ...
Read More »በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው
በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የቤት ማፍረስ ዘመቻን ተከትሎ እስካሁን ከ20 ሺ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ መጠለያ የቀሩ ሲሆን፣ ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ ያደረጉ ነዋሪዎች ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ብዙዎቹ መደብደባቸውንና እስካሁን 2 ሰዎች መገደላቸውንና ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንደኛዋ ቤቷ ሲፈርስ እቃዋን ለማውጣት ስትገባ ቤቱን ...
Read More »የሐረሪ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣን ተነሱ
የሐረሪ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣን ተነሱ (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በሃረሪ ክልል የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ጥያቄዎች በአግባቡ አልመለሱም ሃላፊነታቸውንም በአግባቡ አልተወጡም በሚል ሲተቹ የቆዩት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ጨፌ ኦሮምያ ተዛውረዋል። በእርሳቸው ቦታ አቶ በቀለ ተመስገን የሐረሪ ክልል ኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ተመድበዋል። በሃረሪ ክልል የሚኖሩ ...
Read More »“ባለስልጣናቱ ወረው ለመብላት የተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች ተናገሩ
“ባለስልጣናቱ ወረው ለመብላት የተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ ከተሞች በሃላፊነት ቦታ የተቀመጡ የገዥው መንግስት አመራሮች የድሃውን ህብረተሰብ ችግር ከመፍታት ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም የቆሙ በመሆናቸው ፣ሰርተው ሃገሪቱን ከመለወጥ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ማሳደዳቸውን መቀጠላቸው እንዳማረራቸው በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ አሁን በአመራር ላይ ያለው ትውልድ በአመራር ...
Read More »