ከ4 ሺ በላይ የሶማሊ ክልል ዜጎች ወደ ጅቡቲና ሶማሊላንድ ተሰደዱ (ኢሳት ሐምሌ 27/2010)የሶማሊ ክልል ተወላጆች የአብዲ አሌን አገዛዝ ለመቃወምና ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ድጋፋቸውን ለመግለጽ በድሬዳዋ የሚያካሂዱትን ስብሰባ በሃይል ለመቆጣጠር ወደ ስፍራው ያቀኑት የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት፣ በፌደራል ፖሊሶች እንዲመለሱ ከተደረጉ በሁዋላ በመንገዳቸው ላይ በአይሻ ወረዳ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ4ሺ 500 በላይ ዜጎች ወደ ጅቡቲና ወደ ሶማሊላንድ መሰደዳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የጅቡቲ መንግስት ...
Read More »Amsterdam
በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ከመሃል አገር የሄዱ ሰራተኞች እየታሰሩ ነው ቤተሰቦቻቸው አድራሻዎቻቸውን ማወቅ አልቻንም ሲሉ ተናግረዋል።
(ኢሳት ሐምሌ 27/2010)በመቀሌ፣ ዓድዋ፣ አክሱምና አዲግራት አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሾፌሮችን፤ በተለያዩ የስራ ጉዳዮች ከመሃል አገር ለስራ የተሰማሩ ወጣቶችን ካለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ “ሰላዮች ናችሁ” በሚል እያሰሩ እንደሚገኙ ታውቋል። ካለምንም ጥፋታቸው ከስራ ገበታቸው፣ ከመንገድ ላይ ታፍነው የተያዙት ዜጎችን አድራሻ የት እንደታሰሩና፤ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ ባለመቻላቸው ቤተሰቦቻቸው ስጋት ላይ ወድቀዋል። ከህግ አግባብ ውጭ ታስረው አድራሻቸው የጠፉ ዜጎችን ...
Read More »በትግራይ ክልል የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ መባሉ ትከክል አይደለም ሲል ፖሊስ አስታወቀ
(ኢሳት ሐምሌ 27/2010) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የ መከላከል አባላት ዋሉ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክል አይደለም ብሎአል። በወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀረ-ሽብርና የተደራጁ ወንጀሎኞች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር አበራ ሁንዴ እንደገለፁት፣ የሃገሪቱ ክልሎች የፖሊስ አባላትን እንደሚያሰማሩ ተናግረው፣ በትግራይ ክልልም አባላቱን በማሰማራት ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ “በማህበራዊ ሚዲያ የፖሊስ አባላቱ መቀሌ አየር ማረፊያ ላይ በክልል የፖሊስ ...
Read More »በደሴ ከተማ አንድ ተጠርጣሪ ወጣትን ለመያዝ በተፈጠረ ግርግር የትራንስፖርት አገልግሎት ለሰዓታት ተቋረጠ
(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)ነዋሪነቱ አራዳ በመባል በሚታወቀው የደሴ ከተማ ኗሪ የሆነውን ወጣት ባዬን ለመያዝ ፖሊስ የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሞክር ሁኔታውን በቅጡ ባልተረዱ የአካባቢው ነዋሪዎችና በፀጥታ አስከባሪዎች መሃከል ግጭት ተቀሰቀሰ። ተጠርጣሪውን ይዘው የአዲስ አበባ ታርጋ ባላት ሲቪል መኪና ሲጓዙ በነበሩት ፖሊሶች ላይ በከተማው መውጫ ኬላ አቅራቢያ ወጣቶች ግርግር በመፍጠር የተሽከርካሪዋን መስታወት በመስበር ግለሰቡን አስመልጠዋል። የፀጥታ አስከባሪዎቹ ጉዳት ...
Read More »የሶማሊ ክልል ተወላጆች ታሪካዊ ያሉትን ሁለተኛ ጉባኤያቸውን በድሬዳዋ በማካሄድ ላይ ናቸው
(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)የአብዲ ኢሌን አገዛዝ የሚቃወሙ የክልሉ ተወላጆች ሁለተኛ ስብሰባዎችን በድሬዳዋ ከተማ ላይ በማካሄድ ላይ ናቸው። የክልሉ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ባለፈው አዲስ አበባ ላይ ተደርጎ የነበረው የመጀመሪያው ስብሰባ በአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች የተደናቀፈ ቢሆንም፣ ዛሬ የተጀመረው የድሬዳዋው ስብሰባ ግን እስካሁን በሰላም እየተካሄደ ነው። የስብሰባው አስተባባሪዎች እንደሚሉት፣ ሶስተኛውን ስብሰባ ጅግጀጋ ላይ ለማድረግ እቅድ አላቸው። አስተባባሪዎቹ ...
Read More »የአንጋፋው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ
የአንጋፋው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ (ኢሳት ሐምሌ 26/2010)በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ 1948 ዓ.ም የተወለደው አንጋፋው የመድረክ ፈርጥ ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ባጋጠመው የኩላሊት ህመም በተወለደ በ62 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ላለፍት 42 ዓመታት የመድረክ ንጉስ እንደነበር በሙያ ባልደረቦቹና በጥበብ አድናቂዎች የተመሰከረለት ፍቃዱ ተክለማሪያም ኦቴሎ፣ ኤዲፐስ ንጉሥ፣ ሐምሌት፣ ቴዎድሮስ፣ ንጉሥ አርማህ፣ መቃብር ቆፋሪውና የሬሣ ...
Read More »ሰመጉ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከ700 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ
ሰመጉ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከ700 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 24 ቀን 2010 ዓ/ም )የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ)፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመረጃ አስደግፎ በ144ኛ ልዩ መግለጫው በዝርዝር ሪፖርቱ ከ735 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። ከጥር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2010 ...
Read More »ትናንት በሚኒሶታ የተዘጋጀው የኢትዮጵያውያን መድረክ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እና የአቶ ለማ መገርሳን የአመራር ብቃት ያመላከተ ነው ሲሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።
ትናንት በሚኒሶታ የተዘጋጀው የኢትዮጵያውያን መድረክ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እና የአቶ ለማ መገርሳን የአመራር ብቃት ያመላከተ ነው ሲሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ገለጹ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 24 ቀን 2010 ዓ/ም )19 ሺህ ኢትዮጵያውያን የታደሙበት የሚኒሶታው መድረክ ህብረብሄራዊነትን በማንጸባረቅ በኩል ልዩ ውበት የታዪበትን ያህል ፣መድረኩን ያስተባብሩ የነበሩ ጥቂት ሰዎች ዝግጁቱን ወደ ውጥረት የወሰዱት ገና የክብር እንግዶቹ ወደ ስፍራው ሳይደርሱ ነው። ከጥቂት ጊዜ ...
Read More »በሶማሊ ክልል ተቃውሞ ቀጥሎ ዋለ
በሶማሊ ክልል ተቃውሞ ቀጥሎ ዋለ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 24 ቀን 2010 ዓ/ም )ትናንት በራሶም ወረዳ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ በአፍዴራ ዞን ቀጥሎ ውሎአል። በአፍዴራ ዞን በሙሉ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን ለክልሉ ተወላጆች መብት መከበር የሚታገለው አቶ ጀማል ድሪሬ ገልጸዋል። የራሶም ወረዳ ተወላጆች የአብዲ አሌን ባለስልጣናት ማስወጣታቸውንና አስተዳደሩን መቆጣጠራቸውን አቶ ጀማል ገልጸዋል። በቅርቡ ዶ/ር አብይ ምሁራንን ሰብስበው ባናገሩበት ወቅት ፣ በክልሉ ያለውን ...
Read More »በአዊ ዞን የተፈጸመውን ግድያ የክልሉ መስተዳድር አወገዘ
በአዊ ዞን የተፈጸመውን ግድያ የክልሉ መስተዳድር አወገዘ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአዊ ብሄረሰብ ጃዊ ወረዳ ፈንድቃ ከተማ ላይ በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዘው የአማራ ክልል አስተዳደር፣ ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ለህግ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአማራ ቲሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት፣ ክልሉ ብሄርን መሰረት አደርጎ የሚካሄድን ጥቃት አይታገስም። የትግራይ ክልልም እንዲሁ ...
Read More »