መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሟቹ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ የኢትዮጵያ ፓርላማ ከገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የቀረበለትን ዕጩ ጠ/ሚኒስትር ሹመት ተቀብሎ በማጽደቁ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር በትናንትናው ዕለት ቃለመሃላ ፈጽመዋል፡፡ ፓርላማው ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረበለትን የሹመት ጥያቄ ተቀብሎ ያጸደቀበት ሒደት ግን ሕግና ሥርዓትን ያልተከተለ ነው በሚል አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች እየተቹት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአቶ ሀይለማርያምን ሹመት እንደምትቀበለው አስታወቀች
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የክቡር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መመረጥና የክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን መመረጣቸውን በማስመልከት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕ/ት ቤት ያስተላለፈችው መልክት” በሚል ርእስ ትናንት ባወጣችው መግለጫ ለአቶ መለስ ዜናዊ አመራር የነበራትን አድናቆትም ገልጣለች። ቤተክርስቲያኑዋ ” ይህ ያለፈው ዘመን ለአገራችንና ለአፍሪካ ብሎም ለአለም ህዝብ ትልቅ ...
Read More »በቂ የውጪ ምንዛሬ ያለው በወጋገን ባንክ ብቻ ነው ተባለ
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአገሪቱ ባንኮች በውጪ ምንዛሬ እጥረት በተጠቁበት በአሁኑ ጊዜ የወጋገን ባንክ ደንበኞች ብቻ ያለምንም እጥረት ንግዳቸውን እያቀላጠፉ መሆናቸው ተጠቆመ። የአይ.ኤም.ኤፍ የ ኢትዮጵያ ተወካይ አገሪቱ ለሁለት ወራት የሚበቃ የውጪ ምንዛሬ እንዳላት በቅርቡ ቢገልጹም ዋናውን ንግድ ባንክ ጨምሮ በ አገሪቱ የሚገኙ ባንኮች በሙሉ በከፍተኛ እጥረት በመጠቃታቸው ደንበኞቻቸውን ማገልገል እንደተሳናቸው የአዲስ አበባ የ ኢሳት ወኪሎች ከተለያዩ ...
Read More »አቶ መለስ ዜናዊ ሞተውም በከፍተኛ እጀባ እተጠበቁ ነው
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ለተቀበሩት ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ መለስ ዜናዊ ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታተም ቢከለከልም “ኦን ላይን” ጋዜጣ በመሆን በኢንተርኔት ስርጭቱን የቀጠለው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፤ አቶ መለስ ከተቀበሩ በኋላ ባልተለመደ ሁኔታ የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በሮች የተቆለፉ ሲሆን፤ መቃብራቸው በተለየ ኃይል ልዩ ጥበቃ እየተደረገለት ነው፡፡ ከቀብሩ ...
Read More »የብአዴን አባልነትን ያልተቀበሉ ሠራተኛ “ከተማዋን ለቀህ ጥፋ” ተባሉ
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጐንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብርሃጅራ ከተማ ውስጥ የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባልነትን ያልተቀበሉ ሠራተኛ ከከተማዋ ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ የከተማወወ አስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት እየፈፀሙ ነው። የአካባቢው ሹመኞችና የቢሮ ሀላፊዎች ራሳቸውን የተለዩ አድርገው ስለሚቆጥሩ የሠራተኞችንና የነዋሪዎችን መብቶች በማናለብኝነት እየጣሱ ...
Read More »እድገት የመብጥ ጥሰት መሸፈኛ ሊሆን አይገባም ተባለ
በሰብአዊ መብት፤ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ኪሳራ የሚመጣ የምጣኔ ሀብትና የቁጥር እድገት ለህዝብ ጎጂ ነው፤ ሲሉ የሂውመን ራይትስ ወች የአፍሪካ ክፍል ሀላፊ አቶ ዳንኤል በቀለ ተናገሩ። ምርጫ 97ን ተከትሎ ከፖለቲካ መሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ለሁለት አመታት ታስረው የነበሩት አቶ ዳንኤል በቀለ በኒው ዮርክ ታይምስ ላይ በጻፉት ጽሁፍ፤ ለጋሽ አገሮች ገንዘባቸውን መሪዎች የፖለቲካ ስልጣን እንዲያጋብሱበት ካደረጉ፤ መርዳት የፈለጉትን ህዝብ ይጎዳል ሲሉ ተናግረዋል። የሩዋንዳ፤ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ ቀጥሎ ዋለ
ለአራት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ቀጥሎ እንደዋለ አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ከስፍራው ለኢሳት ገለጹ። ኢሳት ያነጋገራቸው ሙስሊም እንደተናገሩት ሰሞኑን በፌስቡክና በሌሎችም መገናኛ መንገዶች እነደተነገረው፤ በዛሬው እለት አማኞች በታላቁ አንዋር መስጊድ በግዜ በመገኘት የእለቱን ጸሎት ከጨረሱ በሁዋላ፤ አስቀድሞ በታቀደው መሰረት መጀመሪያ ነጭ መሀረቦችን በማውለብለብ፤ ለጥቆም አላሁዋክበር በማለት፤ ድምጻቸው እንዲሰማ እንዲሁም የታሰሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባለት ...
Read More »የአማራ ክልል ወጣቶች መሪ ጫካ መግባቱን ገለጸ
የአማራ ክልል ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንትና የኢህአዴግ አባል የነበረው ወጣት ዘመነ ካሴ፤ ሥልጣን ላይ ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት ማስወገድ የሚቻለው በኃይል ነው በማለት ወደ ትግል ቦታ መግባቱን ለኢሳት ገለፀ። በኢህአዴግ አባልነቱና በወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንትነቱ ቤትና መኪናን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከሥርዓቱ ሲያገኝ መቆየቱን የገለፀው ወጣት ዘመነ ካሴ፣ በሀገሪቱ በተለይ በወጣቱ ክፍል ላይ እየደረሰ ያለው ችግርና ጉስቁልና እንዲሁም ተስፋ ማጣት፣ ከሥርዓቱ ለመለየትና ሥርዓቱን ለመታገል ...
Read More »የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ጸደቀ
ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ። አቶ ደመቀ መኮንንን ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የትምህርት ሚኒስትር አድርጎ ሾሟቸዋል። የፓርላማው አንዱ አጀንዳ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሾም መሆኑን ተናግረው ፓርላማውን የከፈቱት አፈ ጉባኤ፣ አቶ አባ ዱላ ገመዳ በተናገሩት መሰረት፤ በአቶ ደመቀ መኮንን ጠቋሚነት፤ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ጠቅላይ ሚነስትር ተደርገው ...
Read More »ለዩኒቨርስቲ መምህራን ሊሰጥ የነበረው አገር አቀፍ ስልጠና ተሰረዘ
መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የትምህርት ሚኒስቴር በቁጥር 7/ጠ-259/2311/04 በ 10/12/2004 ዓም በጻፈው ደብዳቤ ለዩኒቨርስቲ መምህራን ከመስከረም 10 እስከ 20 ቀን 2005 ዓም የሚቆይ አገራቀፍ ስልጣን ለመስጠት አቅዶ የነበረ ቢሆንም ይህን እቅዱን በመሰረዝ ስልጠናው ከመስከረም 3 እስከ 20 እንዲሆን አዲስ መመሪያ መበተኑን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። ዩኒቨርስቲው የቪዲዮ ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት በስድስት ኪሎ እና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አዳራሾችን ቢያዘጋጅም፣ በዩኒቨርስቲው ...
Read More »