.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢህአዴግ ለ2002ቱ ምርጫ ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማውጣቱን አንድ ሪፖርት አጋለጠ

መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ በዓለም የምርጫ ታሪክ እጅግ አስደናቂ በሆነ መልኩ 99 ነጥብ 6 በመቶ በማሸነፍ ወደ አውራ ፓርቲ ተሸጋግሬበታለሁ ባለው የ2002ቱ ምርጫ በድምሩ ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን ከግንባሩ የተገኘ ሪፖርት አመለከተ፡፡ ይህ ገንዘብ የኢትዮጵያ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ለምርጫ ቦርድ በቀጣይ ወር ለሚያካሂደው የአካባቢና የአዲስአበባ ምርጫን ጨምሮ ለመደበኛ በጀት ከፈቀደለት 19 ነጥብ 8 ...

Read More »

በኣዲስ ኣበባ ከባለቤቶቹ ፈቃድ ውጪ የቅዱስ ቂርቆስ መካነ መቃበር እየታረሰ ነው

መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ከፒያሳ  እስከ ጎፋ ካምፕ ድረስ ሊሠራ ከታሰበው የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ፥ የ ቅዱስ ቂርቆስ መካነ መቃብር ስፍራ ከሙታን ቤተሰብ አውቅና ውጭ  እየታረሰ እና የሙታን ኣጽምም  ከአፈር ጋር እየታፈሰ ወጣ ወዳለ ስፍራ እየተጣለ እንደሆነ ታውቋል። ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት በልማት ስም እየተካሄደ ያለውን ይህን ዘግናኝ ድርጊት እያስፈፀመ ያለው  የመንገድ ሥራውን በበላይነት እየሠራ ያለው  የመንገዶች ባለስልጣን ...

Read More »

የህወሀት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለድርጅታዊ ጉባኤ መቀሌ ገብተዋል

መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ካለፉት 21 አመታት ጀምሮ የመንግስትን ስልጣን በበላይነት የያዘው ህወሀት፣ ድርጅቱን ለረጅም ጊዜ የመሩት አቶ መለስ ዜናዊ ካረፉ በሁዋላ ያጋጠመውን የመከፋፈል አደጋ ሸፋፍኖ በማለፍ፣ ከመጋቢት 8 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት 11ኛ ጉባኤውን የሚያካሄድ ሲሆን፣ በጉባኤው ለመሳተፍ ነባር አመራሩ መቀሌ መግባታቸው ታውቋል። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ ...

Read More »

የአቶ መለስ ምስሎች አሁን ከአዲስአበባ ጎዳናዎች ላይ አልተነሱም

መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ እና በክልሎች የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ምስሎች በክብር እንዲወርዱ አቶ አዲሱ ለገሰ በመገናኛ ብዙሃን ያስተላለፉት ተማጽኖ እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም። በቀድሞ የህወሃት ታጋይ ባለቤትነት የሚመራው ሪፖርተር ጋዜጣ የአቶ መለስ ምስሎች ጸሐይና ቁር እየተፈራረቀባቸው ስለሆነ በክብር ይነሱ ሲል መጻፉን ተከትሎ የመለስ ፋውንዴሽን መስራች ጉባዔ ሰብሳቢ የሆኑት የቀድሞ ምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ ፋውንዴሽኑን ...

Read More »

በፕሬስ የሚካሄድ ስም ማጥፋትን በተመለከተ የወንጀል ሕጉ ሊሻሸል ነው

መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ በፕሬስ የሚካሄዱ የስም ማጥፋትን ለመዳኘት የወንጀል ሕጉን ለማሻሻል መታቀዱ ተጠቆመ፡፡ ከ2005-2007 የሚቆየውና እስካሁን ሳይጸድቅ በውይይት ላይ የሚገኘው ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃግብር ሰነድ ላይ እንደተመለከተው በመገኛኛ ብዙሃን አማካይነት የሚካሄዱና በተለይ በግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ ያነጣጠሩ የሰም ማጥፋት ዘመቻዎችን ለማስቆም የወንጀል ሕጉን ለማሻሻል ጥናት ይካሄዳል፡፡ ይህው ሰነድ በመገናኛ ብዙሃን የሚቀርብ የስም ማጥፋት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል በሚል የምሽት ጉዞዎች ሊከለከሉ ነው

መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-የትራንስፖርት እና መገናኛ ሚኒስቴር  የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ በምሽት የሚደረጉ  ጉዞዎችን ለማገድ ዝግጅት አጠናቅቄያለሁ አለ። እንደ ሚኒስቴር መስሪያ  ቤቱ ገለፃ ለመንገድ የትራፊክ ደህንነት አደጋ ዋነኛ መንስኤዎች ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ፣ ከተፈቀደ የሰው ቁጥር በላይ መጫን ፣የመንገድ ህግና ስርአትን አለማክበር እና ህገ-ወጥ የሌሊት ጉዞ  ናቸው፡፡ ስለሆነም  በህገወጥ የሌሊት ጉዞ ተሳታፊ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር በሚኒስቴር መስሪያ ...

Read More »

ኢትዮ ቴልኮም ግንቦት7 ን መሰለሉ ተጋለጠ

መጋቢት ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በህወሐት ጄኔራሎች አመራር ስር የወደቀው ኢትዮ ቴልኮም ፊን ሰፓይ በተባለ ሶፍትዌር የግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ መረጃዎችን ሲሰልል መገኘቱን ተቀማጭነቱ አውሮፓ የሆነ አንድ አለማቀፍ የሶፍት ዌር ኩባንያ አጋልጧል። ሞርጋን ማርኩዊስ ቦሪ፣ ቢል ማርዛክ ፣ ክላውዲዮ ጋርኔሪ እና ጆን ስኮት ሬይላተን ሲትዝን ላብ በተባለ ዌብሳይት ላይ ባወጡት ጽሑፍ ፣ ፊን ስፓይ የግንቦት 7ትን መሪዎች ...

Read More »

ተመድ ሜጀር ጄነራል ዮሀንስ ገብረመስቀልን ለአቤይ ግዛት ሀላፊ አድርጎ ሾመ

መጋቢት ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ፣  ባንኪ ሙን ደቡብ እና ሰሜን ሱዳንን እያወዛገበ በሚገኘው የአቢይ ግዛት ለሰፈረው የሰላም አስከባሪ  ጦር ሜ/ጄኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀልን ሾመዋል። ሜ/ጀኔራል ዮሀንስ ከዚህ ቀደም የሀይሉ አዛዥ የነበሩትን ሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን መተካታቸውን የተመድ ቃል አቀባይ ማርቲን ንስርኪይ ተናግረዋል። አዲሱ ሹም በወር ከ10 ሺ ዶላር በላይ እንደሚከፈላቸው ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወሳል። ...

Read More »

ታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርስ ነው

መጋቢት ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ ሆቴልን የገዙት ባለሀብት  ሆቴሉን ሙሉ በሙሉ አፍርሰው ሌላ ሆቴል ሊገነቡ እንደሆነ ተዘገበ። -ኢትዮጵያ ሆቴልና አዳማ ራስ ሆቴል ለባለሀብቱ የተሸጡት፤ በ134 ሚሊዮን ብር ነው በመሀል አዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንግዶችን እንዲያስተናግድ ከ50 ዓመታት በፊት የተገነባው የኢትዮጵያ ሆቴል ፈርሶ፣ በምትኩ 60 ፎቅ ያለው ሆቴል እንዲገነባ የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ መወሰኑን ምንጮቹን በመጥቀስ የዘገበው ...

Read More »

ለሙ እየተባለ በሚጠራው የአዲስ አበባ አካባቢ በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸው ታወቀ

መጋቢት ፫(ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ለሚ እየተባለ በሚጠራው ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኝ አካባቢ በኮብል ድንጋይ ማንጠፍ ስራ ላይ በተሰማሩ የደቡብ እና የኦሮሞ ተወላጅ ሰራተኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቁጥሩን በትክክል ለማወቅ ባይቻልም በርካታ ሰዎች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል።  ኢሳት ሰዎች መገደላቸውን መረጃ የደረሰው ቢሆንም፣ አሀዙን ከመንግስት ወይም ከሌላ ገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልቻለም። ይሁን እንጅ አንድ ...

Read More »