ተመድ ሜጀር ጄነራል ዮሀንስ ገብረመስቀልን ለአቤይ ግዛት ሀላፊ አድርጎ ሾመ

መጋቢት ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ፣  ባንኪ ሙን ደቡብ እና ሰሜን ሱዳንን እያወዛገበ በሚገኘው የአቢይ ግዛት ለሰፈረው የሰላም አስከባሪ  ጦር ሜ/ጄኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀልን ሾመዋል።

ሜ/ጀኔራል ዮሀንስ ከዚህ ቀደም የሀይሉ አዛዥ የነበሩትን ሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን መተካታቸውን የተመድ ቃል አቀባይ ማርቲን ንስርኪይ ተናግረዋል።

አዲሱ ሹም በወር ከ10 ሺ ዶላር በላይ እንደሚከፈላቸው ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወሳል።

ሜ/ጀ ዮሀንስ ገብረመስቀል በ 55 ሚሊዮን ብር አንድ ዘመናዊ ህንጻ ማሰራታቸውን በፎቶ ግራፍ አስደግፈን መዘገባችን ይታወሳል።