መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል ግቢ ውስጥ አዲስ ቤተመንግሥት ሊገነባ መሆኑን ምንጮችን በመጥቀስ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል። የስብሰባ ማዕከል ያለበት ቦታ ለቤተመንግሥቱ ግንባታ የተመረጠው፣ ቦታው ከመሐል ከተማ ወጣ በማለቱ፣ ዙሪያ ገባው ለደህንነት ምቹ ስለሆነ፣ መንግሥት ከምኒሊክ ቤተመንግሥት ወጥቶ የራሱን አዲስ ታሪክ ለመስራት በመፈለጉ ነው ተብሎአል። በስብሰባ ማዕከል ዙሪያ የሚገኙ የድሃ መኖሪያ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የገዢው ፓርቲ አባላት እንዲሆኑ እየተጠየቁ ነው
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን በግድ የፓርቲ አባል እያደረገ ያጠመቀው ኢህአዴግ አሁን ደግሞ በአካል ጠና ያሉትን ታዳጊ ወጣት የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን የአባልነት ፎርም እያስሞላ እንደሚገኝ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ታዳጊ ወጣቶች በጠርናፊ መምህራን በኩል እየተመለመሉ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በዚህ ሳምንት በመላ አዲስ አበባ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚማሩትን ታዳጊ ወጣቶች በግማሽ ቀን ሥልጠና የመግባቢያ ዝግጅት ...
Read More »የኬንያ ጠ/ፍርድ ቤት ምርጫው ትክክለኛ መሆኑን አረጋገጠ
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ወር በተካሄደው የኬንያ ምርጫ ፣ በስልጣን ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚ/ር ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያቀረቡትን ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል። ዳኛ ዊሊ ሙቲንጋ ምርጫው ትክክለኛ መሆኑን፣ አሁሩ ኬንያታም ምርጫውን ማሸነፋቸውን ገልጸዋል። ተሸናፊው እጩ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ኦዲንጋ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ ብለዋል። ዳኛው ሁሉም ኬንያውያን ለአገሪቱ ሰላምና ደህንነት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መክረዋል። ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣናት እያስፈራሩዋቸው መሆኑን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት ተፈናቃዮች ተናገሩ
መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ ተወላጅ አርሶደአሮች ከክልሉ ዋና ከተማ እና ከዞኑ የተውጣጡ ባለስልጣናት ዛሬ ሰብስበው ያነጋገሩን ቢሆንም ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ መልስ ሰጥተውናል በማለት ለኢሳት ተናግረዋል። አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ባለስልጣናቱ ከተማውን ለቀው ወደ ወረዳቸው እንዲሄዱ፣ የተቀሙትን ሀብትና ንብረት በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡም ” ቀድሞ ማን ሂዱ አላችሁ ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት ለአባይ ግድብ መዋጮ የጠራውን ሰብሰባ እንዲቋረጥ አደረጉ
መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሱት የመንግስትን ፖሊሲ በመቃወም ነው። ጉዳዩን በማስመልከት ቃለመጠይቅ ያደረግንለት አቶ ሙሉጌታ ፈለቀ “ኢትዮጵያኑ መንግስት በድብቅ ስብሰባ ማዘጋጀቱን እንደሰሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰባስበው በመቃማቸው የመንግስት ባለስልጣናት ስብሰባውን በመሰረዝ አዳራሹን ለቀው መውጣታቸውን እና መንግስት ከፍሎ በተከራየው አዳራሽ የራሳቸውን ስብሰባ ማካሄዳቸውን” ገልጸዋል። በተቃውሞም ግጭት አለመነሳቱንም አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል
Read More »በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ
መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሞ የውይይት መድረክ አዘጋጅነት ሚኒሶታ ውስጥ ሲካሄድ የሰነበተውን ውይይት ተከትሎ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ። የፓርቲው ስያሜ፦” የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር” እንደሆነ በምስረታው ጊዜ ይፋ ሆኗል። ይፋ ከተደረገው የፓርቲው ዓላማና ፕሮግራም ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመታገል የኦሮሞ ህዝብ ነፃነቱን እንዲቀዳጅና ራሱን በራሱ ማስተዳደር እንዲችል ይሠራል። በ አቶ ሌንጮ ...
Read More »አለማቀፍ መንግስታዊ ድርጅቶች ባደረጉት ጫና ካራቱሬ ገንዘብ ለመበደር አለመቻሉን አስታወቀ
መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ እንደዘገበው ኦክላንድ የምርምር ድርጅቶችን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት ባሰረፉት ጫና ኩባንያው ከአለማቀፍ ድርጅቶች ገንዘብ ለመበደር ባለማቻሉ ከህንድ መንግስት ለመውሰድ ሳይገደድ አይቀርም። የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሳይ ራካማራሺና እንደተናገሩት በ100 ሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከሌላ ወገን ለማግኘት ፈቃድ አግኝተዋል። ካራቱሬ በኢትዮጵያ ሰፊ የእርሻ መሬት በመውሰድ ሩዝ በማምረት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። ድርጅቱ 6 ሚሊዮን 500 ...
Read More »ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀዋል
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከ3 እስከ 4 ሺ የሚሆኑ ከቤንሻcccጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ከመስተዳድሩ ፊት ለፊት ባለ ሜዳ ላይ ያለምንም መጠለያ እንዲሰፍሩ ተደርጓል። ከከተማው ነዋሪዎች ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ተፈናቃዮቹ ቀን በጸሀይ፣ ሌሊት በብርድ እየተሰቃዩ ነው። እጅግ በርካታ ህጻናትና ሴቶች ከተፈናቀሉት መካከል ይገኙበታል። ተፈናቃዮች ከአካባቢያቸው ይዘውት የመጡትን ዱቄት እየጋገሩ በበመገብ ...
Read More »መንግስት እና ነጋዴው በዶላር አቅርቦት ዙሪያ ያላቸው ውዝግብ ጨምሯል
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረውን ከፍተኛ የዶላር እጥረት ተከትሎ ነጋዴዎች ላለፉት 8 ወራት ኤልሲ ከፍተው እቃዎችን ለማስገባት ሳይችሉ ከመቅረታቸውም በተጨማሪ አብዛኛው የውጭ ምንዛሬ መንግስት ለሚያስገነባቸው ግንባታዎች አቅርቦት መግዢያ ብቻ እንዲፈቀድ አድርጎ ቆይቷል። ሰሞኑን መንግስት ለነጋዴዎች ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ማንም በውጭ ንግድ ላይ የተሳተፈ ሁሉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት እንደሚችል ግልጽ አድርጓል። ይሁን እንጅ አዲሱ ...
Read More »መንግስት ለአባይ ግድብ ግንባታ ከህዝብ ለመሰብሰብ ያወጣውን እቅድ ሳይተወው አይቀርም ተባለ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የአባይ ግድብን በሕዝብ ተሳትፎ ለመገንባት ባቀደው መሰረት ከመንግስት ሰራተኞች፣ባለሃብቶች፣አርሶአደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እያካሄደ ያለውን የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ዘንድሮም ለመቀጠልም አቅዶ ቢንቀሳቀስም ከህዝቡ የታሰበውን ያህል ምላሽ ባለመገኘቱ ለማቋረጥ ሳይገደድ እንደማይቀር ምንጮቻችን ገለጡ። የአባይ ግድብ ከተጀመረ በኋላ በተለይ ባለፈው ዓመት የመንግስት ሰራተኞች ሳይወዱ በግድ የአንድ ወር እና ከዚያ በላይ ደመወዛቸውን በአንድ ዓመት ...
Read More »