በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ

መጋቢት ፳  (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሞ የውይይት መድረክ አዘጋጅነት ሚኒሶታ ውስጥ ሲካሄድ የሰነበተውን ውይይት ተከትሎ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ።

የፓርቲው ስያሜ፦” የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር” እንደሆነ በምስረታው ጊዜ ይፋ ሆኗል።

ይፋ ከተደረገው የፓርቲው ዓላማና ፕሮግራም ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል  በመታገል የኦሮሞ ህዝብ ነፃነቱን እንዲቀዳጅና ራሱን በራሱ ማስተዳደር እንዲችል ይሠራል።

በ አቶ ሌንጮ ለታ ሰብሳቢነትና እና በ አቶ ዲማ ነገዋ ምክትል ሰብሳቢነት የሚመራው አዲሱ ፓርቲ ደንቡን በማጽደቅ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።