በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት ለአባይ ግድብ መዋጮ የጠራውን ሰብሰባ እንዲቋረጥ አደረጉ

መጋቢት ፳  (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሱት የመንግስትን ፖሊሲ በመቃወም ነው።

ጉዳዩን በማስመልከት ቃለመጠይቅ ያደረግንለት አቶ ሙሉጌታ ፈለቀ “ኢትዮጵያኑ መንግስት በድብቅ ስብሰባ ማዘጋጀቱን እንደሰሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰባስበው በመቃማቸው የመንግስት ባለስልጣናት ስብሰባውን በመሰረዝ አዳራሹን ለቀው መውጣታቸውን እና መንግስት ከፍሎ በተከራየው አዳራሽ የራሳቸውን ስብሰባ ማካሄዳቸውን” ገልጸዋል።

በተቃውሞም ግጭት አለመነሳቱንም አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል