አለማቀፍ መንግስታዊ ድርጅቶች ባደረጉት ጫና ካራቱሬ ገንዘብ ለመበደር አለመቻሉን አስታወቀ

መጋቢት ፳  (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ እንደዘገበው ኦክላንድ የምርምር ድርጅቶችን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት ባሰረፉት ጫና ኩባንያው ከአለማቀፍ ድርጅቶች ገንዘብ ለመበደር ባለማቻሉ ከህንድ መንግስት ለመውሰድ ሳይገደድ አይቀርም።

የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሳይ ራካማራሺና እንደተናገሩት በ100 ሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከሌላ ወገን ለማግኘት ፈቃድ አግኝተዋል።

ካራቱሬ በኢትዮጵያ ሰፊ የእርሻ መሬት በመውሰድ ሩዝ በማምረት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። ድርጅቱ 6  ሚሊዮን 500 ሺ የሚያወጣ ሩዝ ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረቡን ገልጿል።

የህንዱ ኩባንያ ከ100 ሺ ሄክታር በላይ መሬት 108 ሺ ዶላር በመክፈል ብቻ በሊዝ መግዛቱን ብሉምበርግ ዘግቧል።

ሟቹ ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ የአገሪቱን መሬት በነጻ በሚባል ሁኔታ ለውጭ ባላሀብቶች መስጠታቸው ከፍተኛ ወቀሳ እንዲሰርባቸው ማድረጉ ይታወሳል።