ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀዋል

 መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:- ከ3 እስከ 4 ሺ የሚሆኑ ከቤንሻcccጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ከመስተዳድሩ ፊት ለፊት ባለ ሜዳ ላይ ያለምንም መጠለያ እንዲሰፍሩ ተደርጓል።

ከከተማው ነዋሪዎች ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ተፈናቃዮቹ ቀን በጸሀይ፣  ሌሊት በብርድ እየተሰቃዩ ነው። እጅግ በርካታ ህጻናትና ሴቶች ከተፈናቀሉት መካከል ይገኙበታል። ተፈናቃዮች ከአካባቢያቸው ይዘውት የመጡትን ዱቄት እየጋገሩ በበመገብ ላይ መሆናቸውም ታውቋል።

እስካሁን ድረስ ተፈናቃዮችን ቀርቦ ያነጋገራቸው ባለስልጣን አለመኖሩንም ለማወቅ ተችሎአል።

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ 60 የአማራ ተወላጆችን  ይዞ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ 59 ሰዎች መሞታቸውን እንዲሁም ትናንት ሁለት ህጻናት በአይሲዙ መኪና ተጭነው ሲጓዙ ታፍነው መሞታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።