መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ሰፍረው የሚገኙት የአማራ ተወላጆች በቂ መጠለያ፣ በቂ ህክምናና በቂ ምግብ ማግኘታቸውን የዞኑ የምግብ ዋስትና እና የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ገልጸዋል። ው አቶ ያዛቸው በላይ ለኢሳት እንደገለጡት በከተማው የሚገኙት ተፈናቃዮች ለህክምና በሚመች ቦታ የኮብል ስቶን ድንጋይ ማምረቻ በነበረ ግቢው ውስጥ እንዲሰፍሩ ተደርጓል። አቶ ያዛቸው እንዳሉት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ሂደት ብዙ ጥያቄዎችን እንደሚያስነሳ ሂውማን ራይትስወች ገለጠ
መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መገለጫ በ29 የሙስሊም መሪዎች ላይ የተጀመረው የፍርድ ሂደት ለ40 ቀናት ከተቋረጠ በሁዋላ ዛሬ የሚጀመር ቢሆንም እስካሁን የነበረው የፍርድ ሂደት ተአማኒ እንዳልነበር ገልጿል። መሪዎቹ በእስር ቤት እያሉ ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ በቂ የሆነ የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ አለመደረጉንና የፍርድ ሂደቱ ከሚዲያ፣ እና ከሌሎች ታዛቢ አካላት ውጭ እንዲካሄድ መደረጉን ጠቅሷል። የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ...
Read More »የመንግስት መ/ቤቶች ሐብትና ንብረት በትክክል አለመታወቁ ለብክነትና ለሌብነት እንዲዳረግ ምክንያት ነው ተባለ
መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የፌዴራል መ/ቤቶች ሐብትና ንብረት በትክክል አለመታወቁ ለብክነትና ለሌብነት እንዲዳረግ ምክንያት መሆኑን ከፌዴራል የመንግስት ግዥ አስተዳደር የተገኘ ሰነድ ጠቆመ፡፡ የመንግስት የሐብትና ንብረቱ መጠን በትክክል አለመታወቅና ተመዝግቦ አለመያዙ ለጉዳትና ለብክነት በር ከፍቶ መቆየቱን ሰነዱ ጠቁሞ በመንግስት ንብረት አስተዳደር ያለውን ጉድለት ለመሸፈን ኤጀንሲው ተቋቁሞ ወደስራ ሊገባ መቻሉን ተመልክቷል፡፡ የመንግስት ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ...
Read More »በሐይል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ችግራችን ተባብሶአል ይላሉ
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ፣ የክልላቸው ባለስልጣናትም ሆኑ የፌደራል መንግስቱ መፍትሄ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ገለጸዋል። በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከመሀል ከተማ እንዲወጡ ተደርገው፣ ባከል እየባለች በምትጠራ ገጠራማ ቀበሌ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መገደዳቸውን በባከል ቀበሌ ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ በድጋሜ ጠየቀ
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዘፈቀደ የሚካሄዱ እስሮችን የሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል የሆነው ፍሪደም ናው የተባለው ተቋም እንደገለጸው ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አስሮ እስካሁን ማቆየቱ አለማቀፍ ህግን የሚጻረር ነው ። አምስት ገለልተኛ ፓናሊስቶች የጋዜጠኛ እስክንድርን እስር በመመርመር፣ እስሩ ህገወጥ መሆኑን በመግለጽ፣ ጋዜጠኛው በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጋዜጠኛው አያያዝ እና የፍርድ ሂደት አለማቀፍ ...
Read More »አቶ ናትናኤል መኮንን የረሀብ አድማ ጀመሩ
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል ተከሰው 18 አመት እስራት የተፈረደባቸው አቶ ናትናኤል መኮንን የረሀብ አድማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አቶ ናትናኤል አድማውን የጀመሩት ቤተሰቦቻቸውን ለአንድ ወር ያክል እንዳይጠቁ በእስር ቤቱ ሀላፊዎች ማእቀብ ከተጣለባቸው በሁዋላ ነው። በአቶ ናትናኤል ላይ የተጣለው ማእቀብ ፣ ከእስር ቤቱ ሀላፊዎች ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ነው። ባለቤታቸውን ልጆቻቸውን በመያዝ ...
Read More »በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ ተብሎ በመንግስት የተጠራውን ስብሰባ ተቃወሙ
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነዋሪነታቸው ፍራንክፈርት የሆኑ ኢትዮጵያውያን መንግስት በሙዚቃ ድግስ ስም አድርጎ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለማሰባሰብ ማቀዱን ከሰሙ በሁዋላ ወደ ስብሰባ አዳራሹ በመግባት ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶ እንደነበር በስፍራው የተገኙ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ” ከአባይ በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው በደል ይገደብ” በሚል ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ተውቋል።
Read More »33 የፖለቲካ ድርጅቶች ስለመጪው ምርጫ ህገወጥነት ህዝቡን ሊያወያዩ ነው
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉ 33ቱ የአዳማ ፔትሽን ፈራሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በመጪው እሁድ መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓም ህዝቡን ለውይይት ጠርተዋል። ከህዝቡ ጋር የሚደረገው ውይይት በአንድነት ፣ በመድረክ፣ በሰማያዊ እና በመኢአድ ፓርቲዎች አዳራሾች ከ ቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስብሰባው አላማም መጪው ምርጫው ህገወጥ መሆኑን ለህዝቡ ለማስረዳት ነው። በሌላ ...
Read More »መንግስት የክልል ነዋሪዎችን በአዲስ አበባ ምርጫ ሊያሳትፍ ነው
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባና የወረዳ ምርጫዎች የተመዘገበው መራጭ ቁጥር ከተጠበቀው በታች መውረዱ ያሰጋው መንግስት ፣ ከክልል ከተሞች የራሱ ደጋፊ አባላትን በማምጣት በምርጫው እንዲሳተፉ ዛሬ ስልጠና ሲሰጥ ውሎአል። ከክልል የመጡት ሰዎች በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ የስልጠና ጣቢያዎች በመጪው ምርጫ እንዴት ድምጽ እንደሚሰጡ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በነጻነት ትምህርት ቤት ...
Read More »9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ “ተረት ተረት” የሞላበት ነበር ሲሉ የቀድሞው የፓርላማ አባል ተናገሩ
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የፓርላማ አባል፣ የመድረክ ስራ አስፈጻሚና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ገብሩ ገብረማርያም ለኢሳት እንደተናገሩት የኢህአዴግ 9ኛው ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ተረት ተረት መሆናቸውን ገልጸዋል። “እኛ ትናንት የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙስና መዘፈቃቸውን፣ የሚዲያ ጉዳይ መነጠቁ የዲሞክራሲ ግንባታን የሚገድል መሆኑን” ስንነግራቸው ከቆየን በሁዋላ እነሱ ዛሬ መልሰው ይነግሩናል ያሉት አቶ ገብሩ፣ ተተካካን ይሉና ...
Read More »