ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀትን የበረሀ ትግል ታሪክ የሚዘክረውን ገሀዲ ቊጥር አንድ፣ ሁለት እና ሶስት የሚሉ መጽሀፎችን ከመጻፍ በተጨማሪ በትግራይ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በማጋለጥ የሚታወቁት አቶ አስገደ ገብረስላሴ ሁለተኛ ልጅ ታስሯል። የ28 አመቱ የማነ አስገደ ገብረስላሴ የሶፍት ዌር ኢንጂነረግ ምሩቅ ሲሆን፣ በውቅሮ በመምህርነት ሙያ ተቀጥሮ ነበር። አዲሱን ስራውን ሲጀምር አቶ አስገደ ልጅ መሆኑ በመታወቁ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍድር ቤት በአቶ አንዱዓለም አራጌ መዝገብ በተከሰሱት የህሊና እስረኞች ላይ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ አጸና
ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሀሙስ ሚያዚያ 24 ቀን 2005 የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ፣ የ2012 የፔን ኢንተርናሽናል ሽልማት አሸናፊ በሆነው እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ እና በሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች የቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ አድርጎ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የ18 ዓመት እስር ውሳኔ አጽንቷል። መሀል ዳኛው አቶ ዳኜ መላኩ ለረጅም ጊዜ ቀጠሮ ሲሰጡ ከቆዩ በሁዋላ ...
Read More »የታላቁ ሰማእት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ተነሳ
ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዲስአበባ የቀላል ባቡር ዝርጋታ ጋር በተያያዘ ይነሳል በመባሉ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ የነበረው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ዛሬ ለዓመታት ከቆመበት የክብር ቦታ ተነሳ፡፡ መንግስት ሐውልቱ በድንገት ለማንሳት በሞከረበት ሰዓት የአዲስአበባ ሕዝብ ያለምንም ጥሪ በመሰባሰብ ሒደቱን የተከታተለ ሲሆን ሐውልቱ ከተነሳ በኋላ በእንጨት ሳጥን ውስጥ ታሽጎ በሎቤይድ ተሸከርካሪ ተጭኖ ወደ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ቅጥር ግቢ ...
Read More »የመከላከያ ባለስልጣናት በደን ጭፍጨፋው ዋነኛ ተሳታፊዎች ሆነዋል ተባለ
ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክብረ መንግስት ከተማ ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች ” የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ከአካባቢው ደላሎች ጋር በመመሳጠር በእየለቱ በትላለቅ መኪኖች ጣውላዎችን እየጫኑ እንደሚያጓጉዙ” ገልጸዋል። ዛፎችን መቁረጥ እና ከክልል ክልል ማስተላለፍ ህገወጥ ቢሆንም የመከላከያ ባለስልጣናት ግን በዚሁ ንግድ ግንባር ቀደም ተዋናዮች ሆነዋል ብለዋል ነዋሪዎቹ። የመከላከያ መኪኖች በመንገድ ላይ የማይፈተሹ በመሆኑ ፣ ባለስልጣናቱ ጣውላዎችን እየጫኑ ወደ ...
Read More »መንግስት በድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች ላይ በድጋሜ ዘመቻ ሊከፍት ነው
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት በየሳምንቱ የሚያቀርቡት ተቃውሞ የስርአቱን ህልውና እየተፈታተነው በመምጣቱ መንግስት ችግሩን በድርድር ከመፍታት ይልቅ በከፍተኛ እና መካከለኛ እንዲሁም በቀበሌዎች አካባቢ ያሉ የተቃውሞ አስተባባሪዎችን በመለየት ሰብስቦ ለማሰር እና ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ ለመመስረት ማቀዱ ታውቋል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ታማኝ ...
Read More »የፌዴራል ዋና ኦዲተር በመንግስት መ/ቤቶች ከፍተኛ ምዝበራ መኖሩን አጋለጠ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ዋና ኦዲተር በኢትዮጽያዊያን 2004 በጀት ዓመት በ116 የፌዴራል መንግስት ተቋማት ላይ ባካሄደው ኦዲት በድምሩ በ84 መ/ቤቶች ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብና የውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ በወቅቱ ያለመወራረድ ችግሮች ማግኘቱን ይፋ አደረገ፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2004 በጀት ዓመት ሒሳብ የኦዲት ግኝት ሪፖርቱን ዛሬ ለፓርላማ ያቀረቡት ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ...
Read More »ሉሲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ ተገለጸ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እጅግ አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ያለፉትን 5 አመታት በአሜሪካ ያሳለፈችው ለኢትዮጵያ “የሰው ዘር መገኛ” የሚል ስም ያሰጠችው ብርቅየዋ የኢትዮጵያ ቅርስ ሉሲ ( ድንቅነሽ) ወደ አገሯ መመለሱዋን መንግስት አስታውቋል። በአሜሪካ በ350 ሺ ሰዎች እንደተጎበኘች የተነገረላት ሉሲ ወደ አገሯ የተመለሰቸው ትክክለኛዋ ሉሲ መሆኑዋን እና አለመሆኑዋን አለማቀፍ እውቅና ያላቸው ኢትዮጵያውያን የመስኩ ባለሙያዎች ማረጋገጫ አልሰጡም። ወደ አገሩዋ ...
Read More »በደብረማርቆስ ከተማ አንድ መሀንዲስ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ከተያዙ በሁዋላ በማግስቱ ተለቀቁ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ ባለሀብት ለኢሳት እንደገለጹት ፣ መሀንዲሱ ገንዘብ ካላመጣችሁ የግንባታ ፈቃድ አልሰጥም በማለቱ ባለሀብቱ ከዞኑ ፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በብሮቹ ላይ ልዩ ምልክት በማድረግ 13 ሺ ብር መስጠታቸውን ቀረውን 7 ሺ ብር እንደሚሰጡትም ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል። መሀንዲሱ ገንዘቡን ከተቀበሉ በሁዋላ ፖሊሶች በስፍራው ደርሰው በቁጥጥር ስር አውለውታል። ይሁን እንጅ ምክንያቱ በውል ...
Read More »የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኅብረት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል ጥሪ አስተላለፈ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ያለተፎካካሪ ሥልጣኑን በኃይል የተቆጣጠረውን ኢህአዴግ በማስወገድ የሕዝብ ሥልጣን ባለቤትነትን ለማምጣት ብቸኛው መፍትሔ በፅናትና በቆራጥነት መታገል ብቻ መሆኑ ተገለፀ። የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ ትላንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሀገራችን ከገባችበት ፈተናና ሕዝቡ ከሚቀበለው ሥቃይ ልናላቅቀው የምንችለው ከያዘን የፍርሃት ቆፈን ተላቀን ባንድነት በመቆም ቀኑ የደረሰውን አምባገነን ሥርዓት ወደተመኘው መቃብር ለመሸኘት በጽናት መታገል ብቻ ...
Read More »ኢትዮጵያ በሚመጣው ዓመት የኤሌክትሪክ እጥረት ያጋጥማታል
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት የ200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እንደሚያጋጥማት ጥናቶች አመለከቱ። ሀገሪቱ ይህንን ችግር ለመወጣት ባለፉት ዓመታት በወር 100 ሚሊዮን ብር ለጄኔሬተሮች ወጪ ስታደርግ ቆይታለች አሁንም በማውጣት ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ያካሄደውን ጥናት ጠቅሶ ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበው፣ ሀገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት የሚያጋጥማት የ200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ኢኮኖሚውን ...
Read More »