.የኢሳት አማርኛ ዜና

አፍሪካ ሚስጢራዊ በሆነ ስምምነት ሀብቷን እየተዘረፈች ነው ተባለ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ  ኮፊ አናን ፣ የቀድሞውን የናይጀሪያ መሪ ኦለሱጎን ኦባሳንጆ እንዲሁም የኔልሰን ማንዴላን ባለቤት ግራሻ ሚሸልን ያቀፍ የጥናት ቡድን ይፋ ባደረገው ጥናት አፍሪካ ግልጽነት በጎደለው ሚስጢራዊ ድርድሮች የተፈጥሮ ሀብቷን እየተዘረፈች ነው። ከታክስ ማጭበርበር ፣ በድብቅ በሚካሄድ የማእድን ማውጣት እና በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ወደ ውጭ ከመላክ ጋር በተያያዘ አፍሪካ በየአመቱ ...

Read More »

ታዋቂ የኢትዮጵያ ሶማሊ ተወላጆች የክልሉ ፕሬዚዳንት በድብቅ ያደረጉት ንግግር እየነቀፉ ነው

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢህአዴግ የሽግግር መንግስት ወቅት ለሶስት አመታት በዲፕሎማትነት፣ በመምህርነት እና በጋዜጠኝነት የሰሩትና በርካታ የታሪክ መጽሀፎችን የጻፉት አቶ መሀመድ ሀሰን ለኢሳት እንደተናገሩት ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሀመድ ኡመር  የተናገረው ከወያኔ በስሎ የቀረበለትን ነው በማለት ተናግረዋል። “ግለሰቡ ያልተማረ ነፍሰ ገዳይ ነው” የሚሉት አቶ ሙሀመድ ፣ የመለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ እንደነበረም ገልጸዋል። ክልሉ ለወያኔ ጄኔራሎች ...

Read More »

ጸረ ሙስና ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ የተዘረፈ ገንዘብ እና ሌሎች ንብረቶችን ወረሰ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራልየሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2005 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በሙሰኞች የተመዘበረ ከ8ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ፣ መሬት፣ ህንፃዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶችን ለመንግሥት ማስመለሱን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ከሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ብቻ በሙሰኞች የተመዘበሩ 8, ሚሊዮን 11 ሺ 710 ብር በጥሬ ገንዘብ ፣ 1 ሺ ...

Read More »

የፍትሕ ሚኒስትሩ በማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም አሉ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከብአዴን እና ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት በቅርቡ በተካሄዱት ጉባዔዎች የተነሱት የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ የመብት ጥሰት የለም ሲሉ ተናገሩ። በዛሬው ዕለት የመ/ቤታቸውን የ9 ወራት ሪፖርት ለፓርላማ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ ከብቸኛው የአንድነት ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ አቶ ግርማ ባቀረቡት ...

Read More »

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሬጂስትራር የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ አመራር አባላት ጠበቃን የክስ ማመልከቻ አልቀበልም ብለው መለሱ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት ጀሃዳዊ ሃረካት በሚለው ድራማ በመንግሥት የስም ማጥፋት ዘመቻ ተደርጎብናል ሲሉ ያቀረቡትን የክስ ማመልከቻ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሬጂስትራር አልቀበልም ማለቱ ተገለጠ። የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በዚህ የክስ ማመልከቻ 8 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት ጠበቃ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ...

Read More »

አንድነት መግለጫ አወጣ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነአንዱዓለም አራጌና በናትናኤል መኮንን የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ ማድረጉ በፍትሕ ተቋማት ላይ እምነት መጣል እንደማይቻል ማሳያ ነው ሲል አንድነት ፓርቲ ገለጠ። በፋሲካ በዓል እስረኞቹን ለመጎብኘት የሞከሩት የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትም በልዩ ኃይል ተባረሩ። አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ገዢው ፓርቲ በማን አለብኝነት የፓርቲው አመራሮችን አስሮ የሚሠራው ሽፍጦች ትግሉን የበለጠ ...

Read More »

በአውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጄኔቭ የተባበሩት መንግሥታት ዋና መ/ቤት ፊት ለፊት የሕዝብ ትዕይንት አደረጉ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት በጄኔቭ ስዊትዘርላንድ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በአማሮች ላይ የደረሰውን መፈናቀል የሚያሳይ የጽሑፍ፣ የድምፅና የምስል ማስረጃ ለሦስት ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ማስረከባቸውንም ባልደረባችን ወንድምአገኝ ጋሹ ከሥፍራው ዘግቧል። ከቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል በቅርቡ የተፈናቀሉትን አማሮች ሁኔታ በዋናነት በማንሳት ባለፉት 22 ዓመታት በሀገሪቱ የቀጠለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በማውሳት የተቃውሞ ድምፃቸውን ያስተባበሩት ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ በ አፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊትለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ አቀረበ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአብዛኛው በወጣቶች እና በሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ  እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በመጪው ሜይ 25  በ አፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ህዝባዊ ጥሪ አስተላለፈ። የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረገው የ አፍሪካ ህብረት 50ኛ ኣመት  በ ዓሉን በሚያከብርበት ዕለት ነው። ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰቡ ተቋማትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ በህጋዊውና ሰላማዊው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ ኩባንያን ካሳ እጠይቃለሁ አለ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አየር መንገዱ ካሳ የሚጠይቀው ከአምስት ወራት በፊት አዲስ ያስገባቸው ቦይንግ 787 አውሮፕላኖች  ብዙም አገልግሎት ሳይሰጡ ከበረራ ውጭ ተደርገዉ የቆዩ በመሆኑ ነዉ ፡፡ አውሮፕላኖቹ በረራ አቁመው የነበረው በባትሪያቸዉ ላይ ባጋጠማቸው ችግር ምክንያት በአሜሪካ የፌደራል የበረራ መስሪያ ቤት እገዳ ስለተጣለባቸዉ እንደነበር መዘገቡ  ይታወሳል፡፡ የኢትዮዽያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፥ ከዚህ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤቱን እንዲለቅ ተገደደ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለኢሳት በላኩት መረጃ እንደገለጹት ጋዜጠኛ ተመስገን ተከራይቶ በሚኖርበት ቀበና አካባቢ ያለው ቤቱን እንዲለቅ በአከራዩ የተነገረው አንድ የመስተዳድሩ ባለስልጣንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ አከራዩ ቤቱን እንዲያስለቀቁት ማስጠንቀቂያ ከሰጡዋቸው በሁዋላ ነው። የቤት አከራዩ ”  ሁለቱ ሰዎች መጥተው ለመሆኑ ተመስገን ምን እንደሚሰራ ያውቃሉ ወይ? ተመስገን ማን እንደሆነስ ጠንቅቀው ያውቃሉ ወይ?  ለማንኛውም ...

Read More »