ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጣና ሃይቅ ላይ ከ 100 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ ፋሲለደስ እየተባለ የሚጠራው ጀልባ በማእበል ተመቶ በመስጠሙ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ከ10 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸን ለማወቅ ተችሎአል። የአደጋው መንስኤም ከባድ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተ ማእበል መሆኑን ነው አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የድርጅቱ ሰራተ ለኢሳት የገለጹት ። ይሁን እንጀ ኢሳት ትክክለኛውን ምክንያት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአትዮጵያ የሚታየው የሀኪሞች እጥረት እየጨመረ ነው
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጽያ ሐኪሞችን የማሰልጠኑ ስራ ከታሰበው ግብ አኳያ አፈጻጸሙ ደካማና አሁንም የባለሙያ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ እየታየ መሆኑን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ አመለከተ፡፡ በጤና ዘርፍ ከሰው ኃይል አኳያ ከፍተኛ እጥረት እየታየ ያለው በሐኪሞች፣በአዋላጅ ነርሶች እና በሰመመን ሰጪ ነርሶች ደረጃ ያለው ነው ያለው ሰነዱ ባለፉት ጊዜያት በመደበኛ ፕሮግራም ሐኪሞችን ለማሰልጠን የሚወስደው ጊዜ ረጅም ከመሆኑና ...
Read More »በደሴ ዙሪያ አንድ ህዝብን ያሰቃያል የተባለ ሹም ተገደለ
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት6 ቀን 2005 ዓም ከቀኑ ስድስት ሰአት ላይ ሙሀመድ የሱፍ የተባለ የደሴ ከተማ ቀበሌ 12 ነዋሪ የ ቀበሌያቸውን የመሬት አስተዳደር ሹም አቶ አህመድ እንድሪስን በ2 ጥይቶች በመግደል ማምለጡ ታውቋል። ገዳይ አቶ ሙሀመድ የጦር መሳሪያ ከሌላ ታጣቂ ላይ በመቀማት ነው የቀበሌ ሹሙን ገድለው የተሰወሩት። ሟቹ ባለስልጣን የአካባቢውን አርሶአደሮች መሬት በመቀማት፣ ማዳበሪያ በግድ እንዲወስዱ ...
Read More »በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ ሰዎች በግፍ እየታሰሩ ነው
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍኖተ ነጻነት እንደዘገበው ሚያዚያ 18 ቀን 2005ዓ.ም. በሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል አቶ አንሙት እና አቶ መንግስት በቀለ የተባሉ ወጣቶች በሌሊት በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል። ግንቦት 3 ቀን 2005ዓ.ም. ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት መኮንን አድማስ በሚባል የፀጥታ ኃላፊ እና ወ/ሮ አሰለፈ ከበደ በሚባሉ የወረዳው ካቢኔ በመራዊ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን ወ/ሮ ሙሉ ሲሳይን ...
Read More »ኢሕአዴግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሪዎችን እየመለመ ነው
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው ምልመላውን እያከናወኑ ያሉት የሥልጣን ዘመናቸው በቅርቡ የሚያበቃው ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና ምክትላቸው አቶ አባተ ስጦታው፣ የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃንና ምክትላቸው አቶ ጀማል ረዲ ናቸው፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ድሪባ ኩማ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ መኩሪያ ኃይሌ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣ የፌዴራል ፖሊስ ጄነራል ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ወ/ሮ አዜብ ...
Read More »በኖርዌይ ኦስሎና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቅዳሜ በ18.05.13 ህዝባዊ ውይይት አደረጉ።
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ውይይቱ በሀገራችን በግፍ ለተገደሉ፤ በእስር ለሚንገላቱና ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚሰቃዩና ለተሰደዱ ወገኖች የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል። በርካታ ታዳሚዎችም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ ጥቁር ልብስ ለብሰው ተገኝተዋል። ውይይቱ የተጠራው በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል ሲሆን. በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚጫወተው ሚናና በሀገር ቤት በሰማያዊ ፓርቲ ስለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ፣. ...
Read More »ባህርዳር የተፈጸመው ግድያ እንቆቅልሽ እስካሁን አልተፈታም
ግንቦት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በባህርዳር 17 ሰዎችን በጥይት አርከፍክፎ በግፍ ከገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ፈቃዱ ናሻ ጋር በተያያዘ ግድያው ሲፈጸም በዝምታ ተመልክታችሁዋል በሚል 10 የፊድራል ፖሊስ አባላት ታሰረዋል፡፡ የገዳዩ የቀድሞ ፍቅረኛም ድርጊቱ ከተፈጸመበት ቀን አንስቶ በህግ ቁጥጥር ስር እንደምትገኝ ታውቋል፡፡ የፊደራል ፖሊስ ዋና አዛዥ ጄኔራል ወርቅነህ ገበየሁ ትላንት የተጎጅ ቤተሰቦችን ጎብኝተዋል፡፡ የተጎጅ ቤተሰቦች ለጄኔራል ወርቅነህ ገበየሁ “ገዳዩ ...
Read More »ታዋቂ አፍሪካውያን ወደ ውጭ ተዘርፎ በሚወጣው ገንዘብ ላይ የቡድን 8 እና 20 አገራት እርምጃ እንዲወስዱ ግፊት ማድረግ ጀመሩ
ግንቦት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ ለኢሳት በላከው መረጃ የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ኮፊ አናን፣ የታዋቂው የነጻነት አባት የኔልሰን ማንዴላ ባለቤት ግራሺያ ሚሼል እና ሌሎች ታዋቂ አፍሪካውያን በጋራ ለቡድን 8 እና ለቡድን 20 አገራት መሪዎች በጻፉት ደብዳቤ ከአፍሪካ ባለፉት 9 አመታት ተዘርፎ በውጭ ባንኮች የተቀመጠው 385 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ አህጉሪቱ እንደሚለስ ጠይቀዋል። ኮፊ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን ዜጎች የኢትዮጵያ ጦር ከሱዳን እንዲወጣ ጠየቁ
ግንቦት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደቡብ ሱዳናውያን ጥያቄ እያቀረቡ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጦር ዜጎቻችን በሰሜን ሱዳኖች ሲገደሉ በቂ መከላከል አላደረገም በማለት ነው። እንደ ፊረንጆች አቆጣጠር ሜይ 4፣ 2013 አብየ ውስጥ የአካባቢ የጎሳ ገዚ የነበረው ሚስተር ኲኦል ዴንግ ኲኦል በመሲርያ ጎሳ አባላት በኢትዬጲያ ሰላም አስከባሪ ፊት መገደሉ ይታወሳል። በወቅቱ በተደረገው የተኩስ ልውውጥም ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተገድለዋል። ግድያው የኢትዬጵያ ሰላም ...
Read More »ከ300 በላይ መኪኖች በጉሙሩክ ተይዘው ለ 2 አመታት ያለስራ መቀመጣቸው ተዘገበ
ግንቦት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲስ አድማስ እንደዘገበው አስጐብኚ ድርጅቶች፣ የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎች አቤቱታችንን ለመስማትም ሆነ እኛን ለማነጋገር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እንግልት ደርሶብናል ሲሉ ባካሄዱት ስብሰባ ገልጸዋል። በመቶ የሚቆጠሩ ድርጅቶች በአባልነት የያዘው የአስጐብኚዎች ማህበር ትናንት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ፣ የፀረ ሙስና ኮሚሽን እንቅስቃሴን እንደሚደግፍ በመግለፅ፣ የኛ አቤቱታና መረጃ ለኮሚሽኑ ጠቃሚ ግብአት ይሆናል ብሏል፡፡ የማህበሩ አባላት የሆኑ አስጐብኚ ድርጅቶች ከባለስልጣኑ ...
Read More »