.የኢሳት አማርኛ ዜና

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና ቀጥሏል አለ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለሰብአዊ መብቶች መከበር በመሟገት አለማቀፍ እውቅና ያለው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ባደረገው የዚህ አመት ሪፖርት መንግስት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን፣ የነጻውን ሚዲያ ፣ የፖለቲካ ድርጅቶችንና የሲቪክ ማህበራት እንቅስቃሴዎችን መግታቱን ገልጿል። “ሰላማዊ ተቃውሞ ማድረግ ተከልክሏል፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰዎችን ማሰር ፣ ማሰቃየት እና በእስር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃዎችን መፈጸም ቀጥሏል” ያለው አምነስቲ “ዜጎችን በሀይል ...

Read More »

የፌደራል መንግስት የባህርዳር ጊዮን ሆቴል በአስቸኳይ እንዲመለስ ትእዛዝ መስጠቱ ታወቀ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለኢሳት እንደገለጹት የፌደራሉ መንግስት ለአማራ ክልል ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ባስተላለፈው ተእዛዝ ፣ የሆቴሉ ኪራይ ተስልቶ አስፈላጊው እርክክብ እንዲደረግ አዟል። የክልሉ የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲም ለባለሀብቶቹ በጻፈው ደብዳቤ ሆቴሉን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓም ፣ አስፈላጊውን ኪራይ ከፍለው እንዲያስረክቡ ማዘዙ ታውቋል። ባለሀብቶቹ ለወደፊቱ የመረጡት ቦታ ላይ መሬት እንደሚሰጣቸው ቃል ...

Read More »

የመንግስት ባለስልጣናት በበጎ ነገር ምሳሌ የሚሆነን መሪ አጥተናል አሉ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዛሬ በባህርዳር ከተማ በኩሪፍቱ መናፈሻ በከፍተኛ ጥበቃ በተካሄደው የፌደራል እና የክልሎች የሰቪል ሰርቪስ የቢሮ አመራሮች ግምገማ  ተሰብሳቢዎቹ ” በበጎ የምናነሳው ምሳሌ የሚሆን መሪ አጥተናል ፣ ኢህአዴግ እና  ሲቪል ሰርቪሱ ሆድና ጀርባ ሆነዋል በማለት” ተናግረዋል። በመንግስት የሚወጡ መመሪያዎች ያለሰራተኛው ፈቃድ ተግባራዊ እንደሚሆኑ የገለጹት ተሰብሳቢዎች፣ሲቪል ሰርቪሲ የፓርቲ አገልጋይ በመሆኑ ትክክለኛ አገልግሎት መስጠት አልተቻለም በማለት ...

Read More »

መንግስት የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ በየወረዳው ፖሊስ ጣቢያ አጎረ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአፍሪካ ህብረት 50ኛ አመት ክብረ በአል ጋር በተያያዘ የመንግስትን ምስል ያበላሻሉ የተባሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች በፌደራልና በአዲስ አበባ ፖሊሶች እየተያዙ በየጣቢያው እንዲታጎሩ ተደርገዋል። ትናንት ፖሊሶች ሲቪል በመልበስ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ያፈሱ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በልመና የሚተዳደሩትን  አፍሰዋል። መንግስት አለማቀፍ ስብሰባዎች ሲኖሩ ወይም የኢህአዴግ በአላት ሲከበሩ የመንግስትን መልካም ገጽታ ያበላሻሉ የሚባሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች እየታፈሱ በፖሊስ ...

Read More »

በገላሺ ከተማ የኢትዮጵያ ወታደሮች 10 ሰዎችን መግደላቸውን ኦብነግ አስታወቀ

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ( ኦብነግ) ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ትናንት ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከልዩ ሚሊሺያ ጋር በመተባበር በወሰደው እርምጃ አቶ ማካሊ ሙስጠፋ ሀሰን፣ አቶ ሻፊ አው ካሊፍ፣ አቶ አብዱላሂ አብዲ፣ አቶ ሻኩል አብዲ፣ አቶ  ፋራህ ሙሀመድ፣ አቶ አብዲሀይ ሼክ አህመድኑር እና አቶ አብድራሺ ሻፊቺች የተባሉትን ...

Read More »

በጎንደር የሁለት ቀበሌ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀበሌ 6 እና  7 ወጣቶች ዛሬ ግንቦት14፣ 2005 ዓም ባደረጉት ሰልፍ የመብራት፣ የውሀ፣ የስራ አጥነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አደራጅና የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሀ ወጣቶቹ ብሶታቸውን ለመሳማት ለሰልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል። በሰልፉ መጨረሻ ላይ አንዳንድ ወጣቶች በፖሊሶች ሲዋከቡ መታየታቸውን በስፍራው የተገኘው ...

Read More »

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ታሰረ

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ግንቦት14፣ 2005  ጧት ላይ በደህንነቶች ተይዞ መወሰዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ሀብታሙ አያሌው ለኢሳት ገልጿል። ወጣት ብርሀኑ ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መታሰሩን ወጣት ሀብታሙ ገልጿል። ወጣት ሀብታሙ ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ እስረኛውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ...

Read More »

ሰሞኑን በደሴ ከተማ ሩቂያ እየተባለ በሚጠራው አዳራሽ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስሜቱን በድፍረት ሲገልጽ ዋለ

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ስብሰባው ከማንኛውም የድምጽና የምስል ቀረጻ ነጻ እንዲሆን ቢደረግም ኢሳት በደሴ ከተማ ከሚኖሩ ወጣቶች ጋር በመተባበር  ስብሰባውን ለመቅረጽ ችሎአል። በዚህ ስብሰባ ላይ ከመልካም አስተዳዳር እና ከንግድ ጋር በተያያዘ የከተማዋ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ትችቶችን እና ምስጋናዎችን አቅርበዋል። አብዛኞቹ ተናገሪዎች በከተማው ፖሊስ ላይ ከፍተኛ ነቀፌታ አሰምተዋል። መንግስቱ ዘገየ የተባሉ የአማራ ክልል ...

Read More »

በጣና ሀይቅ ላይ የደረሰው የጀልባ መገልበጥ መንስኤ አልታወቀም

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ፋሲለደስ እየተባለ የሚጠራው ጀልባ ከቁንዝላ ወደ ደልጊ 102 ሰዎችን አሳፋሮ ሲጓዝ  በመስጠሙ  አምስት ሰዎች መሞታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያና አንድ የጣና ሀይቅ ትራንሰፖርት ሀላፊ ገልጸው፣ የአደጋው መንሰኤም በመጣራት ላይ ነው ብለዋል። አደጋው የተከሰተው ጀልባው ደልጊ ለመድረስ ከ150 እስከ 170 ሜትር ሲቀረው ነው።  የአካባቢው ህዝብ ተረባርቦ አብዛኞቹን ተሳፋሪዎች ለማውጣት እንደቻለ የጣና ...

Read More »

ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ዙሪያ ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን ወቀሱ

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች  ጋር በተያያዘ ሕገወጥ ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉ 35 ተጠርጣሪዎች ከመንግስታዊ ኃላፊነታቸው መባረራቸውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም አስታወቁ፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር የመ/ቤታቸውን የ2005 የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ለፓርላማው ሲያቀርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ3ሺ 248 ያህል የአማራ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት እንደሆኑ የተደረሰባቸው 35 ተጠርጣሪዎች ከያዙት ኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ ...

Read More »