ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህብረቱ ጥያቄውን ያቀረበው በኮሚሽነሩዋ በዳላሚነ ዙማ አማካኝነት ነው። ሁለቱ አገሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለመፈለግ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር መዘጋጀት አለባቸው በማለት ኮሚሽነሩዋ ተናግረዋል። ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እወስዳለው ማለቷን ተከትሎ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግብጽ ስልጣን የያዙ ሰዎች ” ያበዱ” ካልሆኑ በስተቀር ወደ ጦርነት አያመሩም የሚል መልስ ሰጥተዋል። በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የቃላት ጦርነት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሻሸመኔ ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተፈጸመ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቁጥራቸው 13 የሚጠጋ የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት አቶ በየነ ሞርሲ፣ ሳምሶን ራቦ፣ አበራ መቲቦ እንዲሁም በማዘጋጃ ቤት ውስጥ ሀላፊ የሆነ አቶ ዳዊት ደጮ የተባሉት ግለሰቦች ” አብዲ ሁንዳ” እና ሀምሌት የተባሉ የቤትና የንግድ ማህበሮችን መስርተናል በሚል ከግለሰቦቹ በነፍስ ወከፍ እስከ ከ10 ሺ ብር በድምሩ ከ194 ሺ ብር ያላነሰ ገንዘብ ተቀብለዋል። ግለሰቦቹ የኦሮሚያ ...
Read More »ኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የወጣን ጅብ ለማስወጣት 5 ጥይቶች ሲተኮሱ አንድ ወጣት ቆሰለ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው ሰሞኑን ከምሽቱ አራት ሰዓት በአንድ የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት ሶስተኛ ፎቅ ላይ የተኛውን ጅብ ለማስወጣት አምስት ጥይቶች ተተኩሰው ጅቡ የተገደለ ሲሆን፤ በአካባቢው የነበረ አንድ ወጣት ሆዱ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል። ጅቡ በህንጻው ላይ እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ፎቁ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሳይወጡ መቆየታቸውን ፣ እስከ ትናንት ጠዋት አንዳንድ ወላጆች በዱላ እና ...
Read More »ኢትዮጵያና ግብጽ የቃላት ጦርነት ጀምረዋል
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሁለቱ አገሮች መካከል መተነኳኮሱ እየባሰ የመጣው ዘንድሮ ግንቦት 20 ቀን የተከበረውን የገዥውን ፓርቲ በኣል ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ፦” የ አባይ ወንዝን የተፋሰስ አቅጣጫ አስቀየስኩ” ብላ ማወጇን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ በተለይ የግብጽ መንግስት -ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ እስከ ወታደራዊ ጥቃት ድረስ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የመከሩበት ስብሰባ በይፋ ታየ፤ ይሁንና የግብጽ መንግስት-ከተቃዋሚዎቹ ጋር ...
Read More »የኢትዮጵያ ፓርላማ ለመከላከያ፣ ፍትህና ደህንነት ተቋማት ከ10 በሊዮን ብር በላይ መደበ
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሶፊያን አህመድ ለፓርላማው ባቀረቡት የ2006 በጀት መግለጫ ላይ በቀጣዩ ዓመት አገሪቱ 154 ቢሊየን 903 ሚሊየን 290 ሺህ 899 ብር ረቂቅ በጀት በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁን አመልክተዋል። ይህ በጀት ከአምና ጋር ሲነጻጸር የ12 ነጥብ 3 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ በረቂቅ በጀቱ ድልድል ከተደረገላቸው ተቋማት መካከል መከላከያ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር፣ ...
Read More »በመተማ የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች በመሬት ዙሪያ ከመንግስት ጋር እየተወዛገቡ ነው
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመተማ ዮሐንስ እና ኮኪት ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች መሬታችን አድሎአዊ በሆነ መልኩ ለባለሀብቶች እየተሰጠብን ነው በማለት ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ነው። የነዋሪዎቹ ተወካይ እንደተናገሩት አቤቱታቸውን ለም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም ለአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ቢያቀርቡም ፣ ባለስልጣኖቹ ” አልሰማንም ” የሚል መልስ ከመስጠት በስተቀር ፣ ለችግራቸው ፈጣን መልስ አልሰጡም። መንግስት መሬት የአለአግባብ እየተረፈ ...
Read More »በአፋር ፌደራል ፖሊሶች ከህዝቡ ጋር ሲታኮሱ ዋሉ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት የ20 አመቱ ወጣት የሆነው ሙሀመድ ካይብ የፌደራል ፖሊስ አባላት በቅርበት ባሉበት በኢሳዎች መገደሉን ተከትሎ፣ አፋሮች ገዋኔ ወለጌሊ እየተባለ በሚጠራ ስፍራ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ዛሬ ሲታኮሱ ውለዋል። ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ተኩሱ አለመቆሙን ለማወቅ ተችሎአል። ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ የከፈቱት ፣ ፖሊሶቹ ሆን ብለው ሁለቱን ብሄረሰቦች ለማጋጨት እየጣሩ ነው በሚል ...
Read More »በማዳበሪያ እዳ ለስደትና ለእንግልት ተዳርገናል ሲሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሺንዲ ወንበርማ ወረዳ የማንችለውን ውዝፍ የማዳበሪያ እዳ እንድንከፍል በመገደዳችን ለስደትና እንግልት ተዳርገናል ሲሉ በርበሬ አምራች አርሶ አደሮች ተናግረዋል ፡፡ በመንግስት በታጠቁ ሀይሎች ሀብት ንብረታችን ተዘርፎና የቤታችን ቆርቆሮው ተገፎ ተወስዶብናል ያሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አርሶ አደሮች፣ ዛሬ ቤት ንብረታችንን ጥለን ቤተሠባችንን በትነን ለስደት ተዳርገናል ብለዋል። በአየር ንብረት መዛባት ችግር በደረሰብን አደጋ ምርታችን በከፍተኛ ደረጃ ...
Read More »ፓዌ ወደ ልዩ ወረዳነት እንድትመለስ የጠየቁ ነዋሪዎች እንግልት እንደደረሰባቸው አስታወቁ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን የሚኖሩ ነዋሪዎች ፓዌ በፊት ትጠራበት ወደነበረው ልዩ ወረዳነት እንድትመለስ በመጠየቃቸው ከፍተኛ እንግልት እና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ፡፡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በወረዳዋ የሚኖሩ ወጣቶች በጋራ እንደገለፁልን ከ1977 ዓ.ም በፊት ከሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በሠፈራ መጥተው ፓዌ ወረዳ ላይ የቆዩ ሲሆን በ1983 ዓ.ም በአካባቢው ከሚኖሩ ጉምዝ፣ ሺናሻ፣ ርታ፣ ማኦ እና ኮሞ ...
Read More »በሙስና የታሰሩት የጉምሩክ አቃቤ ሕግ፣ ቀብረውት የነበረ ከ1ሚልዪን በላይ ብር መገኘቱ ተነገረ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙስና ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት የሚገኙት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ህግ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ማርክነህ አለማየሁ ቀብረውታል የተባለ ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ መገኘቱ ታውቋል። ጉዳዪን የሚከታተለው የምርመራ ቡድን እንዳስታወቀው ከሆነ፣- አቶ ማርክነህ አለማየሁ በወንድማቸው አማካኝነት ለመሰወር አቅደው የቀበሩት አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሺ ብር የተገኘው ወላይታ ሶዶ፣ ወራንዛላሸ በተሰኘች ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ...
Read More »