.የኢሳት አማርኛ ዜና

በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀው መከላከያ ሂሳቡ እንዳይመረመር ታዘዘ

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ባቀረበው ሪፖርት የመከላከያና የደህንነት ተቋማት የፋይናንስ አያያዝ ከፍተኛ ችግር እንዳለበት ማመልከቱን ተከትሎ በየመ/ቤቶቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት በቀጥታ እነዚህን ተቋማት በተለየ ሁኔታ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ እየተረቀቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ለፓርላማው ባቀረቡት የ2004 ዓ.ም ...

Read More »

የግል ባንኮች ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል አሉ

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት የቁጠባ ፕሮግራም መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲከናወን መደረጉ በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነና በአጭር ጊዜ የግል ባንክ ዘርፉን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል አዲስ አድማስ ዘገበ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የግል ባንክ ባለሙያ፤ እሣቸው በሚሠሩበት ባንክ ደንበኛ የነበሩ ግለሠቦች በቤቶች የቁጠባ ፕሮግራም ተሣታፊ ...

Read More »

በክልል ከተሞች ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ሰኔ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዳማ በአቡበክር መስጊድ በተካሄደው ተቃውሞ ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ” መንግስት ድምጻችንን ይስማ፣ በሀሰት ክስ አንገዛም፣ አሸባሪዎች አይደለንም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል። በአሳሳ ከተማም እንዲሁ በአል ከራም መስጂድ ተቃውሞ መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል። በወልድያም እንዲሁ ሙስሊሙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰምተዋል። በሁለቱም ቦታዎች የተካሄዱት ተቃውሞዎች በሰላም ተጠናቀዋል። መንግስት የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ከእስር በመፍታት ለሙስሊሞች ጥያቄ መፍትሄ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ምዝገባ የተመዘገበው ህዝቡ ቁጥር መንግስት በቅርቡ ካወጣው አዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር ጋር የማይጣጣም ነው ሲሉ አንድ ባለሙያ ገለጹ

ሰኔ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን ሰሞኑን የአዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር 2 ሚሊዮን 900 ሺ መሆኑን ቢገልጽም፣ በ10 – 90 እና በ20 – 80 እየተባለ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተመዘገበው ህዝብ ቁጥር ኤጀንሲው ያቀረበው አሀዝ  ትክክል አለመሆኑን የሚያሳይ ነው በማለት አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ ቀድሞ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ...

Read More »

ሼህ ዳሂር አዌይስ እጃቸውን እንዲሰጡ ለማግባባት እየተሞከረ ነው

ሰኔ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአልሸባብ መሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ሼህ ዳሂር አዌይስ ከሌሎች መሪዎች ጋር ልዩነት መፍጠራቸውን ተከትሎ ጋልምዱግ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ ማቅናታቸው ታውቋል። የአካባቢው የጎሳ መሪዎችም ሼህ ዳሂርን በስልጣን ላይ ላለው የሶማሊያ መንግስት እጃቸውን እንዲሰጡ ለማግባባት እየሞከሩ ሲሆን፣ ሼሁ ግን እጃቸውን ለመስጠት እስካሁን ፈቃደኛ አልሆኑም። በስልጣን ላይ ላለው መንግስት እውቅና እንደማይሰጡም ገልጸዋል። የተባበሩት ...

Read More »

በግብጽ የፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በየፊናቸው ወደ ካይሮ ጎዳናዎች መውጣታቸውን ቢቢሲ ዘገበ

ሰኔ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ  እንዳለው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ  የፕሬዚዳንት ሙርሲ ደጋፊዎች ፤ የፕሬዚዳንቱ ሹመት 1ኛ  ዓመት ከሚከበርበት ከሁለት ቀናት በፊት   በናስር ቀጠና በሚገኘው በዋናው መስጊድ መሰባሰብ ጀምረዋል። በ አንፃሩ የፕሬዚዳንቱ ተቃዋሚዎች  በመጪው እሁድ ከፍ ያለ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በተለያዩ የካይሮ ጎዳናዎች መሰባሰብ መጀመራቸውን  የዜና አውታሩ አመልክቷል። በግብጽ ሁለተኛ ከተማ በአሌክሳንደሪያ. በተቃውሞ ሰልፈኞቹና በሙስሊሞች መካከል ...

Read More »

በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አዘጋጅነት ትናንት ቼክ ሪፐብሊክ ኦስትራቫ ውስጥ በተካሄደ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አኩሪ ድል ተቀዳጁ

ሰኔ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 30 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ ከ 67 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ቀድማ በመግባት ስታሸንፍ፤ ኬኒያዊቷ ግላዴስ ቼሬኖን 30 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ ከ23 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመጨረስ 2ኛ፣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ ሶስተኛ፣ በመሆን ማጠናቀቃቸው ታውቋል። በዚሁ ውድድር ላይ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ  ከአምስት ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ ሰኔ 30 በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱን አስታወቀ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት የህዝባዊ እንቅስቃሴ የትግል ስልቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍም በጎንደር ከተማ ሰኔ 30/10/2005 እንደሚያደርግ አስታውቋል -፡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ” በጎንደር እየተፈጸመ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ሰዎችን በአደራ ማሰር፣ ለሱዳን ከህዝቡ እውቅና እና ፈቃድ ውጪ መሬት መሰጠቱን፣ በነጋዴዎች ላይ የሚፈጸመውን ኢ-ፍትሃዊ አሰራር፣ ...

Read More »

በገዋኔ በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተጎዱ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሰኔ 20፣ 2001 ዓም አንድ የአፋር ወጣት በኢሳዎች መገደሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ሬሳውን በመያዝ ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ ፖሊሶች ወደ ሚገኙበት ካፕም ሲያመሩ የፌደራል ፖሊሶች ” ዘወር በሉ” በማለት ሰልፈኞችን ሲጠይቁ፣ ሰልፈኞችም ” ጥያቄያችን  ሳይመለስ አንሄድም” በማለታቸው  ተኩስ እንደተከፈተባቸው እና ሁለት ሰዎች እንደቆሰለባቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የሞቱ ሰዎች እንዳሉ የተጠየቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ፖሊሶች ...

Read More »

ምርጫ ቦርድ “ቀኝ እጆቼ” ለሆኑት የምርጫ አስፈጻሚዎች የምከፍለው ገንዘብ አጣሁ ሲል አቤቱታ አቀረበ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበጀት ችግር ምክንያት ለምርጫ አስፈጻሚዎች እና የህዝብ ታዛቢዎች የድጎማ ገንዘብ ባለመክፈሉ ምክንያት በቀጣዩ ምርጫ ላይ ሥጋት እንዳጠላበት ለፓርላማው ይፋ አደርጓል፡፡ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና  ለፓርላማው ባቀረቡት የ2005 አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በ2005 ዓ.ም የአካባቢ፣ የአዲስአበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምርጫ ማስፈጸሚያ በድምሩ ከ184 ሚሊየን ብር ...

Read More »