.የኢሳት አማርኛ ዜና

በቁጫ ወረዳ በርካታ ሰዎች ታሰሩ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ከ50 በላይ ሰዎችን ማሰሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል 6ቱ ሴቶች ናቸው። ባለፈው ሐሙስ የኢህአዴግ ካድሬዎችና ፖሊሶች መደብደባቸውን የሚያመለክት ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው በብዛት በማቅናት ሰዎችን በማሰር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ መረጃዎችን በማቀባባል የአካባቢውን ህዝብ ለአመጽ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ የተባሉ 106 ባጃጆችና ...

Read More »

በአማራ ክልል የመልካም አስተዳደር ችግር ስር የሰደደ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት እየተባለ የሚጠራው መስሪያ ቤት በክልሉ ባሉ የአስተዳደር ቢሮዎች ባካሄደው ቅኝት የመልካም  አስተደዳር ችግር በክልሉ ተባብሶ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ በተለይም በፍትህ ፤ በፖሊስ ፤ በማረሚያ ቤቶች ፤ በመሬት ፤ኢንቨስትመንት፤ መብራት እና ውሃ ደግሞ የችግሩ መለያ ቦታዎች መሆናቸውን ለክልሉ ካቢኔ የቀረበው ሪፖርት የቅሬታ ምንጭ መሆናቸውን ያወሳል፡፡ በክልሉም ከጊዜ ወደ ጊዜ የቅሬታዎች ቁጥር እየጨመረ ...

Read More »

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል። በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል። ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ ...

Read More »

አልከሄር የኢትዮጵያን ጦር ክፉኛ ወቀሱ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን አብየ ግዛት የሚገኘው የጥምር ኮሚቴ ስብሳቢዎች አንዱ የሆኑት አልከሄር አል ፋቲም አማጺ የሆነውን የሱዳን አብዮታዊ ግንባር በአካባቢው መኖሩ እያወቀ በስፍራው የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር በዝምታ በማለፉ ክፉኛ ወቅስዋል:: አልከሄር አል ፋቲም ሰሜን ሱዳንን ወክለው የሚገኙ ሲሆን እንደሳቸው ገለጻ አማጺው ሃይል በምስራቅ አብየ ሰፍሮ እንደሚገኝ ገልጸዉ የኢትዮጵያን ጦር ዝምታ ግን የሰላሙን ሂደት እንዳያበላሸው አሳስበዋል:: ቅርብ ...

Read More »

በተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞች ታፍሰው እየታሰሩ ነው

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት በ ኢድ አል ፈጥር እለት የፌደራል ፖሊሶች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎ ሌሊቱንና ዛሬም በርካታ ሙስሊሞች ከቤታቸው እየተወሰዱ ታስረዋል። በአሁኑ ጊዜ በትክክል የታሰረውን ህዝብ ቁጥር ለማወቅ ባይቻልም   በሺዎች እንደሚቆጠር ይገልጻሉ። በዛሬው እለትም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር ተፈተዋል።  ድምጻችን ይሰማ እንደገለጸው ደግሞ በትናንትናው ተቃውሞ አንዲት ...

Read More »

የጦር መሳሪያ የጫነ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አውሮፕላን ወድቆ ተከሰከሰ

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጦር አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ላይ ነው። ሶቭየት ሰራሹ አንቶኖቭ አውሮፕላን መሬት ላይ እንደወደቀ በእሳት ጋይቶ 4 ቱን አብራሪዎች ገድሎአዋቸል። አውሮፕላኑ በአየር ላይ እያለ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከሳምንት በፊት አንድ የመከላከያ ንብረት የሆነ ሄሊኮፕተር ወድቆ መከስከሱ ይታወቃል።

Read More »

በቁጫ ወረዳ ውጥረቱ እንደገና ተባብሶአል

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በወረዳው የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በትናንትናው እለት አልፋ እየተባለ ወደ ሚጠራው ቀበሌ ያመሩ የፖሊስ አባላትና ካድሬዎች ምሽቱን መደብደባቸውን የተመለከተ መረጃ የደረሰው ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ከፍተኛ ቁጥር አላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል። በዛሬው እለት በዙሁ ቀበሌ ያለው ውጥረት የጨመረ ሲሆን፣ በካድሬዎቹ እና በፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም ተይዘው ታስረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ...

Read More »

ወደ ኮሪያ ለስልጠና የተላኩት አብዛኞቹ ወጣቶች ጥገኝነት ጠየቁ

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኮሪያ ዘማች ቤተሰቦች ተውጣጥው ወደ ደቡብ ኮሪያ ለትምህርት ከተላኩት 59 ኢትዮጵያውያን መካከል 38ቱ ጥገኝነት ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ለ8 ወራት የተሰጣቸውን ስልጠና ሊያጠናቅቁ የቀናት እድሜ ሲቀራቸው ነው ጥገኝነቱን የጠየቁት። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ መበላሸት፣ ወጣቱ በአገሩ የሚሰራበት ሁኔታ ሊመቻች ባለመቻሉ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደተገደዱ ወጣት ሲሳይ ወልደገብረኤል ለኢሳት ገልጿል።

Read More »

በአዲስ አበባና በመላው አገሪቱ ሙስሊሞች 1434ኛውን የኢድ አልፈጥርን በአል ለማክበር በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ሙስሊሞች በፌደራል ፖሊሶች በተወሰደበባቸው እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶዋል።

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢ ከጥቁር አንበሳ እንደገለጸው በዛሬው ድብደባ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ተደብድበዋል፣  እየታፈሱም ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች ተግዘዋል። ኢሳት በራሱ ዘጋቢዎች ባያረጋገጥም፣ ያነጋራቸው ሰዎች አንድ ነፍሰጡርና አንድ ታዳጊ ልጅ መሞታቸውን ጠቁመዋል።  

Read More »

በደሴ የተካሄደው የኢድ ተቃውሞ ላይ ፖሊስ ሕዝቡ ላይ በቀጥታ ጥይት ሲተኩስ አርፍዷል፣ከፍተኛ ድብደባም ፈጽሟል።

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢው በከፍተኛ አስለቃሽ ጭስ ታፍኖ አርፍዷዋል፡፡በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።  የደሴ ህዝብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። እስካሁን የሞቱትን እና የቆሰሉትን ለማወቅ በፊድራል ፖሊስ ሐይሎች ሆስፒታሎች በመከበቡ ለማወቅ አልተቻለም። በደሴ የሚኖሩ ሙስሊሞች 2 ሰዎች መገደላቸውን ለኢሳት ተናግረዋል በአማራ ክልል በወረባቡ ከተማ ፤ እና መርሳ አካባቢ ክፍተኛ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በሙስሊሙ እና በፖሊሶች መካከል በስምንት ሰዎች ላይ ...

Read More »