የጦር መሳሪያ የጫነ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አውሮፕላን ወድቆ ተከሰከሰ

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጦር አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ላይ ነው።

ሶቭየት ሰራሹ አንቶኖቭ አውሮፕላን መሬት ላይ እንደወደቀ በእሳት ጋይቶ 4 ቱን አብራሪዎች ገድሎአዋቸል።

አውሮፕላኑ በአየር ላይ እያለ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ከሳምንት በፊት አንድ የመከላከያ ንብረት የሆነ ሄሊኮፕተር ወድቆ መከስከሱ ይታወቃል።