በቁጫ ወረዳ ውጥረቱ እንደገና ተባብሶአል

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በወረዳው የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በትናንትናው እለት አልፋ እየተባለ ወደ ሚጠራው ቀበሌ ያመሩ የፖሊስ አባላትና ካድሬዎች ምሽቱን መደብደባቸውን የተመለከተ መረጃ የደረሰው ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ከፍተኛ ቁጥር አላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል።

በዛሬው እለት በዙሁ ቀበሌ ያለው ውጥረት የጨመረ ሲሆን፣ በካድሬዎቹ እና በፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም ተይዘው ታስረዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በህዝቡና በፖሊሶች መካከል ግጭት ይፈጠራል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ።

ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ የተነሳ ግጭት የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ወር የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከታሰሩ 40 ሰዎች መካከል 13ቱ  በፍርድ ቤት እንዲለቀቁ ቢወሰንም እስካሁን አለመፈታታቸው ታውቋል።