በአዲስ አበባና በመላው አገሪቱ ሙስሊሞች 1434ኛውን የኢድ አልፈጥርን በአል ለማክበር በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ሙስሊሞች በፌደራል ፖሊሶች በተወሰደበባቸው እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶዋል።

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢ ከጥቁር አንበሳ እንደገለጸው በዛሬው ድብደባ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ተደብድበዋል፣  እየታፈሱም ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች ተግዘዋል። ኢሳት በራሱ ዘጋቢዎች ባያረጋገጥም፣ ያነጋራቸው ሰዎች አንድ ነፍሰጡርና አንድ ታዳጊ ልጅ መሞታቸውን ጠቁመዋል።