በደሴ የተካሄደው የኢድ ተቃውሞ ላይ ፖሊስ ሕዝቡ ላይ በቀጥታ ጥይት ሲተኩስ አርፍዷል፣ከፍተኛ ድብደባም ፈጽሟል።

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢው በከፍተኛ አስለቃሽ ጭስ ታፍኖ አርፍዷዋል፡፡በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።  የደሴ ህዝብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። እስካሁን የሞቱትን እና የቆሰሉትን ለማወቅ በፊድራል ፖሊስ ሐይሎች ሆስፒታሎች በመከበቡ ለማወቅ አልተቻለም።

በደሴ የሚኖሩ ሙስሊሞች 2 ሰዎች መገደላቸውን ለኢሳት ተናግረዋል

በአማራ ክልል በወረባቡ ከተማ ፤ እና መርሳ አካባቢ ክፍተኛ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በሙስሊሙ እና በፖሊሶች መካከል በስምንት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።  ዘጠኝ ምእመናን ታስረዋል፡፡  ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ በከተማዋ ላይ ተክቢራ ማሰማት ከልክለዋል፡፡