በቁጫ ወረዳ በርካታ ሰዎች ታሰሩ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ከ50 በላይ ሰዎችን ማሰሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል 6ቱ ሴቶች ናቸው።

ባለፈው ሐሙስ የኢህአዴግ ካድሬዎችና ፖሊሶች መደብደባቸውን የሚያመለክት ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው በብዛት በማቅናት ሰዎችን በማሰር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ መረጃዎችን በማቀባባል የአካባቢውን ህዝብ ለአመጽ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ የተባሉ 106 ባጃጆችና ሞተር ሳይክሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በወረዳው ውስጥ ወደሚገኙ 27 ቀበሌዎች ምንም አይነት ሰዎች ዝውውር እንደሌለም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወረዳው የታየውን ውጥረት ተከትሎ በብዙ መቶዎች የሚቀጠሩ የወረዳዋ ነዋሪዎች ታስረዋል።