ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በዳኖ ወረዳ አጂላ ዳሌ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ለኢሳት እንደገለጹት ከ19 ዓመታት በላይ ከኖሩበት ቀየ በተለያዩ ሰበቦች ሀብትና ንብረታቸውን ተቀምተው ለቀው እንዲወጡ በመደረጋቸው ቤት አልባ ሆነው ለችግር ተዳርገዋል። “መንግስት በአካባቢው እንድንኖር ፈቃድ ሰጥቶን የሚፈለግብንን ግብር እየከፈልን አካባቢውን ስናለማ ነበር” የሚሉት አርሶ አደሮች፣ ሀብትና ንብረት ካፈራን በሁዋላ ” ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የዞንዘጠኝ ጦማርያን ተጨማሪጊዜተጠየቀባቸው።
ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እሁድ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የ 28 ቀናት ቀጠሮ የተጠየቀባቸው የዞን 9 ጦማርያን ማህሌትፋንታሁን፣አቤልዋበላናበፍቃዱኃይሉ ናቸው። ጦማርያኑ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ሲጠይቅባቸው በመሀል ዳኛዋ ውድቅ ተደርጎ የ15 ቀናት ቀጠሮ መሰጠቱ አይዘነጋም። ይሁንና ችሎቱ ከትናንት በስቲያ እሁድ በአራዳ ምድብ ችሎት ሢሰየም ውሳኔውን ያሳለፉት ዳኛ ከቦታው እንዲነሱ ...
Read More »ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንደቻለች ተደርጎ መገለጹ አነጋጋሪ ሆኗል
ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንቦት 20 በዓል በተከበረበት ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በምግብ ሰብል እህል ምርት ራሱዋን መቻሉዋን ተናግረዋል። ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የዋና ዋና ምግብ ሰብሎች ምርት በ2002 ከነበረበት 202 ሚሊየን ኩንታል፣በ2005 ዓ.ምወደ 251 ሚሊየንኩንታልቢያድግምከሚጠበቀውአንጻርእድገቱዝቅተኛመሆኑንይጠቅሳል ፡፡ይህምጠ/ሚኒስትሩ በምግብ ራሳችንችለናልከሚልገለጻቸውጋርየሚጋጭ ሲሆን ኢህአዴግ በባህርዳር ከተማ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የሰብል ልማት በእድገት ...
Read More »የአሜሪካ ኢምባሲ ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ
ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢምባሲው ማስጠንቀቂያውን ያወጣው አልሸባብ በኢትዮጵያ እና በምእራባዊያን ተቋማት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ፍላጎቱና ችሎታው እንዳለው ተጨባጭ መረጃ እንደደረሰው ከጠቀሰ በሁዋላ ነው። በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ የሰዎች ምልልስ ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቀሰው ኢምባሲው፣ ጥቃቱ የሚፈጸምበት ቦታና ሰአት በትክክል ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ዜጎች የምእራባዊያን ዜጎች በሚሰበሰቡበት በሆቴሎች፣ በምግብ ቤቶች፣ በመጠጥ ቤቶችና በገበያ አዳራሾችና በአምልኮ ቦታዎች ላይ ሁሉ የግል ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኑር መስኪድ ደማቅ ተቃውሞ አደረጉ
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሙስሊም የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በፍትህ እጦት በእስር ቤት መሰቃየት መቀጠላቸውን በመቃወም በአዲስ አበባ በኑር መስጊድ በተደረገው ተቃውሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ መገኘቱን ዘጋቢያችን ገልጻለች። ድምጻችን ይሰማ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ የተቃውሞው ዋና አላማ የሙስሊሙን ህዝብ ጥያቄ አንግበው በመያዛቸው በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙት መሪዎች ድጋፍ ለመግለጽ ነው መሆኑን ጠቅሷል። በዘገየ ፍትህና በችሎት ...
Read More »ታፍኖ የተወሰደው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ማእከላዊ መታሰሩ ታወቀ
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት ከትምህርት ገበታው ታፍኖ ተወስዶ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ አመት ተማሪ እና የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው መልካሙ አምባቸው በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩ ታወቀ። በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራአስፈጻሚ አባል የሆነው ወጣት መልካሙ አምባቸው ...
Read More »ዘመነ ካሴ በቀረረበበት የሽብርተኝነት ክስ መልስ ሰጠ
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአመራር አባልና የቀድሞው የአማራ ክልል ወጣቶች ሊቀመንበር ዘመነ ካሴን ጨምሮ 10 ወጣቶች በተከሰሱበት የሽብረተኝነት ወንጀል ጥፋተኞች መባላቸውን ተከትሎ፣ ክሱን በሌለበት የሚሰማው አንደኛው ተከሳሽ ዘመነ ካሴ የቀረበበትን ክስ አጣጥሎታል። አንደኛ ተከሳሽ ዘመነ ካሴ “ኤርትራ ሄዶ የጦር ስልጠና ወስዶ መምጣቱን ፣ መንግስት አሸባሪ ብሎ ከሰየመው የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራሮች በተለይም ከጄኔራል ተፈራ ...
Read More »ካርል ሃይንዝ ቦም አረፉ
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦስትሪያዊው የፊል ተዋናይ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የ86 ዓመቱ ቦም ያረፉት በሚኖሩበት ሳልዝበርግ ከተማ ውስጥ ነው። ሰዎች ለሰዎች የተባለ የእርዳታ ድርጅት አቋቋመው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሰብአዊ እርዳታዎችን ሲያደርጉ የቆዩት ቦም፣ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅ ናቸው። ሰዎች ለሰዎች የተባለውድርጅት በአሁኑ ጊዜ በትዳር ጓደኛቸው ወ/ሮ አልማዝ ቦም እንደሚመራ ይታወቃል።
Read More »በሊቢያ በርካታ አስከሬኖች ተገኙ
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት በርካታ ስደተኞችን ጭና ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ስታምራ በሰጠመችው ጀልባ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ አስከሬን መገኘቱን የሊቢያ የአደጋ መከላከ ሰራተኞችን በመጥቀስ ዓለማቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። የሊቢያ አደጋ መከላከል ሰራተኞች በጀልባዋ ከ150 በላይ ስደተኞች ተሳፍረው እንደነበር ለ አል ጀዚራ የገለጹ ሲሆን፤ እስካሁን የተገኘው ግን የ 20 ዎቹ አስከሬንብቻ ነው። አበዛኞቹ ተሳፋሪዎች ...
Read More »የሃይማኖት ተቋማት ለብአዴን ጽህፈት ቤት ማሰሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ታዘዙ
ግንቦት ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀወት ወረዳ በሸዋ ሮቢት ከተማ ለሚገነባው የብአዴን ጽህፈት ቤት ማሰሪያ በወረዳዋ የሚገኙ ቤተክርስቲያኖች በነፍስ ወከፍ 1 ሺ 500 ብር እንዲከፍሉ በመታዘዛቸው፣ አስተዳዳሪዎቹ ገቢ ማድረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። የሃይማኖት ተቋማት ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ እንደሆኑ ህግ ቢደነግግም፣ በተግባር የምናየው የዚህን ተቃራኒ ነው ያሉት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አስተዳዳሪዎች፣ ገንዘቡን ለጽህፈት ቤቱ ወስደው ያስረከቡት ከመንግስት የሚመጣውን በቀል ...
Read More »