ካርል ሃይንዝ ቦም አረፉ

ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦስትሪያዊው የፊል ተዋናይ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የ86 ዓመቱ ቦም ያረፉት በሚኖሩበት ሳልዝበርግ ከተማ ውስጥ ነው።

ሰዎች ለሰዎች የተባለ የእርዳታ ድርጅት አቋቋመው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሰብአዊ እርዳታዎችን ሲያደርጉ የቆዩት ቦም፣ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅ ናቸው።

ሰዎች ለሰዎች የተባለውድርጅት በአሁኑ ጊዜ በትዳር ጓደኛቸው ወ/ሮ አልማዝ ቦም እንደሚመራ ይታወቃል።