በሊቢያ በርካታ አስከሬኖች ተገኙ

ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት በርካታ ስደተኞችን ጭና ከሊቢያ  ወደ ጣሊያን ስታምራ በሰጠመችው ጀልባ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች  ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ አስከሬን  መገኘቱን የሊቢያ የአደጋ  መከላከ ሰራተኞችን በመጥቀስ ዓለማቀፍ  ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።

የሊቢያ አደጋ መከላከል ሰራተኞች በጀልባዋ ከ150 በላይ ስደተኞች ተሳፍረው እንደነበር ለ አል ጀዚራ የገለጹ ሲሆን፤ እስካሁን  የተገኘው ግን የ 20 ዎቹ አስከሬንብቻ  ነው።

አበዛኞቹ ተሳፋሪዎች ከአፍሪካ የመጡ እና በሊቢያ በኩል ወደ ጣሊያን ለመሻገር የሞከሩ ስደተኞች እንደሆኑ ተመልክቷል።

እስካሁን 20 አሰከሬኖችን ከባህር ውሰጥ ያወጡት የሊቢያ አሰከሬን ፈላጊዎች፤ ቀሪዎቹን ወደ 130 የሚገመቱ ተሳፋሪዎች አስከሬን ለማውጣት እርዳታ ይደረግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

ቢቢሲ ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደዘገበው በዚህ ዓመት  ከመላው ዓለም ወደ አውሮፓ የሚሻገሩ ስደተኞች ቁጥር  በከፍተኛ እና በአስደንጋጭ ደረጃ ጨምሩዋል።

ካላፈው የፈረንጆች ዓመት መግቢያ እስከ አፐሪል ድረስ ባሉት አራት ወራት ብቻ 42 ሺህ ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ መሻገራቸውን ያመለከተው ቢቢሲ፣ከነኚህ መካከል 25 ሺ 650 የሚሆኑት  በሊቢያ ድንበር አድርገው ወደ ጣሊያን የገቡ መሆናቸውን ጠቀሱዋል።

በተለይ በሰሜን አፍሪካና በአረቡ ዓለም የተቀጣጠሉት አብዮቶች ለስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ዋነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተጠቅሱዋል።

በመረሻታላቅ የእርዳታ ጥሪ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ

ዘመን ተሻጋሪ በሆኑት ባህላዊ ቅኝቶቹ እንዲሁም ሃገርኛ ለዛ ካላቸው ትቂት ባህላዊ ዘፋኞች አንዱ እንዲሁም ሃገሩንና ባህሉን አክባሪ የሆነው አርቲስት ዳምጠው አየለ በጠና ታሞ ይገኛል፥፣ ቤተሰቦቹን ከጎኑ ለማድረግ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የኛን የወገኖቹን እርዳታ ይሻል፥፥ የጥበብ ሰው ሃብቱም ንብረቱም ወገኑ ነውና ዛሬ ቁርጥ ቀን ላይ ወንድማችን አርቲስት ዳምጠው አየለን በመለው የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንቆም ዘንድ የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ጥሪውን ያስስተላልፋል፥፥

በኖርዌይ ለምትኖሩ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ቁጥር 1503 43 13420 ሲሆን ከኖርዌይ ውጭ ለምትገኙና መርዳት ለምትልጉ

ምትፈልጉ በሂሳብ ቁጥር፥

Bank : DNB (Den Norske Bank)

BIC/ SWIFT ADDRESS : DNBANOKKXXX

IBAN : NO 0315034313420 OR

(IBAN for use in print : NO 03 1503 4313 420)