.የኢሳት አማርኛ ዜና

በጋዜጣ አዙዋሪዎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩ ታወቀ

  ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የሆነው ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው  ሃሙስ ምሽትላይ  በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ጋዜጣ አዙዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ታግተው አምሽተዋል፡፡የደህንነት ኃይሎች ‹‹ለማዞር የተደራጃችሁበትንና ፈቃድ የተሰጣችሁበትን ወረቀት አምጡ›› በማለት ወደ ጣቢያ ሊወስዱዋቸው እንደ ነበርና አዙዋዎቹም ‹‹መደራጀት አይጠበቅብንም ፣ጣቢያም አንሄድም›› ብለው የደህንነቶቹን ትዕዛዝ መቃወማቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ መንግስትን የሚተቹ ጋዜጦችና መጽሄቶች እንዲያዞሩ እንደማይፈልግና እሱ የሚፈልገውን ...

Read More »

አንድነት በደብደረማርቆስ እና በአዳማ ለሚካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እያካሄደ ነው

ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድርጅቱ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በርካታ በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል፣ ፖስተሮችን መለጠፍና በድምጽ ማጉያ መሳሪያ በመጠቀም ቅስቀሳ ተካሂዷል። የህዝቡ ስሜት አስገራሚ ነው የሚሉት አመራሮች፣ ህዝቡ ወረቀቶችን ያለምንም ችግር እየተቀበለ እንደሚያሰራጭ፣ በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ አመራሮች ገልጸዋል። የአንድነት ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ሰብሳቢ አቶ ዋለ ባየ በእሁዱ ሰልፍ ብዙ ህዝብ ወጥቶ ...

Read More »

መንግስት በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ቦንብ የወረወሩትን መያዙን አስታወቀ

ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸር ሽብር ግብረሃይል ለአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋትና ከ15 በላይ ተማሪዎች መቁሰል ተጠያቂ የሆኑ ተማሪዎችን በተለያዩ ጊዜ አፈላልጎ መያዙን አስታውቋል። አበበ ኡርጌሳ፣ ኑረዲን ሃሰን፣ ኒሞና ጫሌና መገርሳ ወርቁ የተባሉት ተማሪዎች ቦንቦን ካፈነዱ በሁዋላ በተማሪዎቹ ላይ በፌሮና በድንጋይ ድብደባ መፈጸማቸውን ግብረሃይሉ ገልጿል። ኑረዲን ሃሰን የተባለው የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪ በእስር ቤት ራሱን ማጥፋቱን መንግስት አክሎ አስታውቋል። ...

Read More »

በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጰያውያን ስደተኞች የርሀብ አድማ ጀመሩ።

ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀርመን-ባየርን ክልል የሚገኙ ወደ 60 የሚጠጉ ኢትዮጰያውያን ስደተኞች የረሀብ አድማ ለማድረግ የተገደዱት የኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ በጀርመን ካሉ አካባቢዎች በተለየ መልኩ በባየርን ክልል እና ፍርድ ቤት ተቀባይነት ስለማያገኝ ነው። በከተማ መሀል ላይ በመሰባሰብ ባለፈው ረቡእ የተጀመረው የኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የረሀብ አድማ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤  በአሁኑ ወቅት የሶሪያ፣የሊቢያ እና የኢራቅ ስደተኞችም በአድማው ከኢትዮጵርያውያኑ ጋር እየተቀላቀሉ ነው። ...

Read More »

የቡድን 7 አገራት ከድሃ አገራት በህገ ወጥ መንገድ የሚወጣውን ገንዘብ ለመቆጣጠር በድጋሜ ቃል ገቡ

ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ በእንዱስትሪ ሃብታቸው የበለጸጉት 7ቱ አገራት ከድሃ አገሮች እየተዘረፈ በምእራባዊያን ባንኮች የሚቀመጠውን ገንዘብ ለመቆጣጠር በድጋሜ ቃል ገብተዋል። የቡድን 7ቱንአገራትአቋምያደነቀውግሎባልፋይናንሻልኢንተግሪቲ፣ቃሉበተግባርመለወጥእንዳለበትአሳስቧል። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንትግሪቲ ከኢትዮጵያ በ9 አመታት ውስጥ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ መውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ወደ ውጭ የወጣው ገንዘብ ኢትዮጵያ በዚህ አመት ከመደበችው 8 ...

Read More »

በሀረር ከተማ በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ

ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአቦከር መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የታሰሩት የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ካጠናቀቁ በሁዋላ ከግቢያቸው በመውጣት መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ማሃል ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ነው። ተማሪዎቹ “በሀረር ክልል የሚታየው አድሎ ይቁም፣ ፍትሃዊ አስተዳደር ይኑር፣ መንግስት በህዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል ይቁም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች እያሰሙ ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ አርፍደዋል። የክልሉና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ተቃውሞውን የተቆጣጠሩት ሲሆን፣ ...

Read More »

በባህርዳር 27 ወጣቶች ታሰሩ

ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማዋ አውቶቡስ መናሃሪያ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ 27 ወጣቶች ጣቢያ 2 ወደ ሚባለው እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ከታሰሩት መካከል 9ኙ በማግስቱ ሲፈቱ ቀሪዎቹ አሁንም በእስር ላይ ናቸው። ከተፈቱት መካከል አንዳንዶቹ  ያለምንም ምክንያት ወይም የፖሊስ ምርመራ ታስረው እንደተለቀቁ ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የባህርዳር ፖሊስ ጽ/ቤትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Read More »

በአዲስ አበባ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በደቡብ ሱዳን ሰላም  ሊያሰፍን አልቻለም ተባለ

ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቡዩን እንደዘገበው ብዙ በኢጋድ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በአገሪቱ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም አልቻለም። በፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና በተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር መካከል የሚካሄደው ጦርነት የበርካታ ደቡብ ሱዳናውያንን ህይወት እየቀጠፈ ነው። የሰላም ስምምነቱ ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገራት የሰላም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

Read More »

በጊኒ በተከሰተ የኢቮላ ቫይረስ በትንሹ 208 ሰዎች መሞታቸውን  የዓለም የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት አስታወቁ።

ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለስልጣናቱን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደሰገበው፤ ካለፈው ሜይ እስከ ጁን ድረስ ባለው የአንድ ወር ጊዜ ጊኒ ውስጥ በ ኢቦላ 21 ሰዎች ሲሞቱ 37 አዲስ ተጠቂዎች ተመስግበዋል። ይህም በምእራባዊቱዋ አፍሪቃሀገር በኢቦላ የተጠቁትን ሰዎች አጠቃላይ ድምር ወደ 328 ከፍ ይደርገዋል። ኢቦላ ፤መድሀኒት የሌለው፣  ክትባት ያልተገኘለት እና በዓለማችን ዋነኛ ገዳይ በሽታዎች ተብለው ከተመሰገቡት መካከል አንዱ ነው። በርካታዎች የሞቱት ...

Read More »

በደብረ ዘይት ነዋሪዎች ብሄራቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲያስመዘግቡ መገደዳቸው አስግቶዋቸዋል

ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ ቀበሌ አንድ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት ፖሊሶች ከስቪል ሰራተኞች ጋር በመሆን ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ብሄር እና ሃይማኖት ሲመዘግቡ ውለዋል። “የምዝገባው አላማ ሰዎችን እየመረጡ ለማፈናቀል ሊሆን ይችላል” በማለት ስጋታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ብሄርን መመዝገቡ ለምን እንዳስፈለገ ሲጠይቁ ከላይ የተላለፈ መመሪያ ነው በሚል እንደተነገራቸው ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ...

Read More »