ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ የሆኑት ሬክማቻር በናስር በተባለው ከተማ እንደ አዲስ በተነሳው ጦርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ወታደሮችንና ንብረቶችን ማውደማቸውን ሲገልጹ የናስር ከተማን ደግሞ በእጃቸው ማስገባታቸውን እየተናገሩ ነው። ሬክማቻር ምንጮቻቸውን ጠቅሰው እንደተናገሩት 3 የሚሆኑ የጦር ተሽከርካሪዎችን አውድመው በመቶዎች የሚቆጠሩ(100) የመንግስት ወታደሮችን መግደላቸውን ሲናገሩ የመንግስቱ የጦር አዛዝ የሆኑት ፓል ማሎንግ አዋን ማስተባበላቸውንና የሬክማቻር ቡድን በኢጋድ የተፈረመውን የተኩስ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውጥረት ሰፍኖ ሰንብቷል።
ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሃ ቤቴ ወረዳ በአለም ከተማ ከመብራት ማሰራጫ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ አንድ ሰው ከፌደራል ፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ቆስሏል። መብራት ሃይል የከተማውን የመብራት ማሰራጫ በማንሳት ወደ ሌላ አካባቢ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲጀምር የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ አሰምቷል። እሁድ እለት ወደ ከተማዋ የገባው የፌደራል ፖሊስ ከህዝቡ ጋር ፊት ለፊት መጋጨቱን ፣ ህዝቡ በድንጋይ ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበት ቦታ እስካሁን ይፋ አልሆነም
ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበትን ቦታ ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ትክክለኛ ቦታውን ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጅ በማእከላዊም ሆነ በቃሊ እስር ቤት አለመኖራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የገዥው ፓርቲ ሰዎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፕሮፓጋንዳ ስራ ለመስራት የተለያዩ ሰዎችን እያነጋገሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ኤርትራ ውስጥ ነበርን ያሉ እና በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያካሂዱ ” ...
Read More »ባለፈው አርብ በሙስሊሙ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ እርምጃ ” ጥቁር ሽብር” ነው ሲል ድምጻችን ይሰማ ገለጸ
ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታላቁአንዋርመስጂድበመንግስትየደህንነትኃይሎችናበፖሊስሀላፊዎችከቀናትበፊትታቅዶበሙስሊሙ ላይ በተወሰደእርምጃከ6 ሺ በላይየመንግስትቅጥረኛሲቪልለባሾችመሰታፋቸውን አስታውሷል። “ቅጥረኞቹየተከበረውየረመዳንወርየጁምአሰላትከመሰገዱበፊትበመስጊዱውጫዊሰሜናዊአቅጣጫግርግርበማስነሳትናከፖሊሶችጋርከሁለቱምአቅጣጫድንጋይበመወራወር የታለመውን ውጤትለማምጣትሞክረዋል” የሚለው ድምጻችን ይሰማ፣ በሁሉምአቅጣጫየነበሩናበአስርሺዎችየሚቆጠሩሙስሊሞችየጁምአሰላታቸውንእንዳይፈጽሙእክልከመሆናቸውም በላይበበርካታጾመኛሙስሊሞችላይእጅግአሰቃቂጭፍጨፋ”መፈጸሙን ገልጿል። “ሙስሊሙንከሁሉምአቅጣጫበቆረጣስልትለሰላትበተቀመጠበትበመቁረጥበነፍስወከፍበያዙዋቸውዱላዎችናየመሣሪያሰደፎችርህራሄአልባበሆነሁኔታመደብደባቸውንና መጨፍጨፋቸውን የገለጸው ደምጻችን ይሰማ፣ በእለቱየተወሰደውመንግስታዊሽብር ‹‹ጥቁርሽብር›› የሚልስያሜተሰጥቶታል ብሎአል። ” ‹‹ጥቁርሽብር›› በሰለጠነውይይትከማያምን፣ሰላማዊነትናዲሲፒሊንከማይገባውመንግስትየሚፈልቅ፣ሰዎችሳይሆኑዱላብቻየሚናገርበት፣ሐሳብየሚንሸራሸርበትሳይሆንነውጥናግፍ የሚሰፍንበትሂደትነው ” ብሎአል። ‹‹ጥቁርሽብር›› አይናቸውንየጋረደውጥቁርግርዶሽየህዝብንእውነታእንዳይረዱያደረጋቸውናብቃትየሌላቸውኃላፊዎችየሚወስኑት፣ሰብዓዊነትበጭካኔጭለማውስጥየሚሰጥምበት አስከፊክስተትመሆኑን የጠቀሰው ድምጻችን ይሰማ፣ ለሰላማዊሕዝብናጥያቄምላሹንዱላያደረገኃይል፣ባልታጠቀናበእጁድንጋይባልጨበጠጾመኛሕዝብላይየጥይትቃታየሚስብ መንግስት ከርሞምየሚነዳውበ‹‹ጥቁርሽብር›› ብቻነው ብሎአል። የሐምሌ 11/2006ንአሰቃቂየመንግስትጭፍጨፋየታሪክካስማበማድረግእለቱ ‹‹ጥቁርሽብር›› ሲባልከዚህበኋላያሉክስተቶችም ‹‹ከጥቁርሽብርበኋላ›› ወይም ‹‹ከጥቁርሽብርበፊት›› እየተባሉየሚዘገቡይሆናሉ ብሎአል። ስያሜውእስከመቼውምየሚዘልቅሲሆንለወደፊቱምበዚህየ‹‹ጥቁርሽብር›› አሻጥርውስጥየተሳተፉወንጀለኞችለፍርድየሚቀርቡበትጊዜሩቅእንደማይሆንእናምናለን ሲል ...
Read More »የአሜሪካ የበረራ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ በኩል በሚያቋርጡ በረራዎች ላይ ማስጠንቀቂያ አወጣ
ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስሪያ ቤቱ በመግለጫው በሰሜን ኢትዮጵያ ከ12 ዲግሪ የትይዩ መስመሮች እስከ ኤትዮ ኤርትራ ድንበር ባለው የአየር ክልል ምንም አይነት በረራ እንዳይካሄድ መክሯል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በዚሁ ክልል የሚያልፉ የንግድም ሆነ ሌሎች አውሮፓላኖችን ሊመታ እንደሚችል አስጠንቅቋል። የአሜሪካ መንግስት ማስጠንቀቂያ ካወጣባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል ኬንያ እና ሶማሊያ ይጠቀሳሉ። የአሜሪካ አቪየሽን እገዳ የጣለበት የሰሜኑ ክፍል የትግራይ ክልልን ...
Read More »የታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እህት ከስራ ታገደች
ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር። የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ የለንም፣ ላንቺ እንኳን ስራ፣ መሬቱም ...
Read More »በአዲስ አበባ በረመዳን ጾም ስገደት ላይ በነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በተወሰደ የጭካኔ እርምጃ ብዙዎች ተጎዱ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ለከፈልነው መስዋትነት አቻ ውጤት እናመጣለን” በሚል መፈክር የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት አምርቷል። የፌደራል ፖሊሶች ሆን ብለው ባስነሱት ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ቆስለዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ ባይችልም አንዳንድ ሙስሊሞች ስልክ በመደወል የተገደሉ ሙስሊሞች መኖራቸውን ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊሶች እርምጃ ለመውሰድ ሲዘጋጁ ...
Read More »በለንደን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድረጉ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ፣ የኢህአዴግ መንግስት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወሰደው ህገወጥ እርምጃ የእንግሊዝ መንግስት ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በስፍራው የነበረውን ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹን አነጋግረነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ አሸባሪዎችን እንዲዋጋላቸው በሚል ...
Read More »በዳንሻና ጸገዴ ወረዳዎች አካባቢ የብአዴን እና የህወሃት ታጣቂዎች ተፋጠው እንደሚገኙ ታወቀ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ በትግራይ ክልል በኩል ምን ያክል ...
Read More »የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት በ24 ሰአታት አገር ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ
ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሰአታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የታዋቂው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የወንድማቸውን ጉዳይ ለመከታተል በሚል ከ10 ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቢያመሩም፣ ከትናንት በስቲያ ደህንነት ጽ/ቤት ከተጠሩ በሁዋላ አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። በታዘዙበት ሰአት ለመመለስ እንደሚቸገሩ የተናገሩት ወ/ሮ ብዙአየሁ፣ የ 24 ሰአት ጊዜ የጊዜ ገደብ ከተሰጣቸው በሁዋላ ...
Read More »