የደቡብ ሱዳን አማጺዮች  እንደ አዲስ በተነሳው ግጭት  100 የመንግስት ወታደሮች መግደላቸውን አስታወቁ

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ የሆኑት ሬክማቻር በናስር በተባለው ከተማ እንደ አዲስ በተነሳው ጦርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ወታደሮችንና

ንብረቶችን ማውደማቸውን ሲገልጹ የናስር ከተማን ደግሞ  በእጃቸው ማስገባታቸውን እየተናገሩ ነው።

ሬክማቻር ምንጮቻቸውን ጠቅሰው እንደተናገሩት  3 የሚሆኑ የጦር ተሽከርካሪዎችን አውድመው በመቶዎች የሚቆጠሩ(100) የመንግስት ወታደሮችን መግደላቸውን ሲናገሩ የመንግስቱ የጦር አዛዝ

የሆኑት ፓል ማሎንግ አዋን ማስተባበላቸውንና የሬክማቻር ቡድን በኢጋድ የተፈረመውን የተኩስ ማቆም ስምምነት መጣሱን አስታውቀዋል::

በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ወኪል የአማጺያንን ድርጊት ያወገዘ ሲሆን ሁለቱንም አካሎች ወደሰላም ጠረጴዛ ውይይት እንዲመለሱ አሳስባል።

የአማጺያኑ ቡድን ወኪል ደግሞ የተባበሩት መንግስታትና በአቶ ስዩም መስፍን የሚመራው የኢጋድ አደራዳሪ ቡድን የብቃት ማነስ እንደሚታይባቸው እና በሳልቫኪር የሚመራውን ቡድንን ማ

ስገደድ እንደሚያንሳቸው ገልጿል::

በሌላ በኩል ደግሞ የሪክማቻር የፕሮቶኮል ዳይሪክተር የሆኑት ሓቲም ደንግ  ለራዲዮ ታማዙጅ)  በናስር ከተማ ጦርነት ከመነሳቱ ከዛሬ ሁለት ቀን በፊት አቶ ስዮም መስፍን እና  ሪክ ማቻር በአዲስ አበባ

ከተማ ሚስጥራዊ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጿል::