የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እስር በመቃወም በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፊታችን አርብ በቤልጂየም ብራሰልስ በሚደረገው ተቃውሞ በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

ላይ የተወሰደውን እርምጃ ያወግዛሉ።

የተቃውሞ ሰልፉ  በብራሰልሰሹማንአደባባይ እኤአ ጁላይ 25 ቀን ከቀኑ 13 ፡30 እስከ 17 ሰአት ይካሄዳል። ነገ ረቡዕ ደግሞ በጀርመን በርሊን እንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚኖር ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢሳት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታሰሩበትን ቦታ ለማወቅ እያደረገ ያለው ጥረት  አለመሳካቱን መዘገቡን ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች መረጃዎችን እየሰጡ ነው። አንዳንድ ወገኖች

አቶ አንዳርጋቸው ደብረዘይት በሚገኘው አየር ሃይል ግቢ ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑንና በግቢው የሚገኙ ወታደሮች የሚደርስባቸውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እየሰሙ ስሜታቸውን

መቆጣጠር እንዳቃታቸው ገልጸዋል። ኢሳት አቶ አንዳርጋቸው የታሰሩበትን ቦታ በትክክል እንዳወቀ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።