የታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እህት ከስራ ታገደች

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር።

የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ የለንም፣ ላንቺ እንኳን ስራ፣ መሬቱም እሳት ሆኖ ያቃጥልሻል ” በማለት ከስራዋም ከህወሃት አባልነትም እንዳባረሩዋት ድርጅቱ አስታውቋል።

የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኣባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ የዓረና መስራችና ኣመራር ኣባልነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወይዘሮኣልጋነሽገብሩበህወሓትመንግስት “ኣሸባሪ” ተብላከተከሰሰችጀምሮ 3ቱ ህፃናት ልጆቿ የጎዳና ሂወት መምራት መጀመራቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

ህፃናቱ  ኣባታቸውንከ9 ዓመትበፊትበሞትያጡሲሆኑ፣  ጠላ እየጠመቀች ታስተዳድራቸው የነበረችው እናታቸውን በእስር ምክንያት ካጡ ብሗላ ትምህርታቸው ኣቋርጠው ፣የጎዳና ሂወት መግፋት ጀምረዋል።

እናታቸውበ”ኣሸባሪነት” ተፈርጃ በእስር ያጡህፃናትን ለመንከባከብ በህብረት ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ በ202 041 606 379 3018 የሚልየአካውንት ቁጥርተከፍቷል።

የሂሳብ ደፍተሩ የተከፍተው በወይ ዘሮ ኣልጋነሽ ታናሽ እህት  ወይዘሮ ፅጌ ገብሩነው።