የአሜሪካ የበረራ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ በኩል በሚያቋርጡ በረራዎች ላይ ማስጠንቀቂያ አወጣ

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስሪያ ቤቱ በመግለጫው በሰሜን ኢትዮጵያ  ከ12 ዲግሪ የትይዩ መስመሮች እስከ ኤትዮ ኤርትራ ድንበር ባለው የአየር ክልል ምንም

አይነት በረራ እንዳይካሄድ መክሯል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በዚሁ ክልል የሚያልፉ የንግድም ሆነ ሌሎች አውሮፓላኖችን ሊመታ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

የአሜሪካ መንግስት ማስጠንቀቂያ ካወጣባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል ኬንያ እና ሶማሊያ ይጠቀሳሉ።

የአሜሪካ አቪየሽን እገዳ የጣለበት የሰሜኑ ክፍል የትግራይ ክልልን የሚሸፍን ነው። በዚህ አካባቢ ምንም አይነት በረራ እንዳይካሄድ መባሉ ብዙ አስተያየቶችን እንዲሰጡ እያደረገ ነው።