በአዲስ አበባ በረመዳን ጾም ስገደት ላይ በነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በተወሰደ የጭካኔ እርምጃ ብዙዎች ተጎዱ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ለከፈልነው መስዋትነት አቻ ውጤት እናመጣለን” በሚል መፈክር የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት አምርቷል። የፌደራል ፖሊሶች ሆን ብለው ባስነሱት ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ቆስለዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ ባይችልም አንዳንድ ሙስሊሞች  ስልክ በመደወል  የተገደሉ ሙስሊሞች መኖራቸውን ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊሶች እርምጃ ለመውሰድ ሲዘጋጁ እንደነበር የኢሳት ምንጮች አስቀድው መረጃ የላኩ ሲሆን፣ በሙስሊም ስም መታወቂያ የተሰራላቸው የደህንነት አባላት ከሙስሊሙ መሃል በመሆን እየጠቆሙ ሲያሲዙ መዋላቸውን ለማወቅ ተችሎአል።