.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአዲስ አበባ መስተዳድር በቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለምርጫ እንዲደርስ በሚል አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት  ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባቁጠባቤቶችኢንተርፕራይዝእስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን  በሰንጋተራእና ቃሊቲ ክራውን ሆቴልበመሳሰሉአካባቢዎችላይእየገነባመሆኑየታወቀሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶችእስከሚቀጥለውዓመትአጋማሽድረስለዕድለኞችለማስተላለፍታቅዷል። የአስተዳደሩምንጮችእንደገለጹትቤቶቹከቀጣይዓመትምርጫበፊትሙሉበሙሉ ተጠናቀውእንዲተላለፉከአስተዳደሩመመሪያተሰጥቷል። ሆኖም ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራምየተመዘገበውጠቅላላሕዝብቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን  በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን የመገንባትአቅምባለመፍጠሩየተመዘገቡትንብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታትበላይጊዜንእንደሚፈልግየአስተዳደሩምንጮችአስታውቀዋል፡፡ ይህደግሞ ከዛሬ ነገየመኖሪያቤትባለቤትእሆናለሁብሎተስፋላደረገውሕዝብተስፋ አስቆራጭዜናነውብለዋል፡፡ በ20/80 ...

Read More »

በአንዋር መስጊድ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሙስሊሞች በድጋሜ ተቀጠሩ

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በአንዋር መስጊድ የተፈጠረውን ተቃውሞ መርተዋል በሚል ከታሰሩት መካከል 6 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የዋስትና መብታቸውን ተነጥቀው ለሰኞ ችሎት እንዲቀርቡ ታዘዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ወ/ት ወይንሸት ሞላ ፣ የፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ ሙሃመድ እና ኢብራሂም አብዱልሰላም በ5 ሺ ብር  ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት በድጋሜ አዟል። እስረኞቹ ቀደም ብሎ እንዲለቀቁ ትእዛዝ ...

Read More »

ፖሊሶች በአበል ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳግማዊ ሚኒልክና በሌሎችም አካባቢዎች የሚሰለጥኑ ፖሊሶች በቀን የሚታሰብላቸው ገንዘብ በቂ ባለመሆኑ ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊሶቹ ለቁርስና ምሳ እንዲሁም ለሻሂና ቡና 24 ብር በቀን የሚታሰብላቸው ቢሆንም፣ ገንዘቡ አይበቃንም በሚል ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊሶቹ  ስልጣናውን ሳያቋርጡ ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለማግባባት እየሞከሩ ነው። በዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ውስጥ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ከ500 በላይ ፖሊሶች እየሰለጡ ነው። ስልጣናው ...

Read More »

በአዲስ አበባ መስተዳደር የነተጠቀ ቦታ በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት እንዲመለስ ታዘዘ

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆኑ በአዲስ አበባ ለአመታት ታጥረው የተቀመጡ የግንባታ ቦታዎች፣ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት እንዲነጠቁ ውሳኔ አስተላልፈው ውሳኔውም ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጅ ሪፖርተር እንደዘገበው ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤ የግባኝ በማለታቸው የተወሰደባቸው ቦታ እንደሚለስላቸው መደረጉንና የመስተዳድሩ ውሳኔ መቀልበሱን ገልጿል። ተወስደው የነበሩት ቦታዎች ልደታ ክ/ከተማ ዋቢ ሸበሌ ጎንና በየካ ክፍለከተማ በሻሌ ሆቴል አካባቢ እንደሚገኙ ...

Read More »

ኬንያ በኢቦላ በሽታ የመጠቃት እድሏ ከፍተኛ ነው ተባለ

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊኒ ፣ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ የታየው የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት እንዳይዛመት ከፍተኛ ስጋት በደቀነበት በዚህ ወቅት፣ ከምስራቅ አፍሪካ ኬንያ በበሽታው ከሚጠቁ ቀዳሚ አገራት ተርታ ተሰልፋለች።ኬንያ የብዙ የምእራብ አፍሪካ አገራት የትራንስፖርት ማእከል በመሆኗ በበሽታው የመጠቃት እድላን ከፍ እንዳደረገው የተባበሩት መንግስታት የጤና ድርጅት አስታውቋል። ጀርመን ዜጓቿ ከላይበሪያ፣ ጊኒና ሴራሊዮን እንዲወጡ ስታዝ፣ጋናደግሞየትምህርት ቤት የመክፈቻ ጊዜን አራዝማለች። ...

Read More »

በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብድራፊ ከተማ ህዝብ በሸፍቶች እየተዳደርን ነው ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናት በመያዝ ከአብድራፊ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በአስተዳደር እና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት መማረሩን ተወካዮቹ ተናግረዋል። አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ ህዝቡ በመብራት፣ ውሃ እና በመንገድ ችግር እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላ ተናጋሪ ደግሞ ህዝቡ በድብቅ ጠመንጃ እየተዳደረ መሆኑንና  ወረዳው ህዝቡን ማስተዳዳር እንደተሳነው ገልጸዋል። በትግራይ ክልል የድብቅ ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ አቋም እንዲይዝ ጠየቁ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢ/ር ይልቃል ከ20 የአውሮፓ ህብረት አገራት ልኡካን ጋር በህብረቱ ጽ/ቤት ተገኝተው በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት ፣ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር ወደ ባሰ ችግር ሳትገባ ህብረቱ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል። ኢ/ር ይልቃል ገዢው ፓርቲ ስለሚያደርገው አፈና፣ በሚዲያው ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ፣ በእስር ላይ ስለሚገኙት ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና ጸሃፊዎች የተናገሩ ሲሆን፣ ኢህአዴግ በርእዮታለም መደናበርና በአመራር ብቃት ማነስ መቸገሩን በመግለጽ መጪውን ...

Read More »

ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢያነ ህጎች እና ዳኞች፣የፈደራልማረሚያቤቶችባለስልጣናት፣የፌደራልናየአዲስአበባፖሊስ አመራሮችናየደህንነትሃላፊዎችበአቶአባዱላገመዳአሰልጣኝነት  የኢትዮጵያህዝቦችትግልናሃገራዊሕዳሴያችንበሚልርእስስልጠናጀምረዋል። ስልጠናው ምናልባትም በቅርቡበቀድሞውም/ል ጠ/ሚ  አዲሱለገሰ  በቀረበዉና የኢህአዴግን የአመራር ችግር በሚዘረዝረውን  ጥናት ላይ ለመወያየት ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች ጠቁመዋል። በዚህጥናትኢህኣዴግበከፍተኛየአመራርእጥረትእየተቸገረመሆኑን፣ኦሮሞየሆኑየኦህዴድኣባላትሙሉበሙሉወደኦነግእንዳደሉእንዲሁምደግሞ፣የአማራው ክፍልየሆነውብሄረ አማራዲሞክራሲያዊንቅናቄ ከግንቦት7 ጋር ሽርክና መፍጠሩን መግለጻቸው ይታወሳል። አቶ አዲሱ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ ሊሳካ ያልቻለው በአመራር ችግር ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል። ስብሰባው ነሃሴ5የተጀመረሲሆንለ3 ሳምንት ያክል ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል።

Read More »

የኢሳት 4ኛ አመት በኒውዚላንድ ተከበረ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈዉ ቅዳሜ ኦገስት 2፣2014 በኒዉዚላንድ አገር በኦክላንድ ከተማ በተደረገዉ የኢሳት አራተኛ አመት በዓል አከባበር በርካታ ኢትዮጵያዉያኖች ቦታዉ ተገኝተው በአሉን አክብረዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባት የሆኑት የ በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ አባል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ቃለ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን፣ አቡነ ሳሙኤል ባደረጉት አጭር ንግግር ኢትዮጵያዉያኖች ይህንን ለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ እያገለገለ ያለ ...

Read More »

በቡርጅና ቦረና ኦሮሞዎች መካከል ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉን መድረክ አስታወቀ

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባወጣው መግለጫ በቡርጅ ብሄረሰብና በቦረና ህዝብ መካከል ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው መልካም ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጸረ-ሰላም ሃይሎች እየደፈረሰ እንደሚገኝ ገልጿል። ከ2 ሺ በላይ የሆኑ የቡርጅ ብሄረሰብ አባላት ከታህሳስ ወር 2006 ኣም ጀምሮ  ከአካባቢው ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሰገን ዞን በመሰደድ አስቸጋሪ ...

Read More »