.የኢሳት አማርኛ ዜና

በረሀቡ ምክንያት ዜጎች መሰደድ ጀምሩ

ኀዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር እብናት ወረዳ በሚገኙ 11 ቀበሌዎች አርሶአደሮች በቂ የሆነ እርዳታ ሊቀርብላቸው ባለመቻሉ በርካታ ሰዎች ቀያቸውን እየጣሉ በሌሊት መሰደዳቸው ታውቋል። እስካሁን ያልተሰደዱትም ቢሆኑ፣ በታጣቂዎች እየተጠበቁ መሆኑን ጉዳዩን ለማየት ወደ አካባቢው የሄዱ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዚህም ላይ ተረጅዎች የመሬት ግብር ክፈሉ ተብለው ሲገደዱ፣ “የት አምጥተን እንከፍላለን” ብለው መጠየቃቸውንና፣ የመንግሰት ካድሬዎች ” እርዳታ ...

Read More »

ኢህአዴግ በሚተማመንባቸው አባሎቹ ተተቸ

ኀዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝና ከቢኔያቸው በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ የሕዝብ ተወካይ ከተባሉ ሰዎች ጋር በተደረገው ውይይት ኢህአዴግ የኔ በሚላቸው አባሎችና ደጋፊዎች ከፍተኛ ወቀሳ ቀርቦበታል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመሩት የህዝብ አገልግሎትና የሰው ኃይል ልማት ሚ/ር አዘጋጅቶት ባለፈው ዕረቡ በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት በተካሄደው ውይይት ላይ በተለይ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ተቋማት የሚባሉት እንደፖሊስ፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ማረሚያ ...

Read More »

በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱ ፍርድ ቤት ቀርበው የደረሰባቸውን ስቃይ ተናገሩ

ኀዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት አቶ ባህሩ ደጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን፣ በምርመራ ወቅት በግዳጅ ቃላቸውን እንዲሰጡ በመርማሪዎቹ መደረጋቸውንና እራቁታቸውን መደብደባቸውን ከድብደባ ብዛት የተነሳም ሽንታቸውን መቆጣጠር እንደተሳናቸውና የራሳቸውን ሽንት እንዲጠጡ በመርማሪዎች መደረጋቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። ” አቶ ባህሩ የግንቦት 7ቱ መሪ ብርሃኑ ነጋ ምንህ ነው? ...

Read More »

በኦሮምያ ክልል የተማሪዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ኀዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ አዲሱን ካርታ ወይም ማስተር ፕላን ተከትሎ በክልሉ ተማሪዎች እያካሄዱት ያለው ተቃውሞ ቀጥሎ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። የክልሉ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ አድርጓል። በደቡብ ምእራብ ሸዋ ቶሌ ወረዳ ባንቱ ከተማ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ አንድ ደጀኔ ሰርቤሳ የተባለ 10ኛ ክፍል ወጣት ተማሪ የተገደለ ሲሆን፣ በምእራብ ...

Read More »

በጎንደር እስር ቤት ለሁለተኛ ጊዜ በእስረኞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

ኀዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ከተማ ከቀኑ 4፡30 ጀምሮ እስሰ 7፡00 ሰዓት የተክስ ልውውጥ ተካሂዷል፡፡ ሰሞኑን በተፈጠረው የአስር ቤቱ ቃጠሎ ህይወታቸው ያለፉት እስረኞች ቤተሰቦች ‹‹ እስር ቤቱ እስረኞችን ሊያስተምርና ወደ መልካም ህይወት ሊለውጥ እንጅ የራሱን ምክንያት እየፈጠረ ሊገድል አይችልም፡፡የሞቱ ልጆቻችንና ወንድሞቻችንን አስከሬን ስጡን ፡፡›› በሚል ጭቅጭቅ በተፈጠረ አለመግባባት መሳሪያ ከታጠቁት የሟች ቤተሰቦች ጋር የተኩስ ልውውጥ ...

Read More »

በሃዋሳ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ

ኀዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት ህዳር 21 ቀን 2008 ዓም ከ100 በላይ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ ነዋሪዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞውን ገልጸዋል። ፖሊሶቹ በወሰዱት አጸፋ እርምጃም በርካታ ሰዎች ተጎደተዋል፤ 24 ሰዎች ደግሞ ተይዘው ታስረዋል። በዚሁ ከተማ ህዳር ወር መግቢያ ላይ አንድ ቻይናዊ ዜጋ አንዱን ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ በፌሮ ደብድቦ የገደለው ሲሆን፣ ቻይናዊው ለጊዜው ...

Read More »

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የቀረበውን ይግባኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገው

ኀዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2 ኛ እስከ 5 ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ተጠይቆ እስር ቤቱ በተደጋጋሚ ጊዜያት ሳያቀርባቸው ቢቆይም፣ ተከሳሾቹ ለጠ/ፍርድ ቤት ባመለከቱት መሰረት፣ የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር ሆነው እንዳይቀርቡ ያቀረበውን ይግባኝ ህዳር 23 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ጠቅላይ ፍርድ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 በኦሮምያና በጎንደር የተፈጸሙትን ግድያዎች አወገዘ

ኀዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ በከተማዋ ዙርያ ያሉ ወገኖቻችንን ማፈናቀል በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው” ያለው አርበኞች ግንቦት7፣ በማስተር ፕላኑ ሰበብ የሚፈናቀሉ ገበሬዎች የሁላችን ወላጆች፣ ወንድሞችና እህቶች በመሆናቸው ይህንን ድርጊት በመቃወም ላይ ያሉት የኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ ንቅናቄው ከጎናቸው ይቆማል።” ብሎአል። በጎንደር ህወሓት ከሶስት ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ...

Read More »

በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሳው ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ ነው

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል መንግስት ያወጣውንና የኦሮምያ ክልል ምክር ቤት ወይም ጨፌ ኦሮምያ በአዲስ አመት የስራ ዘመኑ ያጸደቀው አዲሱን የአዲስ አበባ ካርታ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከደምቢዶሎ እስከ ሃረር ተዛምቷል። ተቃውሞውን ተከትሎ በብዙ የዩኒቨርስቲዎች፣ የሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ሊቀመንበር አቶ በቀለ ነገዓ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ...

Read More »

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ተነጋገሩ

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ትናንት ለአውሮፓ ህብረት አባላት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ንግግር ካደረጉ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ ከህብረቱ የተለያዩ ሃላፊዎች ጋር ሲነጋገሩ ውለዋል። በዛሬው ውሎአቸው በአውሮፓ ህብረት የተለያዩ የፓርላማ ኮሚቴ አባሎችን፣ የኮሚሽኑንና የካውንስሉን የተለያዩ ባለስልጣኖችን ረጅም ሰአት ወስደው አነጋግረዋል። ነገና ከነገ ወዲያም የተለያዩ የህብረቱን ባለስልጣናት ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል። በውይይታቸው ...

Read More »