በሃዋሳ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ

ኀዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት ህዳር 21 ቀን 2008 ዓም ከ100 በላይ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ ነዋሪዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞውን ገልጸዋል። ፖሊሶቹ በወሰዱት አጸፋ እርምጃም በርካታ ሰዎች ተጎደተዋል፤ 24 ሰዎች ደግሞ ተይዘው ታስረዋል።
በዚሁ ከተማ ህዳር ወር መግቢያ ላይ አንድ ቻይናዊ ዜጋ አንዱን ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ በፌሮ ደብድቦ የገደለው ሲሆን፣ ቻይናዊው ለጊዜው ታስሮ የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት ግን አልቀረበም። የሟቹ የቀብር ስነስርአት በይርጋለም ወረዳ ተፈጽሟል። የአካባቢው ባለስልጣናት ከሟቾች ጎን አለመቆማቸው ነዋሪዎች አሳዝኗል።