(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) በወልቃይ የወርቅ ቁፋሮ ላይ የተሰማሩ የወልቃይት ተወላጆች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተገልጸ። ልዩ ስሙ ኢድሪስ በሚባል የወርቅ ክምችት በሚገኝበት ስፍራ በወርቅ ቁፋሮ ስራ በተሰማሩ የወልቃይት ተወላጆች ላይ ድብደባውን የፈጸሙት በትግራይ ፖሊሶች የታገዙ በአካባቢው በሰፈሩ ሰዎች መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል በወልቃይት የማይጸብሪ ከተማ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል። ተቃውሞው በማንነታችን በእኩል እየታየን አይደለም በሚል እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሰሜን ወሎ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) በሰሜን ወሎ ያለው ውጥረት መቀጠሉ ታወቀ። በብአዴን አመራሮች የሚጠሩ ሰብሰባዎችም እየተበተኑ መሆኑ ተሰምቷል። ከቆቦ ጀምሮ እስከ መርሳ ዛሬ መንገዶች ዝግ ናቸው። ከቆቦ ወደ ትግራይ የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች በወታደሮች ታጅበው መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በወልዲያ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ወታደሮች በህዝቡ ላይ ግፍ እየፈጸሙ መሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከመርሳና ወልዲያ በትንሹ 500 ወጣቶች በአፋር ጭፍራ በረሃ ተወስደው በስቃይ ላይ ...
Read More »የወይዘሮ አዜብ መስፍን የውስጥ ሪፖርት ከአመታት በኋላ ተጋለጠ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት የሆኑ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን እንዲሁም ሌሎች ኩባንያዎችን በተመለከተ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀረቡት የውስጥ ሪፖርት ከአመታት በኋላ ተጋለጠ። በሃገሪቱ ህግ መሰረት የፖለቲካ ፓርቲ የመገናኛ ብዙሃን እንዳይኖረው ይከለክላል። ይህ ባለ 92 ገጽ ሪፖርት የሕወሃት ኩባንያዎችን ዝርዝር አፈጻጸምና ገቢያቸውን የተመለከተ እንደሆነም መረዳት ተችሏል። ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ሪፖርት ...
Read More »ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰየሙ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) የኬንያው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪና ዕጩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰይመው ቃለ መሃላ ፈጸሙ። በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት ቃለ መሃላውን ሲፈጽሙ ለማሰራጨት የተዘጋጁት የሀገሪቱ ሶስት የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጸጥታ ሃይሎች ተዘግተዋል። ይህን ተከትሎም በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውጥረት መስፈኑን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የ72 አመቱ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ በናይሮቢ ኡሁሩ ፓርክ ቃለ ...
Read More »መለስተኛ የበረራ ሰራተኞች ላይ እገዳ ተጣለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ መለስተኛ የበረራ ሰራተኞቹን ወደ አሜሪካና ካናዳ እንዳይበሩ እገዳ መጣሉ ተነገረ። አየር መንገዱ የበረራ ሰራተኞቹ ወደ አሜሪካና ካናዳ እንዳይበሩ የከለከለው ወደ ሁለቱ ሀገራት የሚመጡ ባልደረቦቹ በመጡበት ጥገኝነት እየጠየቁ በመቅረታቸው ነው። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ወር ብቻ 21 የበረራ ሰራተኞች ለስራ በወጡበት በካናዳና አሜሪካ ቀርተዋል። እናም የአየር መንገዱ መለስተኛ የበረራ ሰራተኞች በተለይ በአሜሪካና በካናዳ ለስራ እንደወጡ ...
Read More »ኤች አር 128 ለድምጽ አሰጣጥ ሊቀርብ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውና በአሜሪካ ምክር ቤት የወጣው ረቂቅ ሕገ ውሳኔ በምክር ቤቱ ለድምጽ አሰጣጥ እንደሚቀርብ ታወቀ። ሕገ ውሳኔው ለድምጽ አሰጣጥ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት መርማሪዎች በሀገሪቱ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲያጣሩ እስከሚቀጥለው ወር ድረስ የማይፈቅድ ከሆነ ነው። የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ከሌሎች የማህበረሰቡ ተወካዮችና ድርጅቶች ጋር በመሆን ትላንት ከአሜሪካ ምክር ...
Read More »የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመድበው ገንዘብ ተቸገረ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) በኢትዮጵያ ያለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ተባብሶ በመቀጠሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤምባሲዎችና ለቆንስላ ጽህፈት ቤቶች የሚመድበው ገንዘብ መቸገሩ ታወቀ። ኤምባሲዎቹ እየገጠማቸው ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ በየሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በኢንቨስትመንት ማበረታቻና በቤት መስሪያ ቦታ እያግባቡ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ቤት እንዲልኩ ታዘዋል። ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት የውጭ ምንዛሪ እየታየ ለኤምባሲዎቹ የበጀት ጉድለቱ እንደሚሸፈንላቸውም ተመልክቷል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ...
Read More »በመቄት ከተማ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) በሰሜን ወሎ መቄት ከተማ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። ከወልዲያ ወደ ደቡብ ጎንደር የሚወስደው መንገድም ተዘግቷል። በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ መነሳቱም ታውቋል። በሰሜን ወሎ በተለያዩ አካባቢዎች ውጥረት መቀጠሉ ታውቋል። መቄት ከወልዲያ ወደ ደቡብ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ላይ ከሚገኙ ከተሞች አንዷ ናት። በተለያዩ ጊዜያት በተነሱ ተቃውሞዎች መቄት ስሟ ሳይጠቀስ አያልፍም። ሰሞኑንም ሰሜን ወሎን ካዳረሰው ተቃውሞ ጋር ተነስታለች። የመቄት ነዋሪዎች የወልዲያውን ጭፍጨፋ ፣ ...
Read More »የወልዲያ እግር ኳስ ክለብ ተበተነ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) የወልዲያ እግር ኳስ ክለብ ተበተነ። የክለቡ ተጫዋቾች የተበተኑት በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል። የወልዲያ ክለብ ተጫዋቾችና አሰልጣኙ ከተማዋን ለቀው ሄደዋል ተብሏል። በሰሜን ወሎ የተለያዩ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ተጠናክሮ ነው የቀጠለው። የአካባቢውን ከተሞች በፍጥነት ያዳረሰው ተቃውሞ የሕይወትና የንብረት ጉዳት አስከትሏል። ሕወሃት ከመሃል ሀገር ወደ ትግራይ ሸቀጦችንና ወታደራዊ ቁሶችን የሚያሻግርበት መንገድም አገዛዙን በሚቃወሙ የሰሜን ...
Read More »የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን ያህል መድረሱ ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ በተከሰተው ግጭት የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን ያህል መድረሱን አለም አቀፍ ሪፖርቶች አመለከቱ። ስደተኞቹ በ4 መቶ ጣቢያዎች መስፈራቸውን ሪፖርቱን ያቀረቡት ተቋማት ገልጸዋል። ተፈናቃዮቹ በቂ እርዳታ እየተደረገላቸው አለመሆኑንም በሪፖርቱ ተመልክቷል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በተበራከተው ግጭት ምክንያት ተዘንግተዋል። በቀደሙ ሪፖርቶች 7 መቶ ሺ ሕዝብ መፈናቀሉ ሲነገር ነው የቆየው። ...
Read More »