.የኢሳት አማርኛ ዜና

ከሰሜን ወሎ የታፈሱት ወጣቶች በስልጠና ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ታወቀ

ከሰሜን ወሎ የታፈሱት ወጣቶች በስልጠና ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 12 ቀን 2010ዓ/ም) ከጥር 21 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ ከወልድያ፣መርሳና ሮቢት የተሰባሰቡ ዜጎች ጃሪ በሚባል የስሪንቃ እርሻ ምርምር የንብ ማንባት ምርምር የሚያደርግበት ጫካ ውስጥ መጣላቸውን የሚገልጹት ከእስር የተፈቱት ወጣቶች፣ ቦታው ፈፅም ለማረሚያ ቤት ያልተዘጋጀ መፀዳጃ ቤት የሌለው፣ውሀ ፣የህክምና ቦታ የሌለው ነበር ይላሉ። እስረኞቹ ሁኔታዎች ካልተሻሻሉ ምግብ ...

Read More »

የሡዳን መንግስት 8O የፖለቲካ እስረኞችን ለቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) የሡዳን መንግስት 😯 የፖለቲካ እስረኞችን ዛሬ ለቀቀ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ሃሰን ዑመር አልበሽር በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት ፖለቲከኞች፣ተማሪዎችንና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተፈቱት እስረኞች ባለፈው ወር መጨረሻ በካርቱም በተካሔደ የተቃውሞ ሠልፍ ተሣታፊ የነበሩ ናቸው፡፡ መንግስት በስንዴ ዋጋ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጐማ በማቆሙ ሣቢያ ባለፈው ወር አደባባይ የወጡት ሠልፈኞች መንግስትን ባወገዙበት ወቅት አስተባባሪዎቹ ታስረዋል። ከታሳሪዎቹ መካከል የሱዳን ዋነኛው ተቃዋሚ ኡማ ፓርቲ ...

Read More »

የአፍሪካውያን የመጀመሪያው ባንክ በኢትዮጵያውያን ሊቋቋም ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) በአሜሪካ የአፍሪካውያን የመጀመሪያው ባንክ በኢትዮጵያውያን ሊቋቋም ነው። “ማራቶን” የሚል ስያሜ የተሰጠውና ኑሯቸውን በውጭ ሀገር ባደረጉ ኢትዮጵያውያን የተመሰረተው ይህ ባንክ አስፈላጊዎቹን መመዘኛዎች አሟልቶ ለሚመለከተው አካል ማመልከቻውን ማስገባቱን ይፋ አድርጓል። ማራቶን ኢንተርናሽናል ባንክ በሚል ስያሜ የተቋቋመው ይህ የኢትዮጵያውያን ባንክ በጥቂት ወራት ግዜ ውስጥ በዋሽንግተን ዲሲ የመጀመሪያውን የባንኩን ቅርንጫፍ እንደሚከፍት የባንኩ ህዝብ ግንኙነት ለኢሳት ከላከው መግለጫ መረዳት ተችሏል። በባንክ ሙያ ...

Read More »

የሰማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን በኢትዮጵያና በተለያዩ የአለም ክፍሎች ለ81ኛ ጊዜ ታስቦ ዋለ። የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማዕታት ሀውልት ዙሪያ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበሩም ታውቋል። የኢትዮጵያ ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል በጣሊያን ወረራ ጊዜ በጄኔራል ግራዝያኒ ትእዛዝ በሶስት ቀናት ብቻ የተጨፈጨፉ 30 ሺህ ዜጎች የሚታሰቡበት ነው። በ1929 ለጣሊያን ንጉሳዊ ቤተሰብ አንድ ልዑል በመወለዱ በጀኔራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ ...

Read More »

623 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተዘጉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ አመት ብቻ 623 ትምህርት ቤቶች በድርቅና በተለያዩ የግጭት መንስኤዎች ምክንያት ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸው ተነገረ። ሲቭ ዘ ችልድረን የተባለው የሕጻናት አድን ድርጅት የኢትዮጵያን ትምህርት ሚኒስቴር ጠቅሶ እንደገለጸው በሃገሪቱ በድርቅና በግጭት ሳቢያ ባለፈው አመት ብቻ 4 መቶ ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል። አለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት እንደገለጸው በምስራቅ አፍሪካ የተወሰኑ ሃገራት ብቻ 4 ነጥብ 7 ...

Read More »

ሁሉን አቀፍ ንግግር እንዲጀመር የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) የኢትዮጵያ መንግስት ከሁሉም ወገኖች ጋር ሁሉን አቀፍ ንግግር እንዲጀምር የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ። የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በድንገት ከስልጣን የመልቀቅ ርምጃም በሃገሪቱ ያልተጠበቁ ሁኔታዎችን መደቀኑን ህብረቱ አስታወቋል። የአውሮፓ ህብረት ዛሬ ባሰራጨው በዚህ መግለጫ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንደገና መታወጁም በዘላቂ መፍትሄ ጥረቱ ላይ አደጋ መደቀኑንም ገልጿል። በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚዋቀረው መንግስት የተጀመሩ በጎ ርምጃዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሙሉ አቅም ሊኖረው ...

Read More »

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከእስር ተፈቱ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) ባለፈው ዓርብ ክሳቸው ተቋርጦ የነበረው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከእስር ተፈቱ። ለኮሎኔል ደመቀ አቀባበል ለማድረግ የተዘጋጀው የጎንደር ህዝብ ከአገዛዙ ታጣቂዎች ጋር መፋጠጡንም የደረሰኝ መረጃ አመልክቷል። ወጣት ንግስት ይርጋ ክሷ ተቋርጦ እንድትፈታ የተወሰነ ቢሆንም ከእስር ቤት እንዳልወጣች ለማወቅ ተችሏል። በተመሳሳይ እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክሳቸው እንዲቋረጥ ቢደረግም እስካሁን እንዳልተፈቱ ታውቋል። በሌላ በኩል በሽብርተኝነት ተከሰው በማዕከላዊ ከፍተኛ ስቃይ ሲደርስባቸው ...

Read More »

በአማራ ክልል በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) በአማራ ክልል ለሶስት ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ በተለይም በጎንደር አድማ ሙሉ በሙሉ የተካሄደ ሲሆን ከተማዋ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ውጭ ሆና መዋሏን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በደብረታቦር፣ በአዲስ ዘመንና በባህርዳር የአድማ እንቅስቃሴ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። የባህርዳሩን አድማ ለማስቆም የአገዛዙ ታጣቂዎች የሃይል ርምጃ እየተጠቀሙ መሆናቸው ታውቋል። በሰሜን ጎንደር በርካታ መንገዶችም ተዘግተዋል። በወልዲያ ተመሳሳይ የአድማ እንቅስቃሴ መኖሩ ...

Read More »

በወልቂጤ የሚደረገው አድማ ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

በወልቂጤ የሚደረገው አድማ ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ (ኢሳት ዜና የካቲት 9 ቀን 2010ዓ/ም) አድማው ወደ ጉብሪና አገና አካባቢዎችም መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መንገዶች ተዘጋግተዋል። ጎማዎችም በመንገዶች ላይ ተቃጥለዋል። ከቡታጅራ ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የነበሩ የሰው ማመላለሻ ተሽከርካሬዎች ወደ ቡታጅራ እንዲመለሱ ተደርጓል። ወደ ጅማ የሚወስደው መንገድም ተዘግቷል። በወልቂጤ ከተማ ሶላት ሰግደው ሲመለሱ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ተከፍቶ ጉዳት መድረሱን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ...

Read More »

የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ስልጣን መልቀቅ መሰረታዊ ጥያቄውን አይመልሰውም ሲሉ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ

የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ስልጣን መልቀቅ መሰረታዊ ጥያቄውን አይመልሰውም ሲሉ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ (ኢሳት ዜና የካቲት 9 ቀን 2010ዓ/ም) ኢሳት ያነጋገራቸው የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደገለጹት የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን መልቀቅ ህዝቡ የሚያነሳውን ዋናውን ጥያቄ የሚመልስ አይደለም፡ የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ግርማ በቀለ ፣ ውሳኔው በኦሮምያ ያለውን ውጥረት ለማስተንፈስ ተብሎ የተደረገ ነው ብለው እንደሚያስቡና ህዝቡ ...

Read More »