በወልቂጤ የሚደረገው አድማ ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

በወልቂጤ የሚደረገው አድማ ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ
(ኢሳት ዜና የካቲት 9 ቀን 2010ዓ/ም) አድማው ወደ ጉብሪና አገና አካባቢዎችም መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መንገዶች ተዘጋግተዋል። ጎማዎችም በመንገዶች ላይ ተቃጥለዋል። ከቡታጅራ ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የነበሩ የሰው ማመላለሻ ተሽከርካሬዎች ወደ ቡታጅራ እንዲመለሱ ተደርጓል። ወደ ጅማ የሚወስደው መንገድም ተዘግቷል።
በወልቂጤ ከተማ ሶላት ሰግደው ሲመለሱ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ተከፍቶ ጉዳት መድረሱን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ከተማዋ በአጋዚ እየተጠበች ነው ብለዋል። በርካታ ወጣቶች መያዛቸውንም ተናግረዋል።