የሡዳን መንግስት 8O የፖለቲካ እስረኞችን ለቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010)

የሡዳን መንግስት 😯 የፖለቲካ እስረኞችን ዛሬ ለቀቀ

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ሃሰን ዑመር አልበሽር በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት ፖለቲከኞች፣ተማሪዎችንና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተፈቱት እስረኞች ባለፈው ወር መጨረሻ በካርቱም በተካሔደ የተቃውሞ ሠልፍ ተሣታፊ የነበሩ ናቸው፡፡

መንግስት በስንዴ ዋጋ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጐማ በማቆሙ ሣቢያ ባለፈው ወር አደባባይ የወጡት ሠልፈኞች መንግስትን ባወገዙበት ወቅት አስተባባሪዎቹ ታስረዋል።

ከታሳሪዎቹ መካከል የሱዳን ዋነኛው ተቃዋሚ ኡማ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ፉዲላህ እንደነበሩበትም ታውቋል።

የሱዳን መንግስት ለተቃውሞው መነሻ በሆነው ጉዳይ ላይ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መፍትሔ እንደሚፈልግም ቃል ገብቷል፡፡

እስረኞቹ ዛሬ ከወህኒ ሲወጡ ቤተሰብና ደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሱዳን የመገበያያ ገንዘቧን ፓዉንድን መቀነሷን ተከትሎ በስንዴ ላይ ስታደርግ የነበረዉ ድጐማ መነሣቱ በሐገሪቱ ለተካሔዳው ተቃውሞና ለተከተለው እስር ምክንያት መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።