.የኢሳት አማርኛ ዜና

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚቀጥለው ሳምንት ከእስር ይፈታሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010)የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ዶክተር አብይ አሕመድ ትላንት በብሔራዊ ቤተመንግስት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ባካሄዱት ውይይት እንዳሉት ኢትዮጵያ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰሯ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር አጥታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተበላሸውን ኢሕአዴግ የማስተካከል ርምጃ እየወሰድኩ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በብሔራዊ ቤተመንግስት በተካሄደው ስነስርአት ላይ እንደተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ኢሕአዴግ ማሰሩ ...

Read More »

በቴፒ በሚካሄደው ተቃውሞ በርካታ ንብረት ወደመ

በቴፒ በሚካሄደው ተቃውሞ በርካታ ንብረት ወደመ (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በሾንጋ ግቢ ውስጥ ከሴት ተማሪዎች መደፈር ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ተቃውሞ ወደ ሚዛን አማን ከተማ ተዛምቶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ከፍተኛ ንብረት መዘረፉንና መውደሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የግቢው ውሃ በሚጠፋበት ጊዜ ሴት ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ወንዝ ሲወርዱ በአካባቢው ጎረምሶች በተደጋጋሚ እንደሚደፈሩ፣ ትናንት ደግሞ ሁለት ወንዶች ...

Read More »

ህወሃት ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሳዕረ መኮንን ለመተካት ግፊት እያደረገ ነው

ህወሃት ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሳዕረ መኮንን ለመተካት ግፊት እያደረገ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢህአዴግ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሹም ሽር ተከትሎ ለረጅም አመታት የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ሆነው የቆዩትን ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሰዓረ መኮንን ለማስተካት ህወሃት ግፊት እያደረገ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። በትግራይ ብሄርተኝነት ጽንፍ አቋም አላቸው የሚባሉት ጄ/ል ሰዓረ ኢታማዦር ሹም ሆነው የሚሾሙ ከሆነ፣ በኦህዴድና ...

Read More »

በአማራ ክልል የመማሪያ መጽሃፍት ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ መቀጠሉ እንዳሳዘናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ገለጹ፡፡

በአማራ ክልል የመማሪያ መጽሃፍት ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ መቀጠሉ እንዳሳዘናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በዚህ ዓመት ለሶስተኛ ክፍል ተብሎ በአዲስ መልክ በተዘጋጃው የሂሳብ መማሪያ መጽሃፍ ላይ ሆን ተብሎ የትግርኛ ማብራሪያ መለጠፉ በክልሉ መምህራንና ተማሪዎች ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር መሆኑን ምሁራን ተናገሩ፡፡ ከአሁን በፊት በብሄራዊ ፈተናዎች ላይ ተከስቶ የነበረው ስህተት፣የክልሉ መስህብ ቦታ ስለሆነው የራስ ዳሸን ተራራ መገኛ ...

Read More »

በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነብሮ ገዳዮችና አስገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቁ።

በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነብሮ ገዳዮችና አስገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቁ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ አፍሪቃ ለተቸገሩ ወገኖቹ ቀድሞ በመድረስ የሚታወቀው ገዛኸኝ ገብረመሰቀል ወይም ነብሮ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ እንደ አለኝታና መከታ የሚታይ ተወዳጅ ሰው ነው።ሜይል ኤንድ ዘጋርዲያን-ህልፈቱን ተከትሎ ባጠናቀረው ሰፊ ሀተታ እንዳስነበበው። ይህ ሀገር ወዳድ የቁርጥ ቀን ልጅ የዛሬ ወር አካባቢ ነበር በቅጥረኞች የመገደሉ ዜና የተሰማው። ...

Read More »

የተለያዩ ሀገራት 200 አትሌቶች ጥገኝነት ጠየቁ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) ለስፖርታዊ ውድድር አውስትራሊያ የገቡ 200 የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች ጥገኝነት ጠየቁ ። ለኮመን ዌልዝ ውድድር ባለፈው ሚያዚያ አውስትራሊያ የገቡት ከ200 የሚበልጡት አትሌቶች ጥገኝነት የጠየቁት ወደ ሃገራቸው ቢመለሱ ስቃይ እንደሚደርስባቸው በማመናቸው ነው። ብሪታኒያ እና በብሪታንያ ቅኝ የተገዙ ሃገራት በሚያደርጉት ውድድር ላይ ለመሳተፍ አውስትራሊያ ጎልድ ኮስት ከተማ ከገቡት 8 ሺህ ያህል አትሌቶች 205 ቱ ጥገኝነት ጠይቀዋል። ሌሎች 50 የሚሆኑት ደግሞ ...

Read More »

የሶማሌ ክልል የሃገር ሽማግሌዎችን ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) የሕወሃት ጄኔራሎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ የገቡትን የሶማሌ ክልል የሃገር ሽማግሌዎችን እያስፈራሩ መሆኑ ታወቀ። የሃገር ሽማግሌዎቹ ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ጫና እያደረጉ መሆኑም ታውቋል። የአብዲ ኢሌ አስተዳደር ለሕወሃት ጄኔራሎችና ለደህንነቶች ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ሽማግሌዎቹ ወደ ሶማሌ ክልል እንዲመለሱ ግፊት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል። ከአብዲ ኢሌ በድብቅ ገንዘብ ከተከፈላቸው ጄኔራሎቹ መካከልም ገብሬ ዲላና ማአሾ እንደሚገኙበትም የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል። ለአቤቱታ ወደ አዲስ ...

Read More »

የሜድሮክና ኢዛና የወርቅ አውጪ ኩባንያዎች ከመመሪያ ወጭ ወርቅ ሲሸጡ ነበር ተባለ

          (ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14 /2010 ) የሼህ መሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው  ሜድሮክ ጎልድ እንዲሁም የሕወሓት ንብረት የሆነው ኢዛና ጎልድ ከቤሄራዊ ባንክ መመሪያ ወጭ በልዩ  ድጋፍ ወርቅ ሲሸጡ መቆየታቸው ተገለጸ። በሌላም በኩል የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከብር ምንዛሪ  ለውጥ ጋር በተያያዘ መገምገማቸው ታወቀ ።ቤተሰቦቻቸውንም ወደ አሜሪካ አሽሽተዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሜድሮክ ጎልድ ባለፉት 20 ዓመታት ከሻኪሶ የሚያወጣውን ወርቅ ...

Read More »

በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ወደ ተቃውሞ ተቀየረ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ በአካባቢው አመጽ መቀስቀሱ  ተነገረ። የሚዛን ቴፒ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት አመጽም ትምህርት ተቋርጧል። በሚዛን ቴፒ ማጅ እና ጎጄብ መንገዶች ከመዘጋጋታቸው በተጨማሪ የንግድ መደብሮችም ተዘጋግተዋል። የመከላከያ አባላትና የፌዲራል ፖሊስ አመጹን ለማርገብ በሕዝቡ ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸ ተነግሯል። የሚዛን ቴፒ የሕዝብ ተቃውሞ ከጎጀብ ወንዝ በበቃ እንዲሁም ማሻ ይደርሳል። የተቃውሟቸው መንስኤ ደግሞ በተደጋጋሚ ...

Read More »

የህወሃት ጄኔራሎች የኢትዮ-ሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎችን እያስፈራሩ ነው

የህወሃት ጄኔራሎች የኢትዮ-ሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎችን እያስፈራሩ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) አቶ አብዲ ኢሌ በኢትዮ-ሶማሊ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ለከት የለሽ የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም፣ የፕሬዚዳንቱን ከስልጣን መነሳት ለመጠየቅ ከክልሉና ከውጭ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን፣ አቤቱታቸውን ለፌደራል ባለስልጣናት ለማቅረብ አዲስ አበባ መገኘታቸውን ተከትሎ የህወሃት ጄኔራሎችና ነባር የድርጅቱ አመራሮች ወደ አገር ሽማግሌዎች ቤት በመሄድ ዛቻና ማስፈራሪያ እያስተላለፉ መሆኑን ምንጮች ...

Read More »