.የኢሳት አማርኛ ዜና

መንግስት የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሬ አደረገ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲሱ ጭማሪ መሰረት በከተማ ሚኒባስ ታክሲ 1ብር ከ 35 ሳንቲም የነበረው 1ብር ከ40 ሳንቲም፣ 2 ብር ከ70 ሳንቲም የነበረው 2 ብር ከ80 ሳንቲም ሆኗል፡፡ 3 ብር ከ75 የነበረው 3 ብር ከ90 ሳንቲም፣ 3 ብር ከ90 የነበረው 4 ብር፣  5 ብር የነበረው 5 ብር ከ15 ሳንቲም ሆኗል፡፡ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ታሪፍ እንዲሁ 1 ብር ከ45 ...

Read More »

24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ኪሊማንጃሮ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠዉ ገቡ ያላቸዉን 24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ማድረጉን የኬንያ ኪሊማንጃሮ ክልል ፖሊስ አስታወቀ። የክልሉን የፖሊስ አዛዥ በመጥቀስ ዴይሊ ኒዉስ ባወጣዉ በዚሁ ዘገባ ኢትዮጵያዉያኑ ስደተኞች የተያዙት በታንዛኒያና በኬንያ ድንበር አካባቢ ታቬታ በተባለዉ ስፍራ ሲሆን የአካባቢዉ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተገልጿል። ፖሊስ በተጨማሪ ሕገወጥ ስደተኞቹን መንገድ እየመሩ ከድንበር ድንበር ...

Read More »

ከቃል ኪዳኑ ታቦት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ ሴራ እየተጠነሰሰ ነው

ታህሳስ 02 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እግዚአብሄር ለሙሴ ጽፎ የሰጠው የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚገኝበት ቦታ ለሺ አመታት አለምን አነጋግሯል፣ የበርካታ የታሪክ ተመራማሪዎችን ቀልብ ስቦ ቆይቷል፤፡ ታዋቂው ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ግርሀም ሀንኮክ ከአመታት በፊት ” ዘ ሳይን ኤንድ ዘ ሲል” በሚለው መጽሀፋቸው የቃል ኪዳኑ ታቦት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ የሚጠቁም መጽሀፍ አሳትመዋል። በመጽሀፋቸውም የካቶሊክ እና የአይሁድ እምነት ተከታዮች አውሮፓውያን ታቦቱን ፍለጋ ...

Read More »

የፌዴራል ፖሊስ በ11ኛው የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ላይ ሲሳተፉ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን በርካታ ወጣቶች በዋስ መፍታት ጀመረ

ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፌዴራል ፖሊስ በ11ኛው የኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ሩጫ   ላይ ሲሳተፉ በቂርቆስ፣ በቦሌ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ፖሊስ ጣቢያዎች በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን በርካታ ወጣቶች ከማክሰኞ ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በዋስ መፍታት ጀመረ እሁድ ህዳር 17 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ታላቁ ሕዝባዊ ሩጫ ላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ተዘርፎ በውጭ አገር ባንኮች የተቀመጠው 11 ቢሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ እንዲመለስ አንድ ታዋቂ ምሁር ገለጡ

ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአካውንቲግና የፋይናንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ሚንጋ ነጋሽ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት፣ በህግ፣ በወነጀል ምርመራ እና በተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይህን ገንዘብ ለማስመለስ በአንድነት ሆነው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ። ችግሩ በአንድ በኩል መንግስት በፖለቲካውና በንግዱ ውስጥ ጣልቃ መግባቱ የፈጠረው መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰር ሚንጋ፣ ሌሎች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዋነኝነት የሚያሽከረክሩት ኢፈርትና ...

Read More »

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እና ብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ውህደታቸውን አጽድቀው አንድ ውህድ ፓርቲ በመመስረት የፓርቲ ሊቀመንበር እንደሚመርጡ አስታወቁ

ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ  ቅዳሜ እና  እሁድ በዲአፍሪክ ሆቴል 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን የሚያካሂድና ውህደቱን የሚያጸድቅ ሲሆን ፣ ብርሃን ለአንድነት ፓርቲ ደግሞ እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ሆቴል ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ የፓርቲው ህልውና ይከስማል በአዲሱ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የፓርቲው ሊቀመንበር በቀጥታ በጠቅላላ ጉባዔ የምረጣል። የፓርቲውን ካቢኔ መርጦ በብሄራዊ ምክር ቤት ይሁንታ አስጸድቆ የሊቀመንበሩም ሥልጣን ...

Read More »

በአዲስ አበባ የፌዴራል ፖሊስ ጥበቃ ተጠናክሮአል ተባለ፣ የውጭ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊያንም በየቤታቸው እየተፈተሹ ነው

ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመዲናይቱ በሚገኙ ትላልቅ ፎቆችና ዋና ዋና መንገዶች ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ በመባል የሚታወቁት ተወርዋሪ የጥበቃ ኃይሎችና የደህንነት አባላት ሩጫ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ እየታየ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ዛሬ ዘገባ፤የፌደራል ፖሊሶቹ በየመንገዱ ዜጎችን በማስቆምና “ተለጠፍ“ በማለት ልዩ ፍተሻ እያደረጉ ይገኛሉ። የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን በየቤታቸው በሚመጡ ሦስት የፌደራል ፖሊስ አባሎች  ልዩ ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን  የገለጹት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላየት ቴሌቪዥን ቀደም ብሎ ይጠቀምበት የነበረውን የኢንተርኔት ቀጥታ ስርጭት ማሳያ ቲቪዩ ፕለየሩን ወደ ፍላሽ ፕለየር ቀየረ

ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀደም ሲል ኢሳትን በኢንተርኔት ለመከታተል  ቲቪዩ ፐልየር ሶፍት ዌርን መጫን ግዴታ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ አሰራር ግን በማንኛውም ኮምፒዩተር በፍላሽ ፕሌየር ስርጭቱን ለማየት ይቻላል። በርካታ ኢትዮጵያውያን አሰራሩን በተመለከተ ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።የኢሳት ማኔጅመንት ችግሩን ለመፍታት ባደረገው ጥረት  ኢትዮጵያውያን ቲቪዩ ፕለየር የተባለውን ሶፍትዌር ሳይጭኑ በየትኛውም ኮምፒዩተር ላይ በቀጥታ መመልከት የሚያስችላቸውን አሰራር ዘርግቷል። ቀጥታ ስርጭታችንን እንደተለመደው በ ...

Read More »

ደጃዝማች ዘውዴ ገብረስላሴ መለስ ዜናዊ የትግራይ አይሁዶችን ለመመስረት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመው እንደነበር ተገለጠ

ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እውቁ የታሪክ ባለሙያ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ኢትዮጵያን ያገለገሉት፣  ከሶስት አመታት በፊት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ደጃዝማች ዘውዴ ገብረስላሴ ፣ የመለስ ፖሊሲ አገሪቱን እንደማይጠቅማትና ለትግራይ ህዝብም አደገኛ መሆኑን ተናግረው እንደነበር፣ ከእርሳቸው ጋር ቅርበት የነበራቸው ሰው ገለጠዋል። ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉት ምንጫችን እንደተናገሩት፣ ደጃዝማች ዘውዴ ይህን የተናገሩት በዶ/ር ክንፈ አብረሀ ይመራ የነበረውንና አሁን አቶ ስብሀት ...

Read More »

የምስራቅ ጎጃም ህዝብ በኢህአዴግ ባለስልጣናት ላይ ያለውን ተቃውሞ ገለጠ

ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በአማራ ክልል “የህዝብን ቅሬታ ለማስታገስ” በሚል ምክንያት ፣ ብአዴን በክልሉ ያካሄደው   ግምገማ ንቅናቄው ያልጠበቃቸው ነገሮች በመከሰታቸው ግምገማውን ለመሰረዝ ተገዷል። በምስራቅ ጎጃም ዞን በተካሄደው ህዝባዊ ግምገማ ህዝቡ “ኢህአዴግ የ ችግርና መከራ ምንጭ ከመሆን ባለፈ ለአገሪቱ ያመጣም ምንም  ነገር የለም”  በማለት በድፍረት መናገሩን ዘጋቢያችን ገልጧል። በተለይ የደብረ ኤሊያስ አካባቢ የመኢአድ ደጋፊዎች “ተቃውሞዓችን በሙስና ከተዘፈቀ ስርአት ...

Read More »