የኢትዮጵያ ሳተላየት ቴሌቪዥን ቀደም ብሎ ይጠቀምበት የነበረውን የኢንተርኔት ቀጥታ ስርጭት ማሳያ ቲቪዩ ፕለየሩን ወደ ፍላሽ ፕለየር ቀየረ

ህዳር 29 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ቀደም ሲል ኢሳትን በኢንተርኔት ለመከታተል  ቲቪዩ ፐልየር ሶፍት ዌርን መጫን ግዴታ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ አሰራር ግን በማንኛውም ኮምፒዩተር በፍላሽ ፕሌየር ስርጭቱን ለማየት ይቻላል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን አሰራሩን በተመለከተ ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።የኢሳት ማኔጅመንት ችግሩን ለመፍታት ባደረገው ጥረት  ኢትዮጵያውያን ቲቪዩ ፕለየር የተባለውን ሶፍትዌር ሳይጭኑ በየትኛውም ኮምፒዩተር ላይ በቀጥታ መመልከት የሚያስችላቸውን አሰራር ዘርግቷል።

ቀጥታ ስርጭታችንን እንደተለመደው በ www.ethsat.com መከታተል ትችላላችሁ::

በዚህ አሰራር የተቸገሩ ወገኖች ” ወደ ኢሳት ሄልፕ ዴስክ” በመደወል ወይም በኢሜል በመጠየቅ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።