ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማላዊን ድንበር ሲያቋርጡ ከተያዙት ኢትዮጵያውያን መካከል አራቱ ረዥም ጊዜ በዘለቀ ረሀብ ሞተው አስከሬናቸው በሀይቅ ውስጥ ሲገኝ፤ ቀሪዎቹ 90 ኢትዮጵያውያንም በፍርድ ቤት ጥፋተኞች ተባሉ አሶሼትድ ፕሬስ የግብፅን አየር መንገድ ባስልጣናት ጠቅሶ ከካይሮ እንደዘገበው፤ ኢትዮጵያውያኑ በሱዳን ድንበር በኩል ወደ ግብፅ ገብተው የሲና በረሃን በማቋረጥ ወደ እስራኤል በሕገ ወጥ መንገድ ለመግባት ሲሞክሩ ነበር፤ በአየር መንገዱ ሰራተኞች አማካይነት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአውሮፓ ህብረት የስዊድን ጋዜጠኞችን ለማስፈታት ጫና የሚያደርግ ከሆነ እንደማይቀበሉት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ገለጡ
ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ለመንግስት ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የስዊድን መንግስት እስካሁን ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ ይፋዊ የሆነ ጥያቄ አለማቅረቡን ተናግረው ይሁን እንጅ የአውሮፓ ህብረት ከመደበኛው ድርድር ውጭ ጫና ለማሳረፍ ቢሞክር ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል። የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት እና የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋማትን “መንታ ምላሶች” በማለት አቶ ሀይለማርያም ወቀሰዋቸዋል ተችተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ባለበት አለማቀፍ ጫና የተነሳ የስዊድን ጋዜጠኞችን ለመፍታት ቢፈልግም፣ ...
Read More »አዳማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ
ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የፌደራል ፖሊሲ በስፍራው በመገኘት ግጭቱን አስቁሟል። ይህንን ተከትሎም በርካታ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን የኦሮሞ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ሲጮሁ፣ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳት ሲጠይቁ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ መምህር ግጭቱ የብሄር ግጭት ...
Read More »የኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት አባላት በአዲስ አበባ በራሪ ወረቀቶችን መበተናቸውን አስታወቁ
ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ በምስል በማስደገፍ በላኩት መረጃ፣ ወረቀቶችን የበተኑት በመርካቶ ፣ በስድስት ኪሎ፣ ጊዮርጊስ ፣ ሳሪስና ፒያሳ አካባቢዎች መሆኑ ታውቋል። ፖሊስ ወረቀቶች ከተበተኑ እና ከተለጠፉ በሁዋላ የወረቆቶችን ደብዛ ለማጥፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር የድርጀቱ አባላት ገልጠዋል። በቅርቡ በታላቁ ርጫ ላይ መንግስትን የሚቃወሙ ወረቀቶችን የበተኑ ወጣቶች መታሰራቸው ይታወሳል።
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ፤ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂድበትን አዳራሽ በማጣቱ በጽ/ቤቱ ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ
ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከስድስት ወራት በፊት የአንድ ሺህ አምስት መቶ መስራች አባላትን የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂድበትን አዳራሽ በማጣቱ ጠቅላላ ጉባኤውን በጽ/ቤቱ ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ። ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ፤ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂድበትን አዳራሽ በማጣቱ በጽ/ቤቱ ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ ከፓርቲው አደራጆች አንዱ የሆኑት የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት አባል ...
Read More »ኤርትራ፤”ገለልተኛ አይደለም”ያለችው የተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ጉዳይ አጣሪ ቡድን እንዲቀየር ጥያቄ አቀረበች
ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስብሰባ ላይ የቦምብ ጥቃት ለማድረስ ሴራ ጠንስሳ ነበር” በሚል የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አጣሪ ቡድን ያቀረበውን ሪፖርት እንደማትቀበለው በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል። “ኤርትራ ፤የአጣሪ ቡድኑን ሪፖርት ያልተቀበለችው፤ ፍትሃዊነት የሚጐድለውና በአድሎም የተሞላ ስለሆነ ነው” በማለት የየኤርትራ መንግስት በአጣሪ ቡድኑ ላይ ተቃውሞውን መግለጹም አይዘነጋም። በአዲስ መልክ የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ...
Read More »በእነ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በተከሰሱት ላይ የሚያቀርበውን ማስረጃ ማጠናቀቁን አቃቢ ህግ አስታወቀ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍርድ ቤቱ “አኬልዳማን” በተመለከተ እስረኞች ያቀረቡትን አቤቱታም ሳይቀበለው ቀርቷል። አቃቢ ህግ ፣ የብሄራዊ የጸጥታና የደህንነት ቢሮ ህጋዊ በሆነ መንገድ የጠለፋቸው መረጃዎች ናቸው ያላቸውን 2 የኦዲዮ ማስረጃዎች በእስክንድር ነጋ ላይ አቅርቧል። የኦዲዮ ማስረጃዎቹ እስክንድር ነጋ ከ16ኛ ተከሳሽ ከሆነው አበበ በለው ጋር ሲነጋጋር እንደነበር ያረጋገጣል ብሎአል። አበበ በለው የግንቦት 7 ቃል አቀባይና የኢሳት የቦርድ አባል ነው ...
Read More »በአዲስ አበባ የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቤቶች እየተስፋፉ ነው ተባለ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው በአዲስ አበባ ከተማ አንድ እና ሁለት የነበሩት የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቦታዎች በተለያዩ ክፍለ ከተሞችም እየተስፋፉ ነው። በመርካቶ ብቻ ሶስት የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቦታዎች መኖራቸውን የዘገበው ፎርቹን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በፒያሳ፣ ስድስት ኪሎና ሌሎች ቦታዎችም የጉርጫ ምግብ መሸጫ ቦታዎች መቋቋማቸውን ዘግቧል። ጉርሻ የሚባለው ከሆቴሎች የተረፈ ምግብ ወይም በተለምዶ “ቡሌ” ለአንድ ሰው ...
Read More »የአህባሽን እምነት ለመከተል ፈቃደኛ አልሆኑም የተባሉ 10 የእስልምና እምነት ተከታዮች ታሰሩ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር በአድርቃይ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሙስሊሞች የታሰሩት ፣ የአህባሽን አስተምህሮ የሚያስፋፉት የሙስሊም አባላት ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም ተብሎ ነው። ያለምንም ጠያቂና የፍርድ ቤት ሂደት ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ሙስሊሞቹ እየተሰቃዩ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። እስረኞቹ “የድረሱልን ጥሪ” ማሰማታቸውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሙስሊሞቹ የአካባቢው ተወካይ ለኢሳት ተናግረዋል። “ፍርድ አጣን፣ በአገራችን መኖር ...
Read More »27 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራርና አባላት ታሰሩ
ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ልዩ ዞን በዘንጋ አዋንዴ ቀበሌ ውስጥ 27 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራርና አባላት በገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች መታሰራቸውን መኢአድ አስታወቀ፡፡ የደምባ ጎፋ ወረዳ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ማዩ ማይጠሎ በበኩላቸው፣ የተጠቀሱት የመኢአድ አባላት የታሰሩት በአካባቢው እየተከናወነ ያለውን የልማት ሥራ ለማደናቀፍ በመንቀሳቀሳቸው ነው ይላሉ። መኢአድ እንዳስታወቀው፣ ታኅሣሥ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከታሰሩት ...
Read More »