.የኢሳት አማርኛ ዜና

1486ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል መውሊድ ተከበረ

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዓሉ በታላቁ አንዋር መስጊድ ሲከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬ ዚዳንት ሼህ አህመዲን ሼህ አብዱላሂ ሙስሊሙ በተለያየ መንገድ የሙስሊሙን አንድነት ለማደፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን እንዲከላከል አሳስበዋል፡፡ ከ50 ዓመታት በላይ የቆየውን የአወልያ ተቋም በአዲስ አደረጃጀት በመለወጥ ተቋሙን ወደ ሃይማኖታዊ ዩኒቨርስቲ ለመቀየር እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በርካታየኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአወልያ ኮሌጅ እንዲከፈት፣ የአህባሽ አስተምህሮ እንዲቋረጥና መጅሊሱ በአዲስ ...

Read More »

ጋምቤላ አሁንም በውጥረት ውስጥ ናት

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ክልል በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ሢሰሩ  የነበሩት   አቶ ጌታቸው አንኮሬ  ባልታወቁ ሰዎች በድንገት ተገደሉ። የ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ  እንደገለፀው፤ የደህንነቱ አባል መገደላቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል በክልሉ የነበረው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ የተባባሰ ሲሆን፤የክልሉ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችም ስጋት ላይ ወድቀዋል። የህወሃት አባል በመሆን በክልሉ ለረዥም ዓመታት በምስጢር የደኅንነት ሠራተኛነታቸው የሚታወቁት አቶ ጌታቸው ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ...

Read More »

አቶ መለስ በሳልቫኪር አቋም መበሳጨታቸው ተሰማ

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳንን ለመሸምገል ያቀረቡት የሰላም ሀሳብ በደቡብ ሱዳናዊያን ውድቅ በመደረጉ መበሳጨታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚያዉቁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለኢሳት ገልጡ። በቅርቡ ነጻ የወጣችው ደቡብ ሱዳን ከሰሜን ሱዳን ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ወደ ሰሜኑ የሚሄደውን የነዳጅ ዘይት አቋርጧለች። የደቡብ ሱዳን ውሳኔ በሰሜን ሱዳን ህዝብ ህልውና ላይ የተቃጣ በመሆኑ አገራቸው ደቡብ ሱዳንን ለመውረር እንደምትገደድ ...

Read More »

የኤድስ ፈንድ ለፖለቲካ ድጋፍ መሸመቻ እየዋለ ነው

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኤዲስ መከላከያ ተብሎ ከመንግስታት የሚለገሰው ገንዘብ ፣ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ጥቅም ማስገኛ እያዋለው መሆኑን የቀድሞው የተስፋጎህ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ተናገሩ። ተስፋ ጎህን ለረጅም አመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ታደሰ አይናለም ለኢሳት እንደተናገሩት በኤች አይቪ ቫይረስ ለተጠቁት ወገኖች ተብሎ ከግልኦባል ፈንድ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከተለያዩ በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች የሚለገሰው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ፣ በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ትእዛዝ ብቻ ...

Read More »

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ከአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ራሱን ማግለሉ ተዘገበ

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ2000 ዓም ለተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ዝግጅት ተብሎ በተቋቋመው የፓርቲዎች የምክክር  ምክር ቤት ታቅፈው በገዥው ፓርተ በተረቀቀው የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ላይ ከመከሩት የተቃዋሚ  ፓርቲዎች መካከል፤ በአቶ ልደቱ አያሌው የሚመራው ኢዴፓና  በኢንጂነር ሀይሉ ሻውል የሚመራው መኢአድ ዋነኞቹ ናቸው። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፤ ምክር ቤቱ የተዋቀረበትን ሂደት በመቃወሙና አደረጃጀቱ እንዲሻሻል በመጠየቁ ሳቢያ በኢህአዴግ ከመገፋቱም ...

Read More »

የመንግስትና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ፍጥጫ ቀጥሎአል

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለመንግስት ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጣቸው ግፊት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። በዛሬው እለት የአርብን ጸሎት ምክንያት በማድረግ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአወልያ መስጊድ ተገኝተው እንደነበር በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። ሙስሊሞቹ ከዚህ ቀደም ላቀረቡት የመብት ጥያቄ የመንግስትን መልስ ከተወካዮቻቸው ለመስማት በብዛት ቢገኙም፣ የጠበቁትን መልስ ለማግኘት አልቻሉም። የሙስሊሞቹ ተወካዮች ከመንግስት ጋር ተከታታይ ውይይት ለማድረግ በሚቀጥለው ሳምንት  ቀጠሮ ...

Read More »

አንድነት በሊዝ አዋጁ ዙሪያ እሁድ ውይይት ያደርጋል

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በሊዝ አዋጁ ዙሪያ የጠራው ስብሰባ በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚካሄድ ዶ/ር ነጋሶ ገለጡ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለኢሳት እንደገለጡት ፓርቲያቸው ህዝቡን በአገሩ መሬት አልባ እና ንብረት አልባ የሚያደርገውን አዋጅ አጥብቀው ይቃወማሉ። 3፡55-4፡34 ባለፈው ሳምንት ሊካሄድ የነበረው ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ምክንያት በማድረግ ሳይካሄድ እንደቀረ ዶ/ር ነጋሶ ገልጠዋል። 2፡16-2፡50 ...

Read More »

ተመድ የኢትዮጵያን መንግስት ድርጊት ኮነነ

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የፀረ ሽብር ህጉ  የህዝብን መብቶች አላግባብ ለማፈን በጥቅም ላይ መዋል እንደሌለበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፀ የመንግስታቱ ድርጅት ገለልተኛ የሰብኣዊ መብት የባለሙያዎች ቡድን በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ያለአግባብ በመወንጀልና እስራት በመፍረድ የፀረ ሽብር ህጉን በመጠቀም  የህዝብን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማፈን መንግሰት የሚፈፅመዉን ተግባር አውግዘዋል። “የመንግሰት ባለስልጣኖች የሚፈፅሟቸዉን የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመርና በማሳወቅ ሊኖራቸዉ የሚገባዉን ተጠያቂነት ...

Read More »

በሊባኖስ አንዲት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ እራሷን አጠፋች

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንዲት የ23 አመት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ በጋዲር ከስሩዋን በአሰሪዎቿ መኖሪያ ቤት ዉስጥ እራሷን በመስቀል ህይወቷን ማጥፋቷን የሊባኖስ ዴይሊ ስታር ገለፀ። ሳባ ማሩን በተባለዉ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ተሰቅላ ስለተገኘችዉ ኢትዮጵያ አሟሟት ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አሰሪዋ ራሚ አቡ ካሊል ለፀጥታ ሃይሎች ቃሉን እንዲሰጥ መደረጉን ከዜና ምንጩ በተጨማሪ ለማወቅ ተችሏል።

Read More »

በዋካ ከተፈጠረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩት ወጣቶች በገደብ ተፈቱ

ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት አራት ወራት በዋካ ከተፈጠረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩት ወጣቶች በገደብ ተፈቱ፣  ወጣቶችን በግንቦት 7 ስም ለመክሰስ ተዘጋጅቶ የነበረው ክስ በወጣቶቹ ጥንካሬ እንዲከሽፍ ተደርጓል። ለነጻነት ሰመአቱ የኔሰው ገብሬ ህልፈት ምክንያት የሆነው ፣ የዋካ ወጣቶች እስር የመንግስትን የፍትህ ስርአት ያጋለጠ እንደነበር የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጠዋል። በዋካ ከወረዳ እና ከመብት ጥያቄዎች ጋር በተነሳ ረብሻ በርካታ ...

Read More »